Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እንዴት እንደምትሰሙ ተጠንቀቁ

    ኦ፣ የሰው ልብ ምንኛ ተላላ ነው! ክፉ ከሆነ ነገር ጋር መስማማት ምንኛ ቀላል ነው! ከእግዚአብሔር ያልሆነውን ነገር ያለማቋረጥ ከማዳመጥና ከፍ ከፍ ከማድረግ የበለጠ የነፍስን ፍላጎት፣ ንጽህናውን፣ ለእግዚአብሔር እና ቅዱስና ዘላለማዊ ለሆኑ ነገሮች የሚኖረውን እውነተኛና ቅዱስ ሀሳብ የሚጎዳ ሌላ ነገር የለም፡፡ ልብን ይመርዛል፣ ግንዛቤንም ዝቅ ያደርጋል፡፡ ንጹህ እውነት የተቀባዩን ባሕርይ ከፍ ከፍ የማድረግ፣ የመሞረድ፣ እና የመቀደስ ተጽእኖ ስላለው ምንጩ መለኮታዊ ነው፡፡ የእውነት ሁሉ ምንጭ የሆነው ወደ አባቱ እንዲህ በማለት ጸልዮ ነበር፡- «ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፣ ከቃላቸው የተነሳ በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም፤ አንተ እንደላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፣ አንተ አባት ሆይ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፣ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ» (ዮሐ. 17፡ 20፣ 21)፡፡ መለያየትን ለመፍጠር እና ሰዎችን ከእውነት ለማራቅ ነገሮች በተደጋጋሚ ይነሳሉ፡፡ ይህ በሌሎች ላይ ጥያቄ ማንሳት፣ መንቀፍ፣ ማውገዝ እና መፍረድ የክርስቶስ ጸጋ በልብ ውስጥ ስለመኖሩ ማስረጃ አይደለም፡፡ አንድነትን አይፈጥርም፡፡ የዚህ ዓይነት ሥራ ጥልቅ በሆነ ኃጢአት ውስጥ ሆነው ሳለ አስደናቂ ብርሃን እንዳላቸው ይናገሩ በነበሩ ሰዎች ከዚህ በፊት ተፈጽሟል፡፡ መናፍቅነት፣ ታማኝ አለመሆን እና ውሸታምነት በእነርሱ ውስጥ ተደባልቀዋል፡፡ {2SM 78.3}Amh2SM 78.3

    አሁን ያለንበት ጊዜ ለእግዚአብሔር ሕዝብ ትልቅ አደጋ ያለበት ጊዜ ነው፡፡ እግዚአብሔር እየመራ ያለው እዚህና እዚያ ግለሰብን ሳይሆን ሕዝብን ነው፡፡ በምድር ላይ በእውነት የምትኖር ቤተ ክርስቲያን አለችው፤ ወንዶች ብቻ ሳይሆኑ ጨቅላ ልጃገረዶችም ቤተ ክርስቲያንን በመቃወም ሲጮኹ ስናይ እንፈራቸዋለን፡፡ እግዚአብሔር እንዳልላካቸው እናውቃለን፣ ነገር ግን ይሮጣሉ፣ የእነርሱን ያልተስተካከሉ ሀሳቦች የማይቀበሉ ሁሉ የእግዚአብሔርን መንፈስ እንደሚዋጉ ተቆጥረው ይወገዛሉ፡፡ እንደዚህ ያሉ ነገሮች ሁሉ በሰይጣን ሰልፍ ላይ ናቸው፣ አሁንም ሆነ ለዘላለም በቀጥታ የክርስቶስን ጸሎት በመቃወም የሚሰሩ ቢኖሩም የእግዚአብሔር ሥራ ወደ ፊት ይቀጥላል፡፡ እነርሱን ከሰይጣናዊ ፈጠራዎቻቸው ጋር ወደ ኋላ በመተው የእግዚአብሔር ሥራ ወደ ፊት ይቀጥላል፡፡. . . {2SM 79.1}Amh2SM 79.1

    «እንግዲህ እንዴት እንድትሰሙ ተጠበቁ (ሉቃስ 8፡ 1) የሚለው የክርስቶስ ማስጠንቀቂያ ነው፡፡ መስማት ያለብን በእሱ እንሄድ ዘንድ እውነትን ለመማር ነው፡፡ በድጋሚ፣ «ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ» (ማርቆስ 4፡ 24) ይላል፡፡ በጥንቃቄ መርምሩ፣ «ሁሉን ፈትኑ” (1ተሰ. 5፡ 21)፣ «መንፈስን ሁሉ አትመኑ፣ ነገር ግን ብዙ ሀሰተኛ ነቢያት ወደ ዓለም ስለወጡ መናፍስት ከእግዚአብሔር እንደሆኑ ወይም እንዳልሆኑ ፈትኑ” (1ዮሐ. 4፡1)፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ምክር ነው፤ እንሰማዋለን? -- Letter 12, 1890. {2SM 79.2}Amh2SM 79.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents