Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ማንም ቢሆን መታለል የለበትም

    እያንዳንዳችን ክፉኛ እንፈተናለን፤ እምነታችን እስከ መጨረሻው ይፈተናል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ሕያው ግንኙነት ሊኖረን ይገባል፤ የመለኮታዊ ተፈጥሮ ተካፋዮች መሆን አለብን፤ ያኔ በጠላት ዘዴዎች አንታለልም፣ በዓለም ውስጥ ከፍትወት የተነሳ ከመጣው ጥፋት ማምለጥም እንችላለን፡፡ {2SM 50.1}Amh2SM 50.1

    በእምነታችን ሥር ሰደን እና ጸንተን በክርስቶስ መመስረት ያስፈልገናል፡፡ ሰይጣን በወኪሎቹ አማካይነት ይሰራል፡፡ ከሕያው ውኃ ያልጠጡትን፣ ነፍሶቻቸው አዲስና እና እንግዳ ለሆነ ነገር የሚጠሙትን እና ካገኙት ምንጭ ሁሉ ለመጠጣት ዝግጁ የሆኑትን ይመርጣቸዋል፡፡ «እነሆ ክርስቶስ እዚህ ነው» ወይም «እነሆ እዚያ ነው» የሚሉ ድምፆች ይሰማሉ፤ ነገር ግን እነዚህን ድምፆች ማመን የለብንም፡፡ የእውነተኛ እረኛን ድምጽ ለማወቅ የማያሳስት ማስረጃ አለን፣ እሱ እንድንከተለው እየጠራን ነው፡፡ እንዲህ ይላል፡- «እኔ የአባቴን ትዕዛዛት ጠብቄያለሁ፡፡» በጎቹን የሚመራው ራስን ዝቅ በማድረግ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በመታዘዝ መንገድ ነው፣ ነገር ግን ሕጉን እንዲተላለፉ በፍጹም አያደፋፍርም፡፡ {2SM 50.2}Amh2SM 50.2

    «የእንግዳ ድምፅ” የእግዚአብሔርን ቅዱስ፣ ቅን እና መልካም የሆነውን ሕግ ከማያከብርና ከማይታዘዝ የሚወጣ ድምጽ ነው፡፡ ብዙዎች ይህን ታላቅ የጽድቅ መስፈርት ሳያከብሩ ቅድስና እንዳላቸው ያስመስላሉ፣ በሽተኞችን በመፈወስ በሚፈጽሙአቸው ተአምራቶችም ይኩራራሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ፈውሶች የተፈጸሙት በማን ኃይል ነው? የማንኛውም አካል ዓይኖች ሕግን ስለመተላለፋቸው ተገልጠዋልን? እንደ ትሁትና ታዛዥ ልጆች የእግዚአብሔርን መስፈርቶች ሁሉ ለመታዘዝ ዝግጁ ሆነው አቋም ይወስዳሉን? የእግዚአብሔር ልጆች ነን ስለሚሉ ሰዎች ዮሐንስ እንዲህ በማለት ይመሰክራል፡ «አውቀዋለሁ የሚልና ትዕዛዛቱን የማይጠብቅ ውሸተኛ ነው፣ በእርሱ ውስጥ እውነት የለም” (1ዮሐ. 2፡ 4)፡፡ {2SM 50.3}Amh2SM 50.3

    ማንም መታለል የለበትም፡፡ የእግዚአብሔር ሕግ እንደ እርሱ ዙፋን ቅዱስ ስለሆነ ወደ ዓለም የሚመጣ እያንዳንዱ ሰው በእሱ ሕግ ይፈረዳል፡፡ ባሕርይን ለመፈተን ሌላ መስፈርት የለም፡፡ «እንደዚህ ቃል የማይናገሩ ከሆነ፣ በውስጣቸው ብርሃን ስለሌለ ነው፡፡» አሁን፣ የሰዎች ጉዳይ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይወሰን ወይስ የሰው ማስመሰል ዋጋ ይሰጠው? ክርስቶስ «ከፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ» ይላል፡፡ በእነርሱ አማካይነት ፈውስ የተደረገባቸው ሰዎች ከእነዚህ መገለጦች የተነሳ የእግዚአብሔርን ሕግ ችላ ስለማለታቸው ይህን እንደ ምክንያት ለማቅረብ ቢያዘነብሉና ባለመታዘዛቸው ቢቀጥሉ፣ እስከ ፈለጉት ድረስ ኃይል ቢኖራቸውም፣ ታላቁ የእግዚአብሔር ኃይል እንዳላቸው አያሳይም፡፡ ከዚህ በተቃራኒ የታላቁ አታላይ ተአምራት የመሥራት ኃይል ነው፡፡ እሱ የግብረገብ ሕግ ተላላፊ ስለሆነ ሰዎች ስለ እሱ እውነተኛ ባሕርይ እንዳያውቁ ለማሳወር መጠቀም የሚችለውን እያንዳንዱን ዘዴ ይጠቀማል፡፡ በመጨረሻ ዘመን በምልክቶችና በውሸት ተአምራቶች እንደሚሰራ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶናል፡፡ የጨለማ ሳይሆን የብርሃን መልአክ እንደሆነ ለማሳየት ማስረጃ እንዲሆንለት እስከ ምህረት በር መዘጋት ድረስ እነዚህን ተአምራቶች መስራቱን ይቀጥላል፡፡ {2SM 50.4}Amh2SM 50.4

    ወንድሞች ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ሕግ መተላለፍን ከሚፈቅድ የማስመሰል ቅድስና ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡ የእግዚአብሔርን ሕግ በእግራቸው የሚረግጡ ሊቀደሱ አይችሉም፣ ራሳቸው በቀየሱት መስፈርት ራሳቸውን ይመዝናሉ፡፡ --The Review and Herald, Nov. 17, 1885. {2SM 51.1}Amh2SM 51.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents