Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ 9—የስህተት ትምህርት ምልክቶች

    ከሚስተር ጋርማየር ጋር የተደረጉ ተጨማሪ ግንኙነቶች

    በነሐሴ 23 ሰንበት ከሰዓት በኋላ ቤትህን ከጎበኘሁ ጀምሮ ለአንተ እንድነግርህ የሆኑ ነገሮች በአእምሮዬ ውስጥ አርፈዋል፡፡ የኣና ራዕዮች ከእግዚአብሔር አይደሉም ለማለት ምንም ጥርጣሬ የለኝም፡፡ የቤተሰብ አባሎችህ የነበሩአቸው ህልሞች የሰይጣን ማታለያ ናቸው፡፡ . . . {2SM 80.1}Amh2SM 80.1

    ሰይጣን አንተንና ሌሎች ሰዎችን ወደ ወጥመዱ እንድትገቡ ሊመራችሁ ፍሬያማ በሆነ አስተሳሰብህ ላይ መስራት እንደሚችል አየ፡፡ ያንን ስለ ጊዜ የሚናገረውን መልእክት እግዚአብሔር ሰጥቶሃልን? አልሰጠህም፣ እንደዚህ ያለ መልእክት ከእውነተኛ የብርሃን ምንጭ አይመጣም፡፡… ሀሰተኛ ነቢይ እንደሆንክና የኣና ራዕዮችም የሀሰት ተግባራት እንደሆኑ ጊዜ አረጋግጧል፡፡ እግዚአብሔር በፍጹም በዚህ መንገድ አይሰራም፡፡ {2SM 80.2}Amh2SM 80.2

    ሰይጣን ሌሎች ጠንከር ያሉ ማታለያዎችን አዘጋጅቶላችኋል፡፡ ከኣና ራዕይ ጋር በተገናኘ ሁኔታ ከሰማይ በወረደ ጊዜ ከክብሩ የተነሳ ምድርን ካበራው ብርቱ መልአክ ጋር የሚመሳሰል የምትሰራው ሥራ እንዳለህ እስከ አሁን ካልተናገርክ ወደፊት እንደሚኖርህ ትናገራለህ፡፡ አስረውህ ያሉትን የእግር ብረቶች በጌታ ስም ካልሰበርካቸው በስተቀር አእምሮህ በእሱ አስተያየቶች ሊነካ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ እንደሆነ ስለሚያይ አንተን ለማጥፋት አንተኑ ይጠቀማል፡፡ . . . {2SM 80.3}Amh2SM 80.3

    ብዙ ጊዜ፣ በንግግራችን ወቅት፣ እጅግ በጣም ኮስተር ብለህ «ኦ ሀሳበ-ጽኑነት፣ አንተ ጌጥ ነህ!” የሚለውን አረፍተ ነገር ደጋግመህ ነበር፡፡ ከፍ ባለ ኃይል ያንኑ እደግምልሃለሁ፡፡ የኣና ራዕዮች የአውሬው ምስል የሚሰራው የምህረት ደጅ ከተዘጋ በኋላ እንደሆነ ይገልጻሉ ትላለህ፡፡ ይህ እንዲህ አይደለም፡፡ ምስክርነቶችን እንደምታምን ትናገራለህ፤ በዚህ ነጥብ ላይ እነሱ ያስተካክሉህ፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝብ ዘላለማዊ መዳረሻ የሚወሰንበት ታላቁ መፈተኛ ስለሚሆን የአውሬው ምስል የሚሰራው የምህረት ደጅ ከመዘጋቱ በፊት እንደሆነ ጌታ በግልጽ አሳይቶኛል፡፡ {2SM 80.4}Amh2SM 80.4

    የያዝከው አቋም ስርዓት የሌላቸው ነገሮች ክምችት ስለሆነ የሚታለሉት እጅግ ጥቂቶች ናቸው፡፡. . . {2SM 81.1}Amh2SM 81.1

    በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተሰጠውን የአመጸኛ ነቢይ ታሪክ ወስደህ ለሲስተር ኋይት ተጠቅመሃል፡፡ እሷ በትክክል ታማኝ ነች፣ ነገር ግን የተታለለች ነቢይ ነች ትላለህ፡፡ ከዚህ የተነሳ የእግዚአብሔር መንፈስ ምስክርነቶች በአንተ ላይ ውጤት አላመጡም፡፡ ሲስተር ኋይት አመጸኛ እንደሆነች ጌታ ለአንተ ወይም ለሴት ልጅህ፣ ለሚስትህ ወይም ለልጆችህ ገልጦላቸዋልን? ከእግዚአብሔር በተቃራኒ ሄዳ ከሆነ በምን ላይ ከእግዚአብሔር በተቃራኒ እንደሄደች ታሳያለህን? አንተ ለምስክርነቶቼ የተሳሳተ ትርጉም ስለምትሰጥ፣ ከትክክለኛ ትርጉሙ ስለምትነጥል እና ልትል ለምትፈልገው ለማንኛውም ነገር ኃይል እንደሚሰጥ ስታስብ በእኔ ስም ስለምታስተጋባ የእኔ ተግባር ያለኝን አቋም የሚገልጹ አረፍተ ነገሮችን ግልጽ ማድረግ ነው፡፡ ነገር ግን ምስክርነቶቹ ከአንተ ንድፈ ሀሳቦች ጋር የማይጣጣሙ ከሆነ ያኔ ሀሰተኛ ነቢይ እሆንና ትተወኛለህ! ከእውነት የሚሸሽባቸው ብዙ መንገዶች አሉ፡፡ {2SM 81.2}Amh2SM 81.2

    ከኤልደር [ዩሪያ] ስሚዝ እና ከሌሎች ወንድሞቻችን ጋር የተለየ መራርነት ያለህ ትመስላለህ፡፡ እነዚህን ስሜቶች በቤተሰብህ ውስጥ በመናገር እነርሱንም በእርሾህ አበላሽተሃል፡፡ ኤልደር ስሚዝ ስለተሳሳተ እግዚአብሔር ሊመክረውና የተግሳጽ ቃላት ሊሰጠው ገጣሚ ሆኖ አግኝቶታል፤ ነገር ግን ይህ እግዚአብሔር እንደተወው ማስረጃ ነውን? አይደለም፡፡ «የምወደውን ሁሉ እገስጻለሁ እቀጣውማለሁ፡- እንግዲህ ቅና ንስሃም ግባ» (ራዕይ 3፡ 19)፡፡ እግዚአብሔር በሕዝቡ ውስጥ ያለውን ስህተት ይገስጻል፣ ነገር ግን ይህ እንዳልተቀበላቸው ማስረጃ ነውን? አይደለም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስህተቶች አሉ፣ እነዚህን ስህተቶች ሁል ጊዜ በምስክርነቶች አማካይነት ሳይሆን እሱ በሾማቸው ወኪሎቹ አማካይነት ይጠቁማል፡፡ እኛ እነዚህን ተግሳጾች ይዘን በማጉላት እግዚአብሔር ለእርነሱ ብርሃኑንና ፍቅሩን አያጋራም ማለት እንችላለንን? አንችልም፡፡ እግዚአብሔር ለእነርሱ ሊያደርግ እየሞከረ ያለው ሥራ ራሱ እንደሚወዳቸውና ከአደጋ መንገዶች ሊመልሳቸው እንደሚፈልግ ያሳያል፡፡ {2SM 81.3}Amh2SM 81.3

    አንተን በተመለከተ እግዚአብሔር ተናግሯል፡፡ አንተ ከሰማይ የመጣ ብርሃን ነው የምትለውን ነገር እሱ ጨለማ ነው ብሎታል፣ ከዚህ ስህተት የተወለዱ ራዕዮችን ማታለያ ብሎ ይጠራቸዋል፡፡ ይህን ምስክርነት ታምናለህን? እግዚአብሔር በሲስተር ኋይት አማካይነት የተናገረውን ነገር ታዳምጣለህን? ወይስ የጌታን ቃል ከኋላህ ትጥላለህ? በአንዳንድ ነገሮች ላይ ለተሳሳቱ ወንድሞችህ ተግሳጽ የሚሆኑ ምስክርነቶች እንዳሉህ አድርገህ ይህን ምስክርነት በቀጥታና በማጉላት ትጠቅሳለህን? «ኦ ሀሳበ-ጽኑነት፣ አንተ ጌጥ ነህ!” --Letter 11, 1890. {2SM 82.1}Amh2SM 82.1