Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከነገሥታት ንጉሥ የተሰጠ ተግባር

    እግዚአብሔር ለታላቅና ለከበረ ሥራ መርጦሃል፡፡ ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር የሆነውን የእርሱን ክብር ብቻ በመመልከት ይህን ቅዱስ ሥራ መስራት እንድትችል እርሱ ሊያርምህ፣ ሊፈትንህ፣ ሊያጠራህና ሊያከብርህ ሲፈልግ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ሰውን መርጦ ከራሱ ጋር ወደ ቀረበ ግንኙነት ማምጣትና እና ለእርሱ መፈጸም ያለበትን ተልእኮ፣ መስራት ያለበትን ሥራ መስጠት እንዴት ያለ ሀሳብ ነው፡፡ ደካማ የሆነ ሰው ብርቱ፣ ፈሪ የነበረ ሰው ደፋር፣ ወላዋይ የነበረ ሰው ጽኑና ፈጣን ውሳኔ የሚወስን ሰው እንዲሆን ይደረጋል፡፡ ምን? ሰው ከነገሥታት ንጉሥ ማከናወን ያለበትን ተግባር እስከሚቀበል ድረስ ብዙ የሚያስከትለው ውጤት አለው ማለት ነው? ዓለማዊ ፍላጎት ከቅዱስ መታመን፣ ከቅዱስ ተግባር ስሜትን መሳብ ይችላልን? {2SM 167.2}Amh2SM 167.2

    የሰማይ ንጉስ ወደ እኛ ዓለም የመጣው ለሰው ንጹህና ነቁጣ የለሽ የሆነ ሕይወት ምሳሌ ሊሰጥ እና እየጠፋ ያለውን ከማዳን የሚገኘውን ደስታ ለማየት ራሱን መስዋዕት ለማድረግ ነበር፡፡ ክርስቶስን የሚከተል ሁሉ ከእርሱ ጋር ነፍሳትን የማዳን መለኮታዊ ሥራ በመጋራት ከእርሱ ጋር አብሮ ሰራተኛ ነው፡፡ ከዓለም ጋር ሕብረት ከፈጠርክ የተሻለ ታዋቂነትን የሚያመጣልህ ነገር መኖሩን በመመልከት ከዚህ ተግባር ነጻ የመሆን ሀሳብ ካለህ ለዚህ ምክንያቱ ለእግዚአብሔር ምንም ነገር ቢሆን መስራት እንዴት ትልቅና የከበረ እንደሆነ ስለምትረሳ፣ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አብሮ ሰራተኛ መሆን፣ ለዓለም ብርሃን ተሸካሚ መሆን፣ ብርሃንንና ፍቅርን በሌሎች ሰዎች መንገድ ላይ ማሳረፍ እንዴት ከፍ ያለ ሥልጣን እንደሆነ ስለምትረሳ ነው፡፡{2SM 167.3}Amh2SM 167.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents