Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ኢየሱስ «ከእኔ ተማሩ” ይላል

    ልጆቻቸውን በባሕር ላጡ ወላጆች የተሰጡ ቃላት

    ስለ እናንተ ብዙ ጊዜ አስብ ነበር፡፡….Amh2SM 260.3

    ቅዱሳን መጻሕፍት የሚሰጡአቸው ማጽናኛዎች በጣም ትልቅ ናቸው፤ መከራና ሀዘን ለደረሰባቸው፣ ለታመሙና ለሚሰቃዩ ሰዎች በማጽናኛ የተሞሉ ናቸው፡፡ ኢየሱስ ለእናንተ፣ ለአባትና እናት ዲ፣ «በእኔ ተደገፉ፣ በደንብ ተደገፉ፡፡ እኔ እሸከማችኋለሁ፡፡ ክንዴ በፍጹም አይጥላችሁም፡፡ ሸካራና ከባድ በሆኑ ቦታዎች ሁሉ ልደግፋችሁ ብርቱ ነኝ፡፡ በእኔ ብቻ ከታመናችሁ ያለ አንዳች ችግር ትመራላችሁ አጥብቄም እይዛችኋለሁ” ይላል፡፡Amh2SM 260.4

    ኦ፣ ክቡር መጽሐፍ ቅዱስ፣ በውስጡ ያሉ እውነቶች በመቅኔ እና በስብ የተሞሉ ናቸው፡፡ ልናነበውና በተስፋዎቹ ብርሃን ልንደሰት እንችላለን፡፡ ዘላለማዊ የሆነው እግዚአብሔር በቸርነት የተሞሉ ንግግሮች ናቸው፡፡ የእርሱ ድምጽ ከቃሉ ውስጥ እየተናገረን ነው፡፡ ጥሩ ድፍረት እንዳገኛችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ Amh2SM 260.5

    ይህን የመጣባችሁን መከራ ለምን እንደመጣባችሁ ማስረዳት አትችሉም ይሆናል፡፡ ባሕር በውስጡ ያለውን ሙታን እስከሚሰጥ ድረስ እያንዳንዱ ነገር ሊዘለቅ በማይችል ምስጢርነት ውስጥ ሊቆይ ይችላል፡፡ ልጆቻችሁ የእግዚአብሔር ንብረት ስለሆኑ እና የራሱ ለሆኑት የሚያደርገውን ስለሚያደርግላቸው በሀዘን አንገታችሁን አትድፋ፡፡ የእርሱ ፍቅር ከእኛ ፍቅር እንደሚበልጥና ኢየሱስ ስለወደዳቸው እነርሱን ለማዳን ሕይወቱን አሳልፎ እንደሰጠ እናውቃለን፤ ስለዚህ ይረፉ፣ የእናንተም ልብ በጽናት እያንዳንዱን የነፍስ ረሃብ የሚያጠግበውን፣ እያንዳንዱን ፍላጎት የሚሞላውን ኢየሱስን ይከተል፡፡… Amh2SM 260.6

    ያላችሁበት ሁኔታ ምንም ቢሆን፣ እግዚአብሔር የሚመራችሁ መንገድ ምንም ያህል ጨለማ ያለበትና ምስጢራዊ ቢሆንም፣ መንገዱ በጥልቅ ውኃዎች ውስጥ እንኳን ቢሆን፣ ፈተናዎችና ሀዘኖች በተደጋጋሚ በመምጣት ቢያሰቃዩም፣ “ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን” (ሮሜ 8፡ 28) የሚለው ማረጋገጫ አሁንም ይመጣል፡፡ “ያመንሁትን አውቃለሁና፣ የሰጠሁትንም አደራ እስከዚያ ቀን ድረስ ሊጠብቅ እንደሚችል ተረድቻለሁ” (2ኛ ጢሞ. 1፡ 12)፡፡-- Letter 32, 1893.Amh2SM 261.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents