Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    «አትመኑአቸው»

    ለአንተ ከጌታ መልእክት አለኝ፡፡ ወንድም አር እግዚአብሔር እንዲሰራ በሚፈልገው ሥራ ላይ አልተሰማራም፡፡ እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰው ሥራውን ሰጥቶታል፣ ወንድም አር እግዚአብሔር ያልሰጠውን ሥራ ለመስራት ከመስመር እየወጣ ነው፡፡ አሁን እያካሄደ ያለውን ሥራ ውጤት ማየት አይችልም፡፡ አና ፊሊፕስ እየተጎዳች ነው ያለችው፣ የእግዚአብሔርን ፈተና ማለፍ የማይችል ሥራ እንድትሰራ እየተመራች፣ እየተበረታተች ነው ያለችው፡፡ {2SM 88.3}Amh2SM 88.3

    አና ጋርማየርም ደግሞ ተጎድታ ነበር፡፡ እናቷና አባቷ የሞኝነት ሕልሞቿን የእግዚአብሔር ራዕዮች እንደሆኑ እንድታምን አድርገዋታል፡፡ አባቷ ለእግዚአብሔር እንደተመረጠች አድርጎ ተናገራት፤ ፈጠራዎቿና ሕልሞቿ ሁሉ እንደ አና ራዕዮች ተደርገው ተጽፈው ነበር፡፡ የቀረቡላት ስዕሎችና ምልክቶች ነበሩ፣ እነዚህ ነገሮች ለአባቷና ለእናቷ ተግሳጽ ነበራቸው፡፡ ማሾፍ ካለበት ተግሳጽ በኋላ እግዚአብሔር ስለሚያደርግላቸው አስደናቂ ነገሮች እጅግ ሽንገላ ያለባቸው ገለጻዎች ተከተሉ፡፡ እነዚህ ነገሮች ውሸትና ማታለያ እንደሆኑ ተጠቁሜያለሁ፡፡ እጅግ ትንሽ ወደሆኑና ወደማይረቡ ነገሮች ደረጃ ወረዱ፣ ርካሽ ነገሮችን አስፈላጊ ከሆኑ ጉዳዮች ጋር ቀላቀሉ፡፡ የሀሳብ ፈጠራ እጅግ አድጎ ነበር፣ ቅዱሱን ከተራው ጋር መቀላቀል ነበር፡፡ የእግዚአብሔር እውነት ተንቋሽሾ ነበር፣ ነገር ግን አንዳንዶች እነዚህን የማስመሰል ራዕዮችን በመቀበል ትምህርታቸውን ቀጥለው ነበር፡፡ በግልጽ በእነርሱ የተመራ ትንሽ ቡድን ተመስርቶ ነበር፣ ራዕዮቹም ከሲስተር ኋይት ራዕዮች የበለጠ መንፈሳዊ እንደነበሩ ተነገረ፡፡... {2SM 89.1}Amh2SM 89.1