Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 3

    ሰብአዊ ቤተሰቦች ከራሳቸው መጥፎ ልምዶች የተነሳ በራሳቸው ላይ የተለያዩ ዓይነት በሽታዎችን አምጥተዋል፡፡ እንዴት ጤናማ ሆነው እንደሚኖሩ አልተማሩም፣ አካላዊ የጤና ሕጎችን መተላለፋቸው አሳዛኝ ሁኔታዎችን ፈጥሯል፡፡ ሰዎች ለመሰቃየታቸው እውነተኛው መንስኤ የራሳቸው የተሳሳተ እርምጃ እንደሆነ አይቀበሉም፡፡ በአመጋገባቸው መሻታቸውን ባለመግዛት የምግብ ፍላጎታቸውን አምላክ አድርገዋል፡፡ ጤናን እና ሕይወትን በተመለከተ በልምዶቻቸው ሁሉ ግድየለሽነትን አሳይተዋል፡፡ ከዚህ የተነሳ በሽታ ሲመጠባቸው የራሳቸው የተሳሳተ ድርጊት ትክክለኛውን ውጤት አምጥቶባቸው ሳለ እነርሱ ግን በሽታውን ያመጣው እግዚአብሔር ነው ብለው ራሳቸውን ያሳምናሉ፡፡ ስቃይ ሲደርስባቸው ሐኪም ይጠሩና ያድነናል በማለት አካላቸውን በእጆቹ አሳልፈው ይሰጣሉ፡፡ ሐኪሙ ምንነቱን የማያውቁትን መድሃኒት ያዝላቸዋል፣ እነርሱም በሐኪሙ ላይ ካላቸው ጭፍን መታመን የተነሳ እርሱ ሊሰጣቸው የመረጠላቸውን ማንኛውንም ነገር ይውጣሉ፡፡ የሰውነት ክፍሎች የደረሰባቸውን በደል ለመቀየር ተፈጥሮ ጉዳት የማያስከትል ጥረት እያደረገች ሳለ፣ ብዙ ጊዜ የተፈጥሮን ጥረት በእግር ብረት የሚያስሩ ኃይለኛ መርዞች ይታዘዛሉ፤ ከዚህ የተነሳ በሽተኛው ሕይወትን የሚሰናበትበት ሁኔታ ይፋጠናል፡፡ {2SM 441.1}Amh2SM 441.1

    መጠነኛ የሆነ የጤና ችግር ያጋጠማት እናት፣ ለአጭር ጊዜ ምግብ ባለመመገብ እና ስራን ባለመሥራት ጸጥታና እረፍት ብታገኝ ኖሮ ጤንነቷ ሊመለስላት ሲችል ይህን በማድረግ ፈንታ ወደ ሐኪም ትላካለች፡፡ በማስተዋል ጥቂት ቀለል ያሉ መመሪያዎችን እና የአመጋገብ ገደቦችን በመስጠት ወደ ትክክለኛው መስመር መመለስ ያለበት ሐኪም ደግሞ ይህን ለማድረግ እውቀት የሌለው ወይም ገንዘብ ለማግኘት ጉጉት ያለበት ሊሆን ይችላል፡፡ {2SM 441.2}Amh2SM 441.2

    ጉዳዩን አስከፊ ያደርገውና እሱ ራሱ ቢታመም ኖሮ ለመውሰድ የማይደፍራቸውን መርዞች ያዛል፡፡ የበሽተኛው ጤንነት ከመጀመሪያው እየከፋ ስለሚሄድ ተፈጥሮ ራሷን ለማዳን በምታደርጋቸው ጥረቶች ተሸንፋ ጦርነቱን በማቆሟ እናት እስክትሞት ድረስ መርዘኛ መድኃኒቶች ዝም ብለው ይታዘዛሉ፡፡ ወደ ሞት ተጎትታለች፡፡ የአካል ክፍሎቿ መዳን እስከማይችሉ ድረስ ተመርዘዋል፡፡ ተገድላለች፡፡ ጠቃሚ በሆነችበትና ልጆቿ የእሷን እንክብካቤ እጅግ በሚሹበት ሰዓት አምላክ እሷን በመውሰድ ባደረገው አስደናቂ ሥራ ጎረቤቶችና ዘመዶች ይደነቃሉ፡፡ የሰብዓዊ ዋይታን ክብደት በእርሱ ላይ መልሰው በሚጥሉበት ጊዜ መልካምና ጠቢብ የሆነውን ሰማያዊ አባታችንን እየወነጀሉት ነው፡፡ ሰማይ ያቺ እናት እንድትኖር ይመኝ ነበር፣ የእሷ ያለ ጊዜ መሞት እግዚአብሔርን ያዋርዳል፡፡ እናቲቱ እንድትታመም ያደረገው መጥፎ ልምዶቿና ለአካላዊ ሕጎች ትኩረት አለመስጠቷ ነው፡፡ ሐኪሙ ያዘዛቸው ዘመናዊ መርዞች ወደ ሰውነቷ በመግባት የመኖር ዘመኗን ወደ ፍጻሜ በማምጣት ረዳት የለሽ የሆኑ፣ የተበደሉ፣ እናት አልቦ መንጋን ትቷል፡፡ {2SM 441.3}Amh2SM 441.3

    ከላይ የተጠቀሰው ሀሳብ ሁልጊዜ ሐኪም የሚያዘውን መድሃኒት ተከትሎ የሚመጣ ውጤት አይደለም፡፡ እነዚህን መርዝ መድኃኒቶች የሚወስዱ ሕመምተኞች የሚሻላቸው ጊዜ አለ፡፡ አንዳንዶች እረፍት ካገኙ ከሰውነት ውስጥ መርዝን ለማስወጣት ተፈጥሮ የምትደገፍበት በቂ የሆነ የሕይወት ኃይል ስላላት ይሻላቸዋል፡፡ ነገር ግን የመድኃኒቶቹ ተግባር ተፈጥሮ ራሷን ለማዳን የምታደርገውን ጥረት ማሰናከል ብቻ ስለሆነ ለመድሃኒቶቹ ምንም ዋጋ ሊሰጥ አይገባም፡፡ ሁሉም ዋጋ ሊሰጥ የሚገባው ጤንነትን መመለስ ለሚችሉ የተፈጥሮ ኃይሎች ነው፡፡ {2SM 442.1}Amh2SM 442.1

    ምንም እንኳን በሽተኛው ቢድንም ተፈጥሮ መርዙን ለመቋቋም የሚያስችል ተግባር ለማነሳሳት ያስፈለጋት ኃይለኛ ጥረት አካልን ከመጉዳቱ የተነሳ የሕመምተኛውን ሕይወት አሳጥሯል፡፡ መድኃኒቶቹን እየወሰዱ ሳሉ ከመድኃኒቱ ተጽዕኖ የተነሳ የማይሞቱ፣ ነገር ግን የማይጠቅሙ ሰባራዎች፣ ተስፋቢሶች፣ ሀዘንተኞች፣ በአሰቃቂ ሁኔታ የሚሰቃዩ እና ለራሳቸውና ለሕብረተሰቡ ሸክም የሆኑ ብዙዎች አሉ፡፡ {2SM 442.2}Amh2SM 442.2

    እነዚህን መድኃኒቶች የሚወስዱት ብቻ የሚሰቃዩ ቢሆን ኖሮ ክፋቱ ይህን ያህል ትልቅ ባልሆነም ነበር፡፡ ወላጆች መድኃኒት-መርዞችን በመዋጣቸው ኃጢአት የሚሰሩት በራሳቸው ላይ ብቻ ሳይሆን በልጆቻቸው ላይም ነው፡፡ ከመርዘኛ መድሃኒቶች የተነሳ የተበላሸ ደም፣ በመላ አካል ውስጥ የተሰራጨው መርዝ፣ የተሰበራ አቋም፣ እና የተለያዩ ዓይነት ከመድኃኒት የተነሳ የሚመጡ በሽታዎች ወደ ልጆቻቸው በመተላለፍ መጥፎ ውርስ ይሆናል፤ ይህ ለሰብዓዊ ዘር ብልሽት ሌላኛው ታላቅ መንስኤ ነው፡፡ {2SM 442.3}Amh2SM 442.3

    ሐኪሞች መርዝ የሆኑ መድኃኒቶቻቸውን በማዘዝ የሰው ዘር በአካል፣ በአእምሮና በግብረገብ እንዲያሽቆለቁል ለማድረግ ብዙ አስተዋጽዖ አድርገዋል፡፡ በምትሄዱበት ሁሉ በአብዛኛው መድሃኒቶቹ እንዲታዘዙ መንስኤ ለሆነው ሕመም ፈውስ እንዲሆኑ በሐኪም እጅ የታዘዙ መርዘኛ መድኃኒቶች እንደሆኑ ማወቅ የሚያስችሉ አካለ-ጎዳሎነትን፣ በሽታንና ጅልነትን ታያላችሁ፡፡ ፈዋሽ መድኃኒት ተብሎ የሚጠራው ነገር በበሽተኛው ላይ ከባድ የስቃይ ልምምድ በማምጣት መድኃኒቱ እንዲፈውስ ተብሎ ከተወሰደለት በሽታ ይልቅ እጅግ የከፋ መሆኑን በሚያስፈራ ሁኔታ አረጋግጧል፡፡ የተለመዱ ችሎታዎች ያሉአቸው ሁሉ አካላቸው የሚፈልገውን ነገር ማወቅ አለባቸው፡፡ የጤና ፍልስፍና ለልጆቻችን ከሚያስፈልጉ ጠቃሚ ትምህርቶች አንዱ መሆን አለበት፡፡ የሰው አካል ክፍሎችን ማስተዋል በጣም አስፈላጊ ነው፤ ከዚያ በኋላ ብልህ የሆኑ ወንዶችና ሴቶች የራሳቸው ሀኪሞች መሆን ይችላሉ፡፡ ሰዎች የበሽታዎችን መንስኤና ውጤቱን ቢያገናዝቡና በለያቸው የሚበራውን ብርሃን ቢከተሉ ኖሮ ጤንነትን የሚያረጋግጠውን መንገድ ይከተሉ ነበር፣ የሞት መጠንም እጅግ ይቀንስ ነበር፡፡ ነገር ግን ሰዎች ይቅርታ ሊደረግለት በማይቻል ድንቁርና ውስጥ ለመቆየት እጅግ ፈቃደኛ ስለሆኑ በጉዳዩ ላይ ራሳቸው ልዩ ሀላፊነት ከመውሰድ ይልቅ ለአካላቸው ጤንነት በዶክተሮች ይታመናሉ፡፡ {2SM 442.4}Amh2SM 442.4

    የዚህ ታላቅ ርዕስ በርካታ መግለጫዎች በፊቴ ቀርበውልኝ ነበር፡፡ የቀረበልኝ የመጀመሪያው መግለጫ አባትና ሴት ልጁ ብቻ የነበሩበት ቤተሰብ ነበር፡፡ ሴት ልጁ ስለታመመችበት አባትየው ተረብሾ ሐኪም ይጠራል፡፡ አባት ሐኪሙን ወደ ታመመችው ልጁ እየመራ ሳለ ከፍተኛ ስጋት ይታይበት ነበር፡፡ ሐኪሙ የታመመችውን ልጅ ከመረመረ በኋላ ያለው ነገር ትንሽ ነበር፡፡ ሁለቱም ከሕመምተኛዋ ክፍል ወጡ፡፡ አባት ለሐኪሙ እናትን፣ ወንድ ልጁንና ሌላኛዋን ሴት ልጁን እንደቀበረና ከቤተሰቡ መካከል የቀረችለት ይህቺ ልጅ ብቻ እንደሆነች ነገረው፡፡ በተሸበረ መንፈስ ሆኖ የልጁ ሁኔታ ተስፋ ቢስ እንደሆነ ያስብ እንደሆን ሐኪሙን ጠየቀው፡፡ {2SM 443.1}Amh2SM 443.1

    ከዚያ በኋላ ሐኪሙ የሞቱት የቤተሰብ አባላት የህመማቸው ባሕርይ ምን እንደሚመስልና ለምን ያህል ጊዜ እንደታመሙ ጠየቀው፡፡ አባትየው ይወዳቸው ከነበራቸው የቤተሰብ አባላት ሕመም ጋር የተገናኙ አሳዛኝ እውነታዎችን እያቃሰተ ነገረው፡፡ «ልጄ በመጀመሪያ ትኩሳት ያዘው፡፡ ሐኪም ጠራሁ፡፡ ሐኪሙ ቶሎ ትኩሳቱን የሚያበርድለትን መድሃኒት አዝለታለሁ አለኝ፡፡ ከባድ መድሃኒት ሰጠው፣ ነገር ግን በውጤቱ አልተደሰተም፡፡ ትኩሳቱ ቀነሰለት፣ ነገር ግን ልጄ በአደገኛ ሁኔታ ታመመ፡፡ ያንኑ መድሃኒት መልሶ ሰጠው፣ ነገር ግን ምንም የተሻለ ለውጥ አላመጣም፡፡ ሐኪሙ ከመጀመሪያው የበለጠ ኃይለኛ መድሃኒት ሰጠው፣ ነገር ግን ምንም አልተሻለውም፡፡ ትኩሳቱ ተወው፣ ነገር ግን ልጄ ማገገም አልቻም፡፡ ወዲያውኑ ስምጥ አለና ሞተ፡፡ {2SM 443.2}Amh2SM 443.2

    «የልጄ መሞት ድንገተኛና ያልተጠበቀ ስለነበር ለሁላችንም ታላቅ ሀዘን ሆነብን፣ በተለይም እናቱ በጣም ተጎዳች፡፡ ታሞ ሳለ ስቃዩን መመልከትና ከህመሙ የተነሳ የነበራት ጭንቀት፣ እና ከድንገተኛ ሞቱ የተነሳ የተፈጠረው ሀዘን ከነርቮቿ መሸከም አቅም በላይ ስለነበር ባለቤቴ ብዙም ሳትቆይ ደከመች፡፡ ዶክተሩ የተከተለው የሕክምና መንገድ አላረካኝም ነበር፡፡ በእሱ ላይ ያለኝ እምነት ስለወረደ ሁለተኛ ጊዜ እሱን ለሕክምና አልጠራሁትም፡፡ በሕመም እየተሰቃየች የነበረችውን ሚስቴን እንዲያክም ሌላ ሐኪም ጠራሁ፡፡ እሷ በጣም ያስፈልጋት የነበረው እረፍት ስለነበር ሕመሟን እንዲያስታግስ፣ ነርቮቿን ጸጥ እንዲያሰኝ እና እረፍት እንዲሰጣት ይህ ሁለተኛው ሐኪም በርከት አድርጎ ኦፒየም የሚባል አደንዛዥ እጽ ሰጣት፡፡ ኦፒየሙ የማሰብ አቅም አሳጣት፡፡ ወዲያው አንቀላፈች፣ ሞት ከመሰለው አእምሮ መሳት ምንም ነገር ሊቀሰቅሳት አልቻለም፡፡ የደም ግፊቷ እና ልቧ ለተወሰነ ጊዜ በኃይል መታና ከዚያ በኋላ ትንፋሹዋ እስኪቆም ድረስ እየደከመ ሄደ፡፡ ከዚህ የተነሳ ዓይኗን ገልጣ ቤተሰቦቿን ሳታይ ሞተች፡፡ ይህ ሁለተኛ ሞት ከምንሸከመው በላይ መሰለን፡፡ ሁላችንም ጥልቅ ሀዘን ደረሰብን፣ ግን እኔ እጅግ ተሰቃየሁ፣ መጽናናትም አልቻልኩም ነበር፡፡ {2SM 443.3}Amh2SM 443.3

    «ሴት ልጄ ቀጥላ ታመመች፡፡ ሀዘን፣ ስጋትና የሚሆነውን መከታተል ነገሮችን የመሸከም አቅሟን ስለጨረሰው ብርታቷ ተለያትና ታማ አልጋ ያዘች፡፡ አሁን በቀጠርኳቸው በሁለቱም ሐኪሞች ላይ እምነት አጥቻለሁ፡፡ የታመሙትን ሰዎች በማከም የተዋጣለት ነው የተባለ ሌላ ሐኪም እንድጠራ ተነገረኝ፡፡ ምንም እንኳን እሱ የሚኖረው ሩቅ ቦታ ቢሆንም የእሱን አገልግሎት ለማግኘት ወሰንኩ፡፡ {2SM 444.1}Amh2SM 444.1

    «ይህ ሶስተኛው ሐኪም የልጄ ሕመም ምን እንደሆነ እንደሚያውቅ ነገረኝ፡፡ ልጅቷ በጣም ደክማለች፣ የነርቭ ሥርዓቷ ተረብሾአል፤ መቆጣጠር የሚቻል ቢሆንም ትኩሳትም አለባት፣ ነገር ግን አሁን ካለችበት የድካም ሁኔታ ወደ ትክክለኛ ሁኔታ ለመመለስ ጊዜ ይወስዳል አለኝ፡፡ ከአልጋዋ ሊያስነሳት ችሎታ እንዳለው በመተማመን አፉን ሞልቶ ተናገረ፡፡ ትኩሳቱን እንዲያወርድ ኃይለኛ የሆነ መድሃኒት ሰጣት፡፡ ይህ ተከናወነ፡፡ ነገር ግን ትኩሳቱ ሲተዋት ጉዳዩ ከመጀመሪያው የበለጠ አሳሳቢ ባሕርያትን ማሳየት ጀመረና እጅግ ውስብስብ ሆነ፡፡ ምልክቶቹ በተለዋወጡ ቁጥር እነዚያን ምልክቶች ለማጥፋት ሲባል መድሃኒቱም ተቀያየረ፡፡ ከአዲሶቹ መድሃኒቶች ተጽዕኖ የተነሳ ለጊዜው የተነቃቃች መሰለች፣ ይህ ሁኔታ የምትድንልን በማስመሰል በውሸት ተስፋችንን ቢያድሰውም ሁኔታዋ እየከፋ በመሄዱ ተስፋ መቁረጣችንን የበለጠውን መራራ አደረገው፡፡ {2SM 444.2}Amh2SM 444.2

    «ሐኪሙ የነበረው የመጨረሻው አማራጭ ተባይ ማጥፊያ መስጠት ነበር፡፡ ለተወሰነ ጊዜ በሕይወትና በሞት መካከል ያለች መሰለች፡፡ በተከታታይ መንቀጥቀጥ ጀመረች፡፡ እነዚህ ተስፋ የሚያስቆርጡ መንቀጥቀጦች ሲያበቁ የማገናዘብ ችሎታዋ የመዳከሙን አሳዛኝ እውነታ እንድናውቅ ተደረግን፡፡ ምንም እንኳን ትልቅ ስቃይ ውስጥ ብትሆንም ቀስ በቀስ መሻሻል ማሳየት ጀመረች፡፡ ከወሰደቻቸው ኃይለኛ መርዞች የተነሳ እጆቿና እግሮቿ ሽባ ሆነዋል፡፡ ለጥቂት ዓመታት በሚያሳዝን ሁኔታ ረዳተ-ቢስ ሆነ እየተሰቃየች ከኖረች በኋላ በብዙ ሥቃይ ሞተች፡፡” {2SM 444.3}Amh2SM 444.3

    ይህን አሳዛኝ ሁኔታ ከነገረው በኋላ አባት እየተለማመጠ ወደ ሐኪሙ ተመለከተና የቀረችለትን ብቸኛውን ልጁን እንዲያድንለት ተማጸነው፡፡ ሐኪሙ ያዘነና የተሸበረ መሰለ፣ ነገር ግን ምንም መድኃኒት አላዘዘላትም፡፡ በሚቀጥለው ቀን እመጣለሁ ብሎ ለመሄድ ተነሳ፡፡ {2SM 445.1}Amh2SM 445.1

    ከዚያ በኋላ ሌላ ሁኔታ በፊቴ ቀረበልኝ፡፡ እድሜዋ በግልጽ ሰላሳ አመት ገደማ የሆናት ሴት ወዳለችበት አመጣኝ፡፡ ሐኪም በአጠገቧ ቆሞ የነርቭ ሥርዓቷ መረበሹን፣ ደሟ ንጹህ አለመሆኑንና እየተንቀረፈፈ እንደሚንቀሳቀስ እና ጨጓራዋ እንደቀዘቀዛና ሥራውን እንደማይሰራ ዘገባ ያቀርብ ነበር፡፡ ሁኔታዋ ቶሎ እንዲሻሻል የሚያደርግ የሚሰራ መድሃኒት እንደሚሰጥ ተናገረ፡፡ ኑክስ ቮሚካ (Nux Vomica) የሚል ጽሁፍ ካለበት ብልቃጥ ዱቄት ሰጣት፡፡ ይህ መድኃኒት በበሽተኛው ላይ ምን ውጤት እንደሚኖረው ለማየት ተከታተልኩ፡፡ ጥሩ ውጤት የሚያስገኝ መሰለ፡፡ ሁኔታዋ የተሻለ መሰለ፡፡ ሕይወት የዘራች፣ ደስተኛና ንቁ መሰለች፡፡ {2SM 445.2}Amh2SM 445.2

    ትኩረቴ እንደገና ወደ ሌላ ሁኔታ ተሳበ፡፡ ከባድ ትኩሳት ወዳለበት ወደ አንድ የታመመ ወጣት ክፍል እንድገባ ተደረግኩ፡፡ በበሽተኛ አልጋ አጠገብ ካሎሜል (Calomel) የሚል ጽሁፍ ካለበት ብልቀት የተቀነሰ መድሃኒት ይዞ ሐኪም ቆሞ ነበር፡፡ ይህን መርዝነት ያለውን ኬሚካል ሰጠውና ለውጥ የሚታይ መሰለ፣ ነገር ግን ለውጡ መልካም አልነበረም፡፡ {2SM 445.3}Amh2SM 445.3

    ከዚያ በኋላም ሌላ ሁኔታ እንዳይ ተደረግሁ፡፡ ከሕመም የተነሳ ብዙ እየተሰቃየች ያለች ሴት ነበረች፡፡ በበሽተኛዋ አልጋ አጠገብ ሐኪም ቆሞ ኦፒየም የሚል ጽሁፍ ካለበት ብልቃጥ መድሃኒት እየሰጣት ነበር፡፡ ይህ መድሃኒት በመጀመሪያ አእምሮን የሚነካ መሰለ፡፡ እንግዳ በሆነ ሁኔታ ተናገረች፣ ነገር ግን በመጨረሻ ጸጥ አለችና አንቀላፋች፡፡ {2SM 445.4}Amh2SM 445.4

    ከዚያ በኋላ ትኩረቴ ሚስቱንና ሁለት ልጆቹን ወዳጣው አባት ወደ መጀመሪያው ሁኔታ ተሳበ፡፡ ሐኪም በበሽተኛው ክፍል ውስጥ እየተሰቃየች በነበረችው ሴት ልጅ አጠገብ ቆሞ ነበር፡፡ አሁንም መድሃኒት ሳይሰጥ ከክፍሉ ወጣ፡፡ ሐኪሙ በተገኘበት ብቻ እጅግ የተነካ ይመስል የነበረው አባት ትዕግስቱ አልቆበት «ምንም ላለማድረግ አቅደሃል ማለት ነው? የቀረችውን ብቸኛዋን ልጄን እንድትሞት ትተዋታለህ?” ብሎ ጠየቀው፡፡ {2SM 445.5}Amh2SM 445.5

    ሐኪሙ እንዲህ አለ፣… «እጅግ የምትወዳትን የባለቤትህንና የሁለቱን ልጆችህን አሟሟት አሳዛኝ ታሪክ ሰምቻለሁ፣ ከአንተ ከራስህ ከንፈር ሶስቱም በሐኪሞች ጥንቃቄ ሥር ሆነው በእነርሱ የታዘዙ መድሃኒቶችን እየወሰዱ እንደሞቱ መረዳት ችያለሁ፡፡ ውዶችህን መድሃኒት አላዳናቸውም፣ እንደ ሐኪም ደግሞ አንዳቸውም ቢሆኑ መሞት እንደሌለባቸው አምናለሁ፡፡ ተፈጥሮ ያለ አግባብ በተወሰደ መድሃኒት አቅም እንድታጣና በመጨረሻም እንድትሰበር ባይደረግ ኖሮ ያገግሙ ነበር፡፡” ለተረበሸው አባት በእርግጠኝነት እንዲህ አለው፣ «ለልጅህ መድሃኒት መስጠት አልችልም፡፡ ተፈጥሮ በምታደርገው ጥረት እንቅፋቶችን በማስወገድ ብቻ ልረዳ እፈልጋለሁ፣ ከዚያ በኋላ ተፈጥሮ የተንጠፈጠፈውን ኃይሏን እንድትመልስ እተዋለሁ፡፡” አባትየው በቅርበት እንዲከታተል ያዘዛቸውን ጥቂት መመሪያዎች በእጁ ሰጠው፡፡ {2SM 445.6}Amh2SM 445.6

    «ሕመምተኛዋን ከመረበሽ እና ለማስጨነቅ ተሰልቶ ከተዘጋጀ ከማንኛውም ተጽዕኖ ነጻ አድርግ፡፡ የሚጠነቀቁላት ሰዎች ደስተኛና ተስፋ የሚሰጡ ይሁኑ፡፡ ቀለል ያለ ምግብ እና ብዙ ንጹህ ውኃ ትውሰድ፡፡ ቶሎ ቶሎ በንጹህ ውኃ ከታጠበች በኋላ በቀስታ ትታሽ፡፡ ብርሃንና አየር እንደልብ ወደ ክፍሏ እንዲገባ ይደረግ፡፡ ጸጥታ ያለበትና ያልተረበሸ እረፍት ታግኝ፡፡” {2SM 446.1}Amh2SM 446.1

    አባት ትዕዛዙን በቀስታ አነበበና በወረቀቱ ላይ በነበሩት ጥቂት ቀለል ባሉ መመሪያዎች በመደነቅ ይህን የመሰለ ቀላል መንገድ ጥሩ ውጤት ሊያስገኝ ይችላልን? የሚል ጥርጣሬ የገባበት መሰለ፡፡ ሐኪሙ እንዲህ አለው፣ «የሴት ልጅህን ሕይወት በእኔ እጅ አሳልፈህ እስክትሰጥ ድረስ በእኔ ሙያ ላይ በቂ የሆነ መተማመን ነበረህ፡፡ በየቀኑ ልጅህን እጎበኛለሁ፣ ስለ አያያዟም መመርያ እሰጥሃለሁ፡፡ መመሪያዎቼን በመተማመን ተከተላቸው፣ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ባትድን እንኳን ጤንነቷ እጅግ በተሻለ ሁኔታ ላይ ሆኖ መልሼ እንደምሰጥህ እተማመናለሁ፡፡” {2SM 446.3}Amh2SM 446.2

    አባትየው ያዘነ እና ጥርጣሬ ያለበት ይመስል ነበር፣ ነገር ግን ለሐኪሙ ውሳኔ ተገዛ፡፡ ምንም መድሃኒት ካልተሰጣት ልጄ ትሞትብኛለች ብሎ ፈራ፡፡ {2SM 446.4}Amh2SM 446.3

    ሁለተኛው ሁኔታም በፊቴ ቀረበልኝ፡፡ ኑክስ ቮሚካ የተባለው መድሃኒት ካሳደረው ተጽእኖ የተነሳ በሽተኛዋ የተሻላት መሰለች፡፡ ያንገት ልብሷን በዙሪያዋ ጠምጥማ እየበረዳት እንደሆነ እየተናገረች ቁጭ ብላለች፡፡ በክፍሉ ውስጥ ያለው አየር ንጹህ አይደለም፡፡ ሙቆ ሕያውነቱን አጥቷል፡፡ ሕመምተኛዋ በተለየ ሁኔታ ከኋላ በኩል በአንገቷ ላይና ታች በአካርካሪዋ ላይ የሚሰማትን ኃይለኛ ቅዝቃዜ ለመከላከል ሲባል ንጹህ አየር ሊያስገባ የሚችል እያንዳንዱ ስንጥቅ ተሸፍኗል፡፡ በሩ ተከፍቶ ከተተወ ስለሚበርዳት የተደናገጠችና ስቃይ የሚደርስባት ስለምትመስል በሩ እንዲዘጋላት ትማጸናለች፡፡ በበር ወይም በመስኮት የሚገባውን ትንሽ የንፋስ ሽውታን እንኳን መቋቋም አልቻለችም፡፡ አስተዋይ የሆነ ሰው በሀዘኔታ እየተመለከታት እዚያ ለነበሩት እንዲህ አላቸው፣… «ይህ የኑክስ ቮሚካ ሁለተኛው ውጤት ነው፡፡ በተለየ ሁኔታ በነርቮች ላይ ውጤቱ ይሰማና ቀጥሎ መላውን የነርቭ ሥርዓት ይነካል፡፡ ለጊዜው በነርቮች ላይ በግድ እንዲሰሩ የማድረግ ተግባር ይኖረዋል፡፡ ነገር ግን የመድሃኒቱ ጥንካሬ ሲያልቅ የብርድ ስሜትና መድከም ይኖራል፡፡ በሚያነቃቃውና በሚያደምቀው ልክ ሙት የማድረግና የማደንዘዝ ውጤቶች ይከተላሉ፡፡” {2SM 447.1}Amh2SM 447.1

    ሶስተኛው ሁኔታም በድጋሚ በፊቴ ቀረበ፡፡ ካሎሜል የታዘዘለት የወጣቱ ሁኔታ ነበር፡፡ በከፍተኛ ሥቃይ ውስጥ ነበር፡፡ ከንፈሮቹ ጥቁርና ያበጡ ነበሩ፡፡ ድዶቹ ቆስለዋል፡፡ ምላሱ ወፍራምና ያበጠ ነበር፣ ከአፉ ምራቅ በብዛት ይፈስ ነበር፡፡ አስቀድሜ የጠቀስኩት አስተዋይ የሆነ ሰው ይህን ስቃይ እየደረሰበት ያለውን ሕመምተኛ በሀዘኔታ እየተመለከተ እንዲህ አለ፣… «ይህ ከሜርኩሪ የተሰራው ነገር ያስከተለው ውጤት ነው፡፡ ይህ ወጣት በሰውነቱ ውስጥ ጣልቃ የገባውን ይህንን መርዝ-መድሃኒት ከሰውነት ውስጥ ለማስወጣት ሙከራውን መጀመር የሚችልበት የቀራለት በቂ የነርቭ ኃይል አለው፡፡ ብዙዎች ተግባርን ለማነሳሳት የሚችል በቂ የሆኑ የሕይወት ኃይሎች የሉአቸውም፤ ከዚህ የተነሳ ተፈጥሮ ትሸነፍና ጥረቷን ስለምታቆም ተጠቂው ይሞታል፡፡» {2SM 447.3}Amh2SM 447.2

    በድጋሚ በፊቴ የቀረበው አራተኛው ጉዳይ ኦፒየም የተሰጣት ሴት ጉዳይ ነበር፡፡ ከእንቅልፏ የነቃችው እጅግ ደክማ ነበር፡፡ አእምሮዋ ተረብሾ ነበር፡፡ ትዕግሥት የለሽና ግልፍተኛ ነበረች፡፡ እጅግ የምትወዳቸው ጓደኞቿ ስቃይዋን ለማስታገስ ምንም እንዳላደረጉላት በማሰብ በእነርሱ ላይ ስህተት ትፈልግ ነበር፡፡ ተፍጨረጨረችና አእምሮውን እንደሳተ ሰው ቃዠች፡፡ አስቀድሞ የተጠቀሰው ሰው በስቃይ ላይ የነበረችውን ሴት በሀዘኔታ ተመለከታትና እዚያ ለነበሩት እንዲህ አላቸው፣… «ይህ ኦፒየምን ከመውሰድ የሚመጣ ሁለተኛው ውጤት ነው፡፡» ሐኪሟ ተጠራ፡፡ የኦፒየሙን መጠን ከመጀመሪያው ጨምሮ ሰጣትና ከጭንቀት የተነሳ ታደርግ የነበረውን መፍጨርጨር ጸጥ አደረገ፣ ነገር ግን በጣም ለፍላፊና ደስተኛ አደረጋት፡፡ በዙሪያዋ ከነበሩት ሁሉ ጋር ሰላም ሆነች፣ ለምትተዋወቃቸውና ለዘመዶቿ ሁሉ ያላትን ከፍተኛ ፍቅር ገለጸች፡፡ ወዲያውኑ ተጫጫናትና አእምሮዋን ሳተች፡፡ ከላይ የተጠቀሰው ሰው ረጋ ብሎ እንዲህ አለ፣…«አሁን ያለችበት የጤንነት ሁኔታ እየተፍጨረጨረች ትቃዥ ከነበረችበት ሁኔታ ምንም የተሻለ አይደለም፡፡ ሁኔታዋ በእርግጠኝነት የከፋ ነው፡፡ ኦፒየም የተባለ መርዝ-መድሃኒት ከሕመም ጊዜያዊ እረፍት ይሰጣል፣ ነገር ግን ሕመሙን ያመጣውን ነገር አያስወግድም፡፡ ኦፒየም አእምሮን ብቻ በማደንዘዝ ከነርቭ የሚመጡ መልእክቶችን እንዳይቀበል ያደርጋል፡፡ አእምሮ ስሜት የለሽ ሲሆን የመስማት፣ የመቅመስና የማየት ስሜቶችም ጉዳት ይደርስባቸዋል፡፡ የኦፒየም ተጽዕኖ እየቀነሰ ሲሄድና አእምሮ ከሽባነት ሁኔታው ሲነቃ ከአእምሮ ጋር ግንኙነታቸው ተቋርጦ የነበሩት ነርቮች በሰውነት ውስጥ ያለውን ሕመም ከመቼውም በበለጠ ሁኔታ ጮክ ብለው ያስተጋባሉ፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት ሰውነት ተጨማሪ መርዝ ከመውሰዱ የተነሳ ስለተቆጣ ነው፡፡ ለሕመምተኛዋ የሚሰጠው እያንዳንዱ ተጨማሪ መድሃኒት፣ ኦፒየም ይሁን ወይም ሌላ መርዝ፣ ሁኔታውን የበለጠ በማወሳሰብ የበሽተኛውን የመዳን ሁኔታ ተስፋ ቢስ ያደርገዋል፡፡ እንዲያደነዝዙ የሚሰጡ መድሃኒቶች፣ ማናቸውም ቢሆኑ፣ የነርቭ ስርዓትን ያናውጣሉ (ይረብሻሉ)፡፡ በመጀመሪያ ቀላል የነበረው ክፉ፣ ተፈጥሮ ለመከላከል ራሷን አነሳስታ የነበረውና ለራሷ ተትታ ቢሆን ኖሮ ታደርገው የነበረው፣ በሰውነት ውስጥ እየተጨመሩ ካሉት መርዘኛ መድሃኒቶች የተነሳ አሥር እጥፍ የከፋ ሆኗል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ጣልቃ የገባውን መድሃኒት ለመዋጋትና ለማሸነፍ የቀሩት የሕይወት ኃይሎች ከተለመደው በላይ ወደሆነ ተግባር እንዲገቡ የሰውነት ስርዓት ስለሚያስገድዳቸው ነው፡፡ {2SM 447.6}Amh2SM 447.3

    እንደገና በመጀመሪያ ወደተጠቀሰው አባትና ሴት ልጁ ወደነበሩበት የህመምተኛ ክፍል እንድመጣ ተደረግኩ፡፡ ሴት ልጁ በፊቷ ላይ የጤንነት ግለት እየታየባት ፈገግተኛና ደስተኛ ሆና ከአባቷ አጠገብ ተቀምጣ ነበር፡፡ አባት የቀረችለት አንድ ልጁ ከሞት ስለተረፈችለት ፊቱ በልቡ ውስጥ ያለውን ምሥጋና እየተናገረ ደስታ በተቀላቀለበት እርካታ ልጁን እየተመለከታት ነበር፡፡ ሐኪሟ ወደ ክፍሏ ገብቶ ከአባትና ልጅ ጋር ለአጭር ጊዜ ካወራ በኋላ ለመሄድ ተነሳ፡፡ አባቷን እንዲህ አለው፣…Amh2SM 448.1

    «ጤንነቷ የተመለሰላትን ልጅህን እሰጥሃለሁ፡፡ የአካል አቋሟ ሰባራ እንዲሆን ስላልፈለግኩ ምንም መድሃኒት አልሰጠኋትም፡፡ መድሃኒት በፍጹም ይህን አያደርግም ነበር፡፡ መድሃኒት የተፈጥሮን ትክክለኛ ማሽን በማዳከም የሰውነትን አቋም ይሰብራል፣ ይገላልም፤ ነገር ግን በፍጹም አያድንም፡፡ ጤንነትን የመመለስ ኃይል ያላት ተፈጥሮ ብቻ ነች፡፡ የተንጠፈጠፉ ጉልበቶቿን መገንባት እና ውስን ለሆኑ ሕጎቿ ትኩረት ካለመስጠት የተነሳ የተከሰቱ ቁስለቶችን መጠገን የምትችለው እሷ ብቻ ነች፡፡» {2SM 448.2}Amh2SM 448.2

    ከዚያ በኋላ የልጅቷን አባት በእርሱ የህክምና ዓይነት መርካት አለመርካቱን ጠየቀው፡፡ ደስ ያለው አባት ልባዊ ምሥጋናውንና ፍጹም መርካቱን እንዲህ በማለት ገለጸ፣… {2SM 448.3}Amh2SM 448.3

    «በፍጹም የማልረሳውን ትምህርት ተምሬያለሁ፡፡ አስጨናቂ ነበር፣ ነገር ግን በዋጋ የማይተመን ዋጋ ያለው ነው፡፡ ባለቤቴና ልጆቼ መሞት እንዳልነበረባቸው አሁን አምኛለሁ፡፡ ሕይወታቸው በሐኪሞች እጅ ሆኖ በመርዘኛ መድሃኒታቸው ተሰውቷል፡፡” {2SM 448.4}Amh2SM 448.4

    ከዚያ በኋላ ኑክስ ቮሚካ የተሰጣት ሴት፣ ሁለተኛውን ጉዳይ እንዳይ ተደረግሁ፡፡ ከወንበሯ ወደ አልጋዋ በሁለት ሰዎች ተደግፋ እየተወሰደች ነበረች፡፡ እጆቿንና እግሮቿን መጠቀም አቁማለች፡፡ የአከርካሪ ነርቮች በከፊል ሽባ ሆነዋል፣ እግሮችና እጆችም የግለሰቧን ክብደት የመሸከም አቅማቸውን አጥተዋል፡፡ በሚያስጨንቅ ሁኔታ ትስላለች፣ የምትተነፍሳውም በብዙ ችግር ነው፡፡ በአልጋ ላይ እንዳስተኟት ወዲያውኑ ማድመጥና ማየት አቆመች፡፡ ከዚያም ትንሽ ቆይታ ሞተች፡፡ አስቀድሞ ተጠቅሶ የነበረው ሰው ሕይወት የሌለውን አካል በሀዘኔታ ተመለከተና በዚያ ቦታ ለነበሩት እንዲህ አለ፣… {2SM 448.5}Amh2SM 448.5

    «ኑክስ ቮሚካ በሰው የአካል ክፍሎች ላይ ያለውን ቀላልና የተራዘመ ተጽዕኖ ተመልከቱ፡፡ ወደ ሰውነት ሲገባ ይህን መርዘኛ መድኃኒት ለመጋፈጥ የነርቭ ጉልበት ከሚገባው በላይ ተቀስቅሶ ነበር፡፡ ከመጠን ያለፈ መቀስቀስን ከመጠን ያለፈ ድካም ተከትሎ የመጣ ሲሆን የመጨረሻ ውጤቱ የነርቮች መስለል ነበር፡፡ ይህ መድሃኒት በሁሉም ላይ ተመሳሳይ ውጤት የለውም፡፡ አንዳንድ ኃይለኛ የሆነ የሰውነት አቋም ያላቸው ሰዎች አካላቸውን ተገቢ ላልሆነ ሁኔታ ካጋለጡበት ያገግማሉ፡፡ ሌሎች የሕይወት አያያዛቸው እንደ እነርሱ ጠንካራ ያልሆኑት፣ ደካማ የሰውነት አቋም ያላቸው ሰዎች፣ በሰውነታቸው ውስጥ ለአንድ ጊዜ የተወሰነውን ቢወስዱ እንኳን በፍጹም አያገግሙም፣ የዚህን መርዝ አንድ ክፍል ብቻ በመውሰዳቸው ሊሞቱ ይችላሉ፡፡ እነዚህ መርዞች በሚወሰዱበት ወቅት ያለው የሰውነት ሁኔታ የህመምተኛውን ሕይወት ይወስናል፡፡ ኑክስ ቮሚካ አካለ ስንኩል እና ሽባ ሊያደርግ ይችላል፣ ወይም ጤናን ለዘላለም ሊያበላሽ ይችላል፣ ነገር ግን በፍጹም አያድንም፡፡” {2SM 449.1}Amh2SM 449.1

    ሶስተኛው ሁኔታም በድጋሚ በፊቴ ቀረበ፡፡ እርሱም ክላሞል የተሰጠው ወጣት ነበር፡፡ እሱ በጣም የሚያሳዝን ተሰቃይ ነበር፡፡ እጅና እግሮቹ ሽባ ሆነው በከፍተኛ ደረጃ ቅርጸ-ቢስ ሆኖ ነበር፡፡ ያለበት ስቃይ ለመግለጽ ከሚቻለው በላይ እንደሆነና ለእሱ ሕይወት ታላቅ ሸክም እንደሆነች ተናገረ፡፡ በተደጋጋሚ የጠቀስኩት ሰው ይሰቃይ የነበረውን ወጣት በሀዘኔታ ተመለከተና እንዲህ አለ፣… 2SM 449.2}Amh2SM 449.2

    «ይህ ክላሞል ያስከተለው ውጤት ነው፡፡ የክላሞል አንዲት ቅንጣት እንኳን በአካል ውስጥ ከቀረች ታሰቃያለች፡፡ ሕይወት ባለው አካል ውስጥ ብዙ ጊዜ ከመቆየቱ የተነሳ ባሕርዩን ሳያጣ ለዘላለም ይኖራል፡፡ መገጣጠሚያዎችን ያሳብጣል፣ ብዙ ጊዜ በአጥንቶች ውስጥ መበስበስን ይልካል፡፡ ብዙ ጊዜ ራሱን የሚገልጸው በሰውነት ውስጥ ከገባ ከአመታት በኋላ በእብጠቶች፣ በቆላ ቁስሎች እና በካንሰሮች ነው፡፡» {2SM 449.3}Amh2SM 449.3

    አራተኛው ጉዳይም በፊቴ ቀረበ፡፡ ይህች ኦፒየም የተሰጣት ሕመምተኛ ነበረች፡፡ የፊት ገጽታዋ የገረጣ ነበር፣ ዓይኖቿ እረፍት የለሽ እና መስተዋት የሚመስሉ ነበሩ፡፡ እጆቿ የሚጥል በሽታ እንደያዘው ነገር ይንቀጠቀጡ ነበር፣ በዚያ ቦታ የነበሩት ሁሉ በእሷ ላይ እንዳበሩባት በማሰብ ያለመጠን የተጨነቀች ትመስል ነበር፡፡ ሐኪሙ ተጠራና መጣ፣ ነገር ግን በእነዚህ አሰቃቂ እይታዎች ልቡ የተነካ አይመስልም ነበር፡፡ ለታማሚዋ ያሽላታል ያለውን የኦፒየሙን ኃይለኛ የሆነ ክፍል ሰጠ፡፡ ሙሉ በሙሉ እስክትሰክር ድረስ መቃዠቷን አላቆመችም ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ሞት ወደሚመስል መደንዘዝ አለፈች፡፡ የተጠቀሰው ሰው ታማሚዋን ተመለከተና በሀዘኔታ እንዲህ አለ፣… {2SM 449.4}Amh2SM 449.4

    «ቀኖቿ የተቆጠሩ ናቸው፡፡ ተፈጥሮ ያደረገቻቸው ጥረቶች በዚህ መርዝ ተሸንፏል፣ ዋና የሆኑ የአካል ኃይሎች ይህንን መርዘኛ መድሃኒት ከሰውነት ውስጥ ለማስወገድ በተደጋጋሚ ተፈጥሮአዊ ያልሆነ ተግባር ለመፈጸም በመነሳሳታቸው ዝለዋል፡፡ የተፈጥሮ ጥረቶች ሊያበቁ ተቃርበዋል፣ ከዚያ በኋላ የሕመምተኛዋ የስቃይ ሕይወት ያበቃል፡፡» {2SM 450.1}Amh2SM 450.1

    መድሃኒት በመውሰድ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር በሌሎች ምክንያቶች ከሞቱ ሰዎች ቁጥር ድምር ይበልጣል፡፡ በአገር ውስጥ በሺሆች በሚቆጠሩ ሐኪሞች ፋንታ አንድ ሐኪም ብቻ ቢኖር ኖሮ ብዙ ያለ ጊዜ የሚከሰቱ ሞቶች ይከለከሉ ነበር፡፡ ብዛት ያላቸው ሐኪሞችና ብዙ መድሃኒቶች በምድር ኗሪዎች ላይ እርግማን አምጥተዋል፣ ሺሆችንና አሥር ሺሆችን ያለ ጊዜያቸው ወደ መቃብር ወስደዋቸዋል፡፡ {2SM 450.2}Amh2SM 450.2

    ቶሎ ቶሎ መብላትና በብዛት መብላት ምግብን የሚፈጩ የአካል ክፍሎች ላይ ሥራ ያበዛባቸውና እንዲያተኩሱ ያደርጋቸዋል፡፡ ደም ይቆሽሻል፣ ከዚያ በኋላ የተለያዩ ዓይነት በሽታዎች ይከሰታሉ፡፡ ሐኪም ይጠራና ለጊዜው ፋታ የሚሰጥ፣ ነገር ግን በሽታውን የማያድን መድሃኒት ይሰጣል፡፡ የበሽታውን መልክ ሊለውጥ ይችላል፣ ነገር ግን እርግጠኛው ክፋት አሥር እጥፍ ይጨምራል፡፡ ተፈጥሮ ከውስጧ የተጠራቀሙ ቆሻሻዎችን ለማስወገድ የተቻላትን ሁሉ እያደረገች ነበር፣ እንደ ንጹህ አየርና ንጹህ ውኃ ባሉ በተለመዱ የሰማይ በረከቶች በመታገዝ ለራሷ ብትተው ኖሮ ፈጣንና ጉዳት የሌለበት ፈውስ ይፈጸም ነበር፡፡ {2SM 450.3}Amh2SM 450.3

    እነዚህን በሚመስሉ ጉዳዮች ውስጥ ስቃዩ እየደረሰባቸው ያሉ ሰዎች ሌሎች ሊያደርጉላቸው የማይችሉትን ነገር ለራሳቸው ማድረግ ይችላሉ፡፡ ተፈጥሮን በግድ ካሸከሙአት ጭነት ማሳረፍ መጀመር አለባቸው፡፡ መንስኤውን ማስወገድ አለባቸው፡፡ ለአጭር ጊዜ ጹሙና ጨጓራ እንዲያርፍ እድል ስጡ፡፡ ጥንቃቄና ማስተዋል ባለበት ሁኔታ ውኃን በመጠቀም ትኩሳትን ቀንሱ፡፡ እነዚህ ጥረቶች ተፈጥሮ ራሷን ከቆሻሻ ነጻ ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት ያግዛሉ፡፡ ነገር ግን በአጠቃላይ ሲታይ ስቃዩ እየደረሰባቸው ያሉት ሰዎች ትዕግሥት የለሽ ይሆናሉ፡፡ ራስን መካድንና ትንሽ መራብን ሥራ ላይ ለማዋል ፈቃደኞች አይደሉም፡፡ ተፈጥሮ ሥራ የበዛባቸውን የአካል ክፍሎች ጉልበቶች የምትገነባበትን ዘገምተኛ ሂደት ለመጠበቅ ፈቃደኞች አይደሉም፡፡ በአንዴ ፋታ ለማግኘት የወሰኑ ስለሆኑ ሐኪሞች የሚያዙአቸውን ኃይለኛ መድሃኒቶች ይወስዳሉ፡፡ ተፈጥሮ ሥራዋን በደንብ እየሰራች ስለሆነች ማሸነፍ ትችል ነበር፣ ነገር ግን ሥራዋን እየሰራች ሳለች የመርዛማነት ተፈጥሮ ያለው እንግዳ ነገር ወደ ሰውነት ውስጥ ተጨምሯል፡፡ እንዴት ያለ ስህተት ነው! ያለ እግባብ በደል የደረሰባት ተፈጥሮ አሁን አንድ ብቻ ሳይሆን ሁለት የምትዋጋቸው ክፉ ነገሮች አሏት፡፡ ስትሰራ የነበረውን ሥራ ትተውና ወደ ሰውነት ውስጥ አዲስ የገባውን ጣልቃ ገብ ለማስወጣት ቁርጥ ውሳኔ በማድረግ ሥራዋን ትያያዘዋለች፡፡ ተፈጥሮ ባሏት ግብዓቶች ላይ የመጣባት እጥፍ ጥቃት ይሰማትና ትደክማለች፡፡ {2SM 450.4}Amh2SM 450.4

    መድሃኒቶች በሽታን በፍጹም አያድኑም፡፡ መልኩንና ቦታውን ብቻ ይለውጣሉ፡፡ ተፈጥሮ ብቻ ውጤታማ በሆነ ሁኔታ ጤንነትን መመለስ ትችላለች፣ ሥራዋን እንድታከናውን ለራሷ ብትተው ኖሮ እንዴት በተሻለ ሁኔታ ታከናውን ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ እድል ብዙ ጊዜ አይሰጣትም፡፡ ጉዳት የደረሰባት ተፈጥሮ ጫናዋን ተቋቁማ በመጨረሻ ያለባትን እጥፍ ሥራ በከፍተኛ መጠን በመፈጸሟ ህመምተኛው በሕይወት ሲኖር ይህን ያደረገው ሐኪም እንደሆነ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ ነገር ግን መርዙን ከአካል ውስጥ ለማስወጣት በምታደርገው ጥረት ባይሳካላት እና ሕመምተኛው ቢሞት አስደናቂ የሆነ የእግዚአብሔር ፈቃድ ተፈጸመ ይባላል፡፡ ሕመምተኛው ጫና የበዛባትን ተፈጥሮ በወቅቱ ለማሳረፍ እርምጃ ቢወስድ እና በማስተዋል ንጹህ የሆነ ውኃ ቢወስድ ኖሮ በመድሃኒት ምክንያት የሚመጣው ሞት ሙሉ በሙሉ ይቀር ነበር፡፡ ሕመምተኛው አመጋገቡን በጥብቅ መከታተል እንዳለበት ካልተሰማው ውኃን መጠቀም ምንም አይጠቅምም፡፡ {2SM 451.1}Amh2SM 451.1

    ብዙዎች የጤና ሕጎችን በመጣስ ይኖራሉ፤ የአመጋገብ፣ የመጠጥ እና የሥራ ልምዳቸው ከጤንነታቸው ጋር ያለውን ግንኙነት ምንም አያውቁም፡፡ ተፈጥሮ እየተፈጸመባት ካለው በደል የተነሳ እየደረሰባት ያለውን ስቃይ በራስ ምታትና በሕመም መቃወም እስክትጀምር ድረስ ትክክለኛ ስለሆነው ሁኔታቸው አይነቁም፡፡ ነገር ግን ይህ ከሆነ በኋላ እንኳን እየተሰቃዩ ያሉት ሰዎች ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ ቢጀምሩና ችላ ወዳሉት ቀላል ዘዴ - ውኃንና ተገቢ ምግብን ወደ መጠቀም ቢመለሱ ኖሮ ተፈጥሮ የምትፈልገውን እና ከረዥም ጊዜ በፊት ማግኘት የነበረባትን እርዳታ ታገኝ ነበር፡፡ ሰዎች ይህን መንገድ ቢከተሉ ኖሮ በአጠቃላይ ሕመምተኛው ሳይደክም ያገግም ነበር፡፡ {2SM 451.2}Amh2SM 451.2

    መድኃኒቶች ሲወሰዱ ለጊዜው የሚጠቅሙን ይመስላሉ፡፡ ለውጥ ሊከሰት ይችላል፣ ነገር ግን በሽተኛው አልዳነም፡፡ ራሱን በሌላ መልክ ይገልጻል፡፡ ተፈጥሮ መድኃኒቱን ከሰውነት ውስጥ ለማስወጣት በምታደርገው ጥረት አንዳንድ ጊዜ ሕመምተኛው ከፍተኛ የሆነ ስቃይ ይደርስበታል፡፡ ፈወስ እንዲያመጣ ተብሎ መድኃኒት የተወሰደበት በሽታ ሊጠፋ ይችላል፣ ነገር ግን የሚጠፋው በአዲስ መልክ ለመገለጥ ነው፡፡ በአዲስ መልክ የሚገለጠው በቆዳ በሽታዎች፣ በቁስለቶች፣ በመገጣጠሚያም ሕመም እና አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በጣም አደገኛ እና ገዳይ በሆነ መልክ ነው፡፡ ጉበት፣ ልብ እና አእምሮ ብዙ ጊዜ በመድሃኒቶች ጉዳት ይደርስባቸዋል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ የአካል ክፍሎች በሙሉ ከበሽታ የተነሳ ጫና ይደርስባቸዋል፡፡ እነዚህ ያልታደሉ የጥቃት ሰለባዎች ቢኖሩ እንኳን ለመኖር ብቃት የሌላቸው፣ አሳዛኝ ኑሮን በድካም የሚመሩ ናቸው፡፡ እነሆ ያ መርዘኛ መድሃኒት የሚጠይቀው ወጪ ምንኛ ብዙ ነው! ሕይወትን ዋጋ ባያስከፍልም እጅግ ብዙ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ተፈጥሮ በጥረቷ ሁሉ ስንኩል ሆናለች፡፡ መላው የአካል ፋብሪካ ከሥርዓት ውጭ ስለሆነ በሕይወት ውስጥ እነዚህ ጉዳት የደረሰባቸው ደቃቅ ክፍሎች ከተፈጥሮ ረቂቅ ፋብሪካ ጋር ሕብረት በመፍጠር በጣም አስፈላጊ ሥራ እንዲሰሩ እምነት ቢጣልባቸውም በኋለኛው ጊዜ ሥራቸውን በብቃትና በብርታት መስራት ስለማይችሉ መላው አካል ጉድለት ይሰማዋል፡፡ በጤናማ ሁኔታ መገኘት ያለባቸው እነዚህ የሰውነት ክፍሎች ደካማ ይሆኑና ደም ይቆሽሻል፡፡ ተፈጥሮ በድንገት ጥረቷን እስክታቆም እና ሞት እስኪከተል ድረስ ትግሏን ትቀጥላለች፡፡ ተፈጥሮ የራሷን ሥራ እንድትሰራ ብትተው ኖሮ በበሽታ ከሚሞቱ ጠቅላላ ሰዎች ቁጥር ይልቅ መድሃኒት በመጠቀም የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ይበልጣል፡፡ {2SM 451.3}Amh2SM 451.3

    ሐኪሞች ላልታወቁ በሽታዎች መድሃኒቶችን በማዘዛቸው ምክንያት ብዙ ሕይወቶች ተሰውተዋል፡፡ በሽተኛውን እያሰቃየ ያለው በሽታ ምን እንደሆነ ትክክለኛ የሆነ እውቀት የላቸውም፡፡ ነገር ግን ሐኪሞች ምን ማድረግ እንዳለባቸው በቅጽበት እንዲያውቁ ሰዎች ይጠብቁባቸዋል፣ በሽታውን ያወቁ ይመስል ወዲያውኑ እርምጃ ካልወሰዱ ትዕግሥት በሌላቸው ጓደኞቻቸው እና በሕመምተኞቹ ዘንድ ብቃት እንደሌላቸው ሐኪሞች ተደርገው ይታያሉ፡፡ ስለዚህ የተሳሰቱ ሕመምተኞችንና ጓደኞቻቸውን ፍላጎት ለማሟላት ሲባል ምንነቱ በውል ያልታወቀ በሽታን ለመፈወስ መድሃኒት መሰጣት አለበት፣ ሙከራዎችም መደረግ አለባቸው፡፡ ተፈጥሮ ከውስጧ ማስወገድ የማትችላቸው መድሃኒቶች ይጫኑባታል፡፡ ብዙ ጊዜ ሐኪሞች ራሳቸው ለሌለ በሽታ ከባድ መድሃኒቶች መጠቀማቸውን ያምናሉ፣ ውጤቱም ሞት ነው፡፡ {2SM 452.1}Amh2SM 452.1

    ሐኪሞች ተግሳጽ የሚገባቸው ናቸው፣ ነገር ግን ስህተቱ የእነርሱ ብቻ አይደለም፡፡ ሕመምተኞች ራሳቸው ትዕግሥት ቢኖራቸው፣ አመጋገባቸውን ቢያስተካክሉና ትንሽ ስቃይ ቢታገሱ፣ ተፈጥሮ እንድታገግም ጊዜ ቢሰጡአት ኖሮ፣ ምንም መድሃኒት ሳይጠቀሙ በፍጥነት ያገግሙ ነበር፡፡ የመፈወስ ኃይሎች ያላት ተፈጥሮ ብቻ ነች፡፡ መድሃኒቶች የመፈወስ ኃይል የላቸውም፣ ነገር ግን በአጠቃላይ ተፈጥሮ የምታደርገውን ጥረት ይገድባሉ፡፡ ተፈጥሮ ወደ ቀድሞ ሁኔታ የመመለስን ሥራ መሥራት አለባት፡፡ ሕመምተኞች ለመዳን ይቸኩላሉ፣ የህመምተኞቹ ጓደኞችም ትዕግስት የለሾች ናቸው፡፡ መድሃኒት ከወሰዱ በኋላ በአካላቸው ውስጥ ያ ኃይለኛ የሆነ ተጽዕኖ ካልተሰማቸው የተሳሳቱ አመለካከቶቻቸው ያ ስሜት ሊሰማቸው እንደሚገባ እንዲያስቡ ስለሚመራቸው ትዕግስት በማጣት ሌላ ሐኪም ይቀይራሉ፡፡ ለውጡ ክፋቱን የበለጠ ይጨምራል፡፡ አደገኛነቱ ከመጀመሪያው መድሃኒት ጋር እኩል የሆነ እና ገዳይነቱ ከመጀመሪያው የበለጠ መድሃኒት ይታዘዝላቸዋል፡፡ ይህ የሚሆነው ሁለቱ ሕክምናዎች ስለማይጣጣሙና የአካል ክፍሎች መዳን እስከማይችሉ ድረስ ስለሚመረዙ ነው፡፡ {2SM 452.2}Amh2SM 452.2

    ነገር ግን ብዙዎች የውኃን ጥቅም በፍጹም ተለማምደው ስለማያውቁ ከታላላቆቹ የሰማይ በረከቶች አንዱ የሆነውን ለመጠቀም ይፈራሉ፡፡ ውኃ ይጎዳቸዋል ተብሎ ስለሚፈራ እንደ እሳት የሚያቃጥል ትኩሳት ያለባቸው ሰዎች እንዳይጠቀሙ ይከለከላሉ፡፡ ትኩሳት በሚሰማቸው ሰዓት በደንብ እንዲጠጡ ውኃ ቢሰጣቸውና በአካላቸውም ላይ ቢደረግ ኖሮ ረዥም የሥቃይ ቀናትና ሌሊቶች ይቀሩና ብዙ የከበሩ ነፍሳት በዳኑ ነበር፡፡ ነገር ግን በሺሆች የሚቆጠሩ ሰዎች ትኩሳቱን ይመግብ የነበረው ነዳጅ ነዶ እስኪያልቅ ድረስ የሚነድ ትኩሳት ሰውነታቸውን እየበላቸው ሙተዋል፡፡ ብዙዎች የነደደውን ጥማቸውን ለማስታገስ ውኃ እንዲጠጡ ሳይፈቀድላቸው ዋና የአካል ክፍሎቻቸው ተቃጥለው በብዙ ሥቃይ ሙተዋል፡፡ ስሜት የሌለው ሕንጻ ሲቃጠል እሳቱን ለማጥፋት የሚፈቀድ ውኃ ዋና የአካል ክፍሎቻቸውን እየበላ ያለውን ትኩሳት እንዲያጠፋ እንዳይጠጡ ለሰብዓዊ ፍጥረቶች ይከለከላል፡፡ {2SM 453.1}Amh2SM 453.1

    የአካል ሕጎቻቸውን በተመለከተ ብዙዎች ይቅርታ ሊደረግላቸው በማይችል ድንቁርና ውስጥ ናቸው፡፡ ትውልዳችን ለምን ደካማ እንደሆነ እና ለምን ብዙዎች ያለ ጊዜ እንደሚሞቱ ግራ ይገባቸዋል፡፡ መንስኤ የለውምን? ስለ ሰብዓዊ አካል እውቀት እንዳላቸው የሚናገሩ ሀኪሞች ለሕመምተኞች፣ ለራሳቸው ውድ ልጆችና ለጓደኞቻቸው ሳይቀር በሽታን ለመስበር ወይም ቀለል ያለ ሕመም ለመፈወስ ፈጣን ያልሆኑ መርዞችን ያዛሉ፡፡ በርግጥ የእነዚህን ነገሮች ክፋት መረዳት አይችሉም፣ ቢረዱ ኖሮ ይህን አያደርጉም ነበር፡፡ የመርዙ ውጤቶች ወዲያው ላይታዩ ይችላሉ፣ ነገር ግን የሰውነት አቋምን በማዳከም፣ እና ተፈጥሮ የምታደርገውን ጥረት ሽባ በማድረግ በአካል ውስጥ በእርግጠኝነት ሥራውን እየሰራ ነው፡፡ ክፉን ለማረም እየፈለጉ ናቸው፣ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ ሊፈወስ የማይችል ከመጀመሪያው የበለጠ ክፉ እያመጡ ናቸው፡፡ በዚህ ሁኔታ የተያዙ ግለሰቦች ሁልጊዜ ታማሚዎችና እንቅልፋሞች ናቸው፡፡ ነገር ግን ንግግራቸውን ብትሰሙአቸው ሁልጊዜ ሲጠቀሙአቸው የነበሩአቸውን መድሃኒቶች ሲያወድሱና ለራሳቸው ጥቅም ስላገኙባቸው ሌሎችም እንዲጠቀሙአቸው ሲነግሩ ትሰሙአቸዋላችሁ፡፡ ከመንስኤውና ከውጤቱ በመነሳት ማገናዘብ ለሚችሉ ሰዎች ጥቅም አግኝተንበታል የሚሉ ሰዎች የገረጣ ፊት፣ ሁልጊዜ አመመኝ እያሉ መናገር፣ እና አጠቃላይ ከፍተኛ የድካም ስሜት መድሃኒቶቹ ጤንነትን የሚጎዱ ለመሆናቸው በቂ ማረጋገጫ መሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ብዙዎች የተጠቀሙአቸው መድኃኒቶች ሁሉ ከማዳን ይልቅ ሁኔታቸው የበለጠ እንዲከፋ እንዳደረጉ እንዳያዩ ዓይኖቻቸው ታውሯል፡፡ በመድሃኒት ምክንያት ዋጋ ቢስ የሆነ ግለሰብ በዓለም ውስጥ የመጀመሪያውን ቁጥር ይይዛል፣ ነገር ግን በአጠቃላይ ሲታይ ብስጩ፣ ቁጡ፣ ሁልጊዜ ታማሚ፣ አሳዛኝ ኑሮ የሚኖር፣ እና የሌሎችን ትዕግሥት ሁልጊዜ የሚፈታተን ይመስላል፡፡ ተፈጥሮ በሕይወት ላይ ያላትን ቁጥጥር መተው ስለማትፈልግ መርዘኛ መድሃኒቶች ወዲያውኑ አልገደሉአቸውም፡፡ ሆኖም እነዚህ መድኃኒት ወሳጆች በፍጹም ደህና ሆነው አያውቁም፡፡ {2SM 453.2}Amh2SM 453.2

    በገበያ ውስጥ ያሉ መጨረሻ የሌላቸው የመድሃኒት ዓይነቶች፣ እነርሱ እንደሚሉት አስደናቂ ፈውስ ሊያመጡ የሚችሉ አዳዲስ መድሃኒቶች እና ቅልቅሎች ማስታወቂያዎች አንድን ሰው ቢጠቅሙ በመቶዎች የሚቆጠሩትን ይገድላሉ፡፡ ሕመምተኞቹ ትዕግሥተኞች አይደሉም፡፡ ተቀላቅሎ ስለሚሰጣቸው መድሃኒት የሚያውቁት ምንም ነገር ባይኖራቸውም አንዳንዶቹ በጣም ኃይለኛ የሆኑ የተለያዩ ዓይነት መድሃኒቶችን ይወስዳሉ፡፡ የሚወስዷቸው መድሃኒቶች ሁሉ የመዳን ሁኔታቸውን የበለጠውን ተስፋ ቢስ ያደርጉታል፡፡ ሆኖም መውሰዳቸውን ይቀጥሉና እስኪሞቱ ድረስ ሁኔታቸው እየከፋ ይሄዳል፡፡ አንዳንዶች በማንኛውም ጊዜ መድሃኒት ይኖራቸዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች እነዚህን ጎጂ ቅልቅሎችና የተለያዩ ዓይነት ገዳይ መርዞች በራሳቸው ሀላፊነት እንዲወስዱ ተውአቸው፡፡ የእግዚአብሔር አገልጋዮች በአካል ውስጥ ጎጂ የሆነ ውጤት የሚያስከትሉ መሆናቸውን የሚያውቋቸውን መድሃኒቶች፣ ከሕመም ጊዜያዊ ፋታ የሚሰጡ ቢሆኑ እንኳን፣ ማዘዝ የለባቸውም፡፡ --How to Live, no. 3, pp. 49-64. {2SM 454.1}Amh2SM 454.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents