Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሁሉም ለራሳቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንዲያውቁ

    ጥያቄህ፣ «…አስቸኳይ ሁኔታ ሲገጥም፣ በጤና ተቋም ውስጥ ያሉ ሐኪሞች ሥራ ስለበዛባቸው ወደ ውጭ ሄደው ለማገልገል ጊዜ ስለሌላቸው ዓለማዊ ሐኪሞችን መጥራት አለብን ወይ?” ይላል፡፡ ሐኪሞቹ ሥራ ስለሚበዘባቸው ከተቋም ውጭ ሕመምተኞችን ማከም የማይችሉ ከሆነ፣ ትክክለኛ ማንነታቸውን ለመደበቅ ሲባል ረዥም ስም የተሰጣቸውን መድሃኒቶች ለመጠቀም ከመድፈር ይልቅ ሁሉም ቀላል ፈውሶችን እንዲጠቀሙ ማስተማር ጠቢብነት አይደለምን? ማንም ሰው ቢሆን ለእግዚአብሔር ፈውሶች ማሃይም መሆን የለበትም፤ እነርሱም በሙቅ ውኃ መታጠብና በቀዝቃዛና በሙቅ ውኃ መጫን ናቸው፡፡ በሕመም ጊዜ ከአመጋገብ ጥቅም ጋር መተዋወቅ ጠቃሚ ነው፡፡ ለሕመምተኞች የሚጠነቀቅን ሰው ሊጠሩ ይችላሉ፣ ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ስለሚኖርበት ቤት ጥበብ ያለበት እውቀት ሊኖረው ይገባል፡፡ በሕመም ጊዜ ምን ማድረግ እንደሚያስፈልግ ሁሉም ሰው ማወቅ አለበት፡፡Amh2SM 289.4

    እኔ ታምሜ ቢሆን ኖሮ ከአጠቃላይ ባለሙያዎች መካከል ሐኪምን የምጠራው አንድ ጠበቃን ወደ ቤቴ ከምጠረው በማይበልጥ ፍጥነት ነው፡፡ የላቲን ስም የሚሰጡአቸውን ብቃት የሌላቸውን መድሃኒቶቻቸውን በእጄ አልነካም፡፡ ወደ ሰውነቴ የማስገባውን እያንዳንዱን ነገር ቀጥተኛ በሆነ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ለማወቅ ወስኛለሁ፡፡Amh2SM 290.1

    መድሃኒቶችን የመውሰድ ልምድ ያላቸው ሰዎች በማስተዋላቸው ላይ ኃጢአት እየሰሩና የወደ ፊት ሕይወታቸውን በሙሉ አደጋ ላይ እየጣሉ ናቸው፡፡ ሲጠቀሙባቸው ለበርካታ አሳሳቢ ለሆኑ ችግሮች መፍትሄ መስጠት የሚችሉ ጉዳት የሌላቸው እጽዋቶች አሉ፡፡ ለሰውነታቸው አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በተመለከተ ሁሉም ብልህ መሆን ቢፈልጉ ኖሮ ሕመም የተለመደ ነገር ከመሆን ይልቅ ብዙ የማይታይ ነገር ይሆን ነበር፡፡ የአንድ ወቄት መከላከል ከነጥር ፈውስ ጋር እኩል ነው፡፡ Manuscript 86, 1897 (General manuscript, “Health Reform Principles,” written from Cooranbong, Australia).Amh2SM 290.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents