Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    እያንዳንዱን ቃል-ኪዳን አሰባስብ

    የእያንዳንዱ የጸጋ ሕይወት፣ የእያንዳንዱ የተስፋ ሕይወት፣ የእያንዳንዱ የሥርዓት ሕይወት፣ የእያንዳንዱ የበረከት ሕይወት የሆነው ይህ ኢያሱስ ነው፡፡ ኢየሱስ የሕይወት ውጫዊ መገለጫ፣ ክብርና መዓዛ፣ ራሱ ሕይወት ነው፡፡ «የሚከተለኝ የህይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም” (ዮሐ. 8፡ 12)፡፡ ያኔ የተዋጁት እንዲሄዱበት የተነጠፈው ንጉሣዊው መንገድ ተስፋ የሚያስቆርጥ ጨለማ አይደለም፡፡ ኢየሱስ ባይኖር ኖሮ የክርስትና ጉዞአችን በርግጥም ብቸኝነትና ሥቃይ ያለበት ይሆን ነበር፡፡ «ወላጅ እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም” ይለናል (ዮሐ. 14፡ 18)፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱን ተጽፎ ያለውን ተስፋ ሰብስበን እንያዝ፡፡ በቀን እንድገማቸው በሌሊትም እናሰላስላቸው፣ ደስም ይበለን፡፡ Amh2SM 244.1

    “በዚያ ቀን፡- አቤቱ ተቆጥተኸኛልና፣ ቁጣህንም ከእኔ መልሰሃልና፣ አጽናንተኸኛልምና አመሰግንሃለሁ፡፡ እነሆ፣ አምላክ መድሃኒቴ ነው፤ ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌና ዝማሬዬ ነውና፣ መድሃኒቴም ሆኖአልና በእርሱ ታምኜ አልፈራም ትላለህ፡፡ ውኃንም ከመድሃኒት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ፡፡ በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፡- እግዚአብሔርን አመስግኑ፣ ስሙንም ጥሩ፤ በአህዛብ መካከል ሥራውን አስታውቁ፤ ስሙ ከፍ ያለ እንደሆነ ተናገሩ፡፡ ታላቅ ሥራ ሰርቷልና ለእግዚአብሔር ተቀኙ፤ ይህንም በምድር ሁሉ ላይ አስታውቁ፡፡ አንቺ በጽዮን የምትኖሪ ሆይ፣ የእሥራኤል ቅዱስ በመካከልሽ ከፍ ከፍ ብሏልና ደስ ይበልሽ እልልም በዪ (ኢሳይያስ 12:1-6)፡፡Amh2SM 244.2

    ይህ እኛ እየሄድንበት ያለው መንገድ በጌታ የተዋጁት እንዲሄዱበት የተነጠፈ የንጉሥ መንገድ አይደለምን? ከዚህ የተሻለ መንገድ ሊዘጋጅ ይችላልን? ችግር የማያጋጥምበት የተሻለ መንገድ ሊኖር ይችላልን? በፍጹም! በፍጹም! ስለዚህ የተሰጠንን መመሪያ ተግባር ላይ እናውል፡፡ አዳኛችንን እንደ ምሽጋችን፣ ከሰይጣን ፍላጻዎች ለመከላከል በቀኝ እጃችን እንዳለ እንደ ጋሻችን እንመልከት፡፡Amh2SM 244.3

    ፈተናዎች ያጠቁናል፣ ችግርና ጨለማ ይጫኑናል፡፡ ልብና ሥጋ ሊከዱን ሲዘጋጁ በዘላለማዊ ክንዶቹ የሚያቅፈን ማን ነው? ክቡር ተስፋውን የሚተገብር ማን ነው? የመተማመኛና የተስፋ ቃላትን ወደ አእምሮአችን የሚያመጣልን ማን ነው? ከልባቸው በእውነት ለሚጠይቁት ጸጋውን ያለ ሥፍር የሚሰጠው የማን ጸጋ ነው? ጸጋውን የሚሰጠንና ከኃጢአታችን የሚያድነን ማን ነው? ጉምንና ጭጋግን የሚያስወግድና ወደ እርሱ የፀሐይ ብርሐን የሚያመጣን የማን ብርሐን ነው? ይህን የሚያደርግ ከኢየሱስ በቀር ማን ነው? ስለዚህ እርሱን ውደዱት፣ አመስግኑትም፡፡ «ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፣ ደግሜም እላለሁ ደስ ይበላችሁ” (ፊል. 4፡ 4)፡፡ ኢየሱስ ዛሬም ሕያው አዳኝ ነውን? «ከክርስቶስ ጋር ከተነሳችሁ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያሉትን ነገሮች እሹ» (ቆላ. 1፡ 3)፡፡ ከክርስቶስ ጋር ተነስተናል፡፡ ክርስቶስ ሕይወታችን ነው፡፡ በምህረቱና በጸጋው ፍቅር እንደ ተመረጥን፣ የልጅነት ማዕረግ እንዳገኘን፣ ይቅርታ እንዳገኘን እና እንደጸደቅን ተረጋግጦልናል፡፡ ስለዚህ ጌታን ከፍ ከፍ እናድርገው፡፡ --Letter 7, 1892.Amh2SM 245.1