Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከመከራ ወራት የተማርኳቸው ትምህርቶች

    ከሕመም፣ ከሥቃይና ከረዳተ-ቢስነት የተነሳ በታላቅ ፈተና ውስጥ እያለፍኩ ነበር፣ ነገር ግን በዚያ ሁሉ ውስጥ ከወርቅ ይልቅ የከበረ ልምምድ አግኝቻለሁ፡፡ በአውስትራሊያና በኒውዚላንድ ያሉ ቤተ ክርስቲያናትን ለመጎብኘት በውስጤ የያዝኳቸውን እቅዶች መተው እንዳለብኝ መጀመሪያ ራሴን ባሳመንኩ ጊዜ አሜሪካን ለቅቄ ወደዚህ ሩቅ አገር መምጣት የእኔ ተግባር ስለመሆኑ ጠንከር ያለ ጥያቄ መጠየቅ እንዳለብኝ ተሰማኝ፡፡ ይደርስብኝ የነበረው ሥቃይ ኃይለኛ ነበር፡፡ በርካታ እንቅልፍ የሌላቸውን ሌሊቶች አውሮፓን ለቀን ወደ አሜርካ ከሄድን ጀምሮ ያለውን ልምምድ እያመላለስኩ ሳስብ የነበረ ሲሆን ልምምዱ የማያቋርጥ ስጋት፣ ሥቃይ እና ሸክም መሸከም የነበረበት ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ይህ ሁሉ ምን ማለት ነው? አልኩ፡፡ Amh2SM 240.4

    ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ የነበረውን ታሪክና እግዚአብሔር እንድሰራ የሰጠኝን ሥራ በጥንቃቄ ከለስኩ፡፡ አንዴም ቢሆን አልጣለኝም፤. ብዙ ጊዜ ራሱን የገለጠልኝ ጉልህ በሆነ ሁኔታ ሲሆን የማማርርበትን አንድም ነገር አላየሁም፤ በዚያ ፋንታ በልምምዴ ሁሉ ውስጥ የከበሩ ነገሮች እንደ ወርቅ ክር ሲያልፉ አየሁ፡፡ የሚያስፈልጉኝን ነገሮች ከእኔ ይልቅ ጌታ ስለተገነዘበ ወደ ራሱ በጣም እያቀረበኝ እንደሆነ ተሰማኝ፤ ከዚህ የተነሳ እግዚአብሔር ለእኔ ምን ማድረግ እንዳለበት እንዳላዘው መጠንቀቅ አለብኝ፡፡ ይህ አለመታረቅ በስቃይና በረዳተ-ቢስነት ጅምር ውስጥ ነበር፣ ነገር ግን መከራዬ የእግዚአብሔር እቅድ አካል መሆኑ የተሰማኝ ብዙም ሳይቆይ ነበር፡፡ በከፊል ተኝቼና በከፊል ተቀምጬ ምንም እንኳን ብዙ ሥቃይ እየደረሰብኝ ቢሆንም ራሴን አመቻችቼ ሽባ የሆኑ እጆቼን በመጠቀም ብዙ መጻፍ እንደምችል ተገነዘብኩ፡፡ ወደዚህ አገር ከመጣሁ ወዲህ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ገጾችን ጽፌያለሁ፡፡Amh2SM 241.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents