Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ 5—ተአምራቶች በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ (ተቀባይነት) የማግኘት መፈተኛዎች አይደሉም

    ተአምራዊ መገለጦችን አትፈልጉ

    የወደፊቱን የማየት ልዩ ችሎታዎችም ሆኑ ተአምራታዊ መገለጦች ሰዎች ለሥራቸው ትክክለኝነት ወይም ትክክል እንደሆኑ ስለሚከራከሩላቸው ሀሳቦች ማረጋገጫ ናቸው ለሚሉት ሀሳብ ማንም ሰው ዋጋ አይስጥ፡፡ እነዚህን ነገሮች በሰዎች ፊት የምናቆይ ከሆነ ክፉ ውጤት፣ ጤናማ ያልሆነ ስሜት ይፈጥራሉ፡፡ በሰብዓዊ ልቦች ውስጥ ትክክለኛ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በቃሉ አማካይነት ብቃትን እንደሚሰጥ ተስፋ ተሰጥቷል፡፡ ቃሉ መንፈስና ሕይወት እንደሆነ ክርስቶስ ተናግሯል፡፡ «ውሆች ባህርን እንደሚከድኑ ምድር የእግዚአብሔርን ክብር በማወቅ ትሞላለች” (እንባቆም 2፡ 14)፡፡ {2SM 48.1}Amh2SM 48.1

    ሰብዓዊ ፈጠራዎች የመልአክ ልብስ ለብሰው እንዲቀርቡ ለማድረግ ሰይጣን እጅግ ብልጠት ባለበት ሁኔታ ይሰራል፡፡ ነገር ግን ከቃሉ የሚወጣው ብርሃን በሞራል ጨለማ መካከል እያበራ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ በተአምራዊ መገለጦች በፍጹም አይተካም፡፡ እውነት መጠናት አለበት፣ እንደ ተደበቀ ሀብት መፈለግ አለበት፡፡ አስደናቂ ማብራሪያዎች ከቃሉ ውጭ አይሰጡም፣ ወይም የእሱን ቦታ መውሰድ አይችሉም፡፡ በቃሉ ተጣበቁ፣ ሰዎችን ለመዳን ጠቢባን ማድረግ የሚችለውን በአእምሮ ውስጥ የተደረገውን ቃል ተቀበሉ፡፡ ይህ ክርስቶስ ሥጋውን ስለመብላትና ደሙን ስለመጠጣት የተናገራቸው ቃላት ትርጉም ነው፡፡ እንዲህ ይላል፡- «እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት» (ዮሐ 17፡3)፡፡ {2SM 48.2}Amh2SM 48.2

    ያልሆኑትን ነን የሚሉ ሰዎች ያጋጥሙናል፤ ሀሰተኛ ነቢያት ይነሳሉ፤ ሀሰተኛ ሕልሞችና ራዕዮች ይኖራሉ፤ ነገር ግን ቃሉን ስበኩ፣ በቃሉ ውስጥ ካለው የእግዚአብሔር ድምፅ ወደ ሌላ አቅጣጫ አትወሰዱ፡፡ ምንም ነገር አእምሮን ወደ ሌላ አቅጣጫ አይቀይር፡፡ ግሩም፣ አስደናቂ የሆነው ይወከልና ይቀርባል፡፡ በሰይጣናዊ ማታለያዎች አማካይነት አስደናቂ ተአምራቶች ይፈጸማሉ፣ የሰብዓዊ ወኪሎች ጥያቄዎች ይነሳሳሉ፡፡ ከዚህ ሁሉ ተጠንቀቁ፡፡ {2SM 49.1}Amh2SM 49.1

    ማንም ሰው በእውነት ፈንታ ውሸትን እንዳይቀበል ክርስቶስ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡ መንፈስ የሚሰራበት ብቸኛው መስመር የእውነት መስመር ነው፡፡…እምነታችንና ተስፋችን የተመሰረተው በስሜት ላይ ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ ነው፡፡ --Letter 12, 1894. {2SM 49.2}Amh2SM 49.2