Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ለጉዳዩ መዘጋጀት

    የንግድ ማህበራትና የአለም አንድነቶች ወጥመድ ናቸው፡፡ ወንድሞቼ ሆይ፣ ከእነርሱ ራቁ፣ ራቁአቸው፡፡ ከእነርሱ ጋር ምንም ግንኙነት አይኑራችሁ፡፡ ከእነዚህ ማህበራትና አንድነቶች የተነሳ በቅርቡ ተቋሞቻችን በከተማዎች ውስጥ ሥራቸውን ለመስራት በጣም ከባድ ይሆንባቸዋል፡፡ ማስጠንቀቂያዬ ከከተማዎች ራቁ የሚል ነው፡፡ በከተማዎች የጤና ተቋማትን አትገንቡ፡፡ ሕዝባችን ከከተማዎች ወጥተው ትንሽ መሬት ወደሚያገኙበትና ለራሳቸውና ለልጆቻቸው ቤት ወደሚሰሩበት እንዲሄዱ አስተምሯቸው፡፡…{2SM 142.3}Amh2SM 142.3

    ምግብ ቤቶቻችን በከተማዎቻችን መሆን አለባቸው፤ ይህ ካልሆነ በእነዚህ ምግብ ቤቶች የሚሰሩ ሰራተኞች ሕዝብን መድረስና የትክክለኛ አኗኗርን መርሆዎች ማስተማር አይችሉም፡፡ አሁን በከተማዎች የመሰብሰቢያ ቤቶችን መያዝ እንችላለን፡፡ ነገር ግን በቅርቡ ከተማዎችን መልቀቅ የሚፈልጉ እስከማይችሉ ድረስ በከተማዎች ጠብና ግራ መጋባት ይሆናል፡፡ ስለ እነዚህ ጉዳዮች እየተዘጋጀን መሆን አለበት፡፡ ይህ የተሰጠኝ ብርሃን ነው፡፡ --General Conference Bulletin, April 6, 1903. {2SM 142.4}Amh2SM 142.4