Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ግልጽ የሆነ መረዳት አስፈላጊነት

    ሥልጣናትና ኃይላት እና በከፍታ ሥፍራ ያሉ መንፈሳዊ ክፋቶች እውነትን ወደሚዋጉበት ጊዜ ስንቃረብ፣ የሰይጣን የማታለል ኃይል ቢቻለው የተመረጡትን እንኳን እስኪያስታቸው ድረስ እጅግ ታላቅ ሲሆን፣ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንድናውቅና ለሰይጣን ማታለያዎች አለአዋቂዎች እንዳንሆን መረዳታችን በመለኮታዊ መገለጥ መሞረድ አለበት፡፡ የወቅቱን የመዝጊያ ሥራ ማከናወን እንድንችል ሰብዓዊ ጥረት ከመለኮታዊ ኃይል ጋር መጣመር አለበት፡፡ {2SM 15.3}Amh2SM 15.3

    ክርስቶስ ንፋስን እንደ እግዚአብሔር መንፈስ ምሳሌ አድርጎ ተጠቅሟል፡፡ ንፋስ ወደ ወደደው አቅጣጫ እንደሚነፍስ እና ከየት እንደሚመጣና ወዴት እንደሚሄድ እንደማናውቅ ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስም እንዲሁ ነው፡፡ በማን አማካይነት እንደሚገለጽ አናውቅም፡፡ {2SM 15.4}Amh2SM 15.4

    ነገሮችን የመፈተን ቀንና ዕድሉ እያላቸው የእግዚአብሔርን ድምፅ ለይተው ያላወቁትን ወይም የእርሱን መንፈስ አነሳሽነት ያላደነቁትን የእግዚአብሔር መንፈስ ትቷቸው ያልፋል ስል የራሴን ቃላት እየተናገርኩ አይደለሁም፡፡ በሺሆች የሚቆጠሩ በ11ኛው ሰዓት ላይ እውነትን ይመለከቱና ይቀበላሉ፡፡ {2SM 16.1}Amh2SM 16.1

    «እነሆ አራሹ አጫጁን፣ ወይን ጠማቂውም ዘሪውን የሚቀድምበት (የሚያገኝበት) ወራት ይመጣል ይላል እግዚአብሔር” (አሞጽ 9:13). {2SM 16.2}Amh2SM 16.2

    እነዚህ ወደ እውነት የሚደረጉ መለወጦች ቤተ ክርስቲያንን በሚያስደንቅ ፍጥነት ስለሚፈጸሙ የእግዚአብሔር ስም ብቻ ይከበራል፡፡ --Letter 43, 1890. {2SM 16.3}Amh2SM 16.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents