Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ትዝ የሚሉ ጥቂት ጉዳዮች

    በመሞት ላይ የነበረ ኤልደር ኬ የተባለ ሰው በባትል ክሪክ ሆስፒታል ውስጥ እያለ ክፍሉ ለማትረፍ ከፍተኛ ጉጉት በነበራቸው ሰዎች ተሞልቶ ነበር፡፡ ብዙዎች ተታለው ነበር፡፡ ሰውዬው መገለጥ ያለው ይመስል ነበር፡፡ ነገር ግን ለእኔ የተሰጠኝ ብርሃን «ይህ ሥራ ከእግዚአብሔር አይደለም፣ መልእክቱን አትመኚ» የሚል ነበር፡፡ [ገጽ 96ን እና ሰሌክትድ መሰጅስ አንደኛው መጽሐፍ ገጽ 176-184ን ይመልከቱ]፡፡ {2SM 64.1}Amh2SM 64.1

    ከጥቂት አመታት በኋላ በካሊፎርኒያ ግዛት ውስጥ ካለው ሬድ ብለፍ ከሚባል ቦታ ኤን የተባለ ሰው ለእኔ መልእክት ሊያስተላልፍ መጣ፡፡ መልእክቱ ከክብሩ የተነሳ ምድርን ሊያበራ ያለው የሶስተኛው መልአክ ከፍ ያለ ጩኸት ነው አለ፡፡ እግዚአብሔር በመሪነት ደረጃ ያሉትን ሰራተኞችን በሙሉ ትቶ በማለፍ መልእክቱን ለእሱ እንደሰጠው ያስባል፡፡ እንደተሳሳተ ላሳየው ሞከርኩ፡፡ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች ባቢሎን ናቸው አለ፡፡ እኛም ትክክል እንዳልሆነ ከነገርነው በኋላ ተሳስተሃል ያልንበትን ምክንያቶች በመንገር ጉዳዩን በፊቱ ስናስቀምጥለት ታላቅ ኃይል በላዩ መጣበትና በርግጥም ታላቅ ጩኸት ጮኸ፡፡…ከእሱ ጋር ብዙ ተቸገርን፤ አእምሮው ሚዛኑን ስቶ በአእምሮ ሕመምተኞች መጠጊያ እንዲቆይ ተደረገ፡፡ {2SM 64.2}Amh2SM 64.2

    ጋርማይር የተባለ አንድ ሰው [ምዕራፍ 9ን ይመልከቱ] የሶስተኛውን መልአክ ከፍ ያለ ጩኸት በተመለከተ ሌሎች እንዲቀበሉት ሀሳብ ያቀረበውን መልእክት አሳተመ፤ አሁን አንተ ከምታደርገው ጋር ተመሳሳይ በሆነ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያንን ወነጀለ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ መሪዎች በሙሉ ራሳቸውን ከፍ ከፍ ከማድረጋቸው የተነሳ ይወድቁና ሌሎች አስደናቂ ሥራዎችን የሚሰሩ ትሁት ሰዎች ወደ ፊት ይመጣሉ አለ፡፡ ይህ ሰው ራዕዮች እንዳሏቸው የሚናገሩ ሴት ልጆች ነበሩት፡፡ {2SM 64.3}Amh2SM 64.3

    ይህ ማታለያ በፊቴ ተገልጦ ነበር፡፡ ይህ ሰው አዋቂ የሆነ፣ ተቀባይነት ያለው፣ ራሱን የካደ፣ ከፍተኛ ፍላጎት ያለውና ቅን የሆነ፣ ራስን ቀድሶ የመስጠትና የመሰጠት መልክ ያለው ነው፡፡ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ቃል እንዲህ ሲል መጣልኝ፣ «እኔ አልላኳቸውምና አትመኗቸው!” {2SM 64.4}Amh2SM 64.4

    በምስክሮች እንደሚያምን ተናገረ፡፡ እውነት መሆናቸውን እንደሚያምን በመናገር አንተ በተጠቀምክበት ሁኔታ እሱ አምናለሁ ለሚላቸው ነገሮች ኃይልና የእውነት መልክ እንዲሰጡ ተጠቅሞባቸዋል፡፡ ይህ መልእክት ከእግዚአብሔር እንዳልነበረ ነገርኳቸው፤ ነገር ግን ላልተጠነቀቁት አሳሳች ነበር፡፡ ሲነገረው ለማመን ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ የልጁ ራዕዮች [የኣና] ውሸት መሆናቸውን ነገርኳቸው፣ ነገር ግን እነዚህ ራዕዮች ከሲስተር ኋይት ራዕዮች ጋር ተመሳሳይ መሆናቸውንና ተመሳሳይ ነገሮችን እንደሚገልጹ ተናገረ፡፡ ይህቺ ሴት ልጅ ቤተሰቦቿንና እነዚህን የውሸት መልእክቶችን ያመኑትን ሌሎች ብዙ ሰዎች እያታለለች ነበር፡፡ ይህቺ ወጣት ልጃገረድ መልካም ባሕርይ እንደሌላት፣ ነገር ግን የተበላሸች እንደሆነች እንዳይ ተደርጌ ነበር፡፡... {2SM 65.1}Amh2SM 65.1

    እንዲህ በአክብሮት ስለታየ ሰው መገለጥ የሚኖረው ቢሆን ኖሮ የሚሆነው ይህ ሰው ነበር፤ ነገር ግን የእርሱ መገለጥ ከእግዚአብሔር ሳይሆን ከሰይጣን መሆኑን በግልጽ ነገርኩት፡፡ መልእክቱ መለኮታዊ ሥልጣን ያለው አልነበረም፡፡ {2SM 65.2}Amh2SM 65.2

    ይህን መልእክት ለዓለም ማሰራጨት እንዲችል አንድ የዋህ፣ ትጉህ ወጣት የሪቪውና ሄራልድ ዝርዝርን መስረቅ ሀላፊነቱ እንደሆነ እንዲያምን አደረገው፡፡ ይህ በመንግሥት ደረጃ የሚያሳስር ወንጀል ስለነበር ወጣቱ ባትል ክሪክን ለቆ ሸሸ፡፡ ለተወሰነ ጊዜ ወደ ባትል ክሪክ መመለስ አልደፈረም ነበር፡፡ የምህረት ደጅ የሚዘጋበት ጊዜ ተወስኖ ነበር [በዚህ አክራሪ መምህር]፣ እያንዳንዱ ትንቢት ሳይፈጸም ሲቀር ይህ ወጣት እንደተታለለ አየና ኃጢአቱን ተናዞ አሁን የባትል ክሪክ ቤተ ክርስቲያን የተከበረ አባል ነው፡፡ {2SM 65.3}Amh2SM 65.3

    ከዚያ በኋላ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ኦ የሚል ስም ያለው ሌላ ሰው ከኮኔክቲከት የሶስተኛውን መልአክ መልእክት በተመለከተ አዲስ ብርሃን ብሎ የጠራውን መልእክት ይዞ መጣ፡፡ ይህ ብልህ ቤተሰብ በዚህ ማታለያ አማካይነት ከሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን ተለይቶ ነበር፡፡ ይህን አዲስ ብርሃን ተብሎ የተጠራውን መልእክት የሚቃወም ጽኑ ምስክር ስላስተላለፍኩ፣ እሱ በሚኖርበት በ-----፣ ኮኔክቲከት፣ እኔን፣ ሥራዬንና ምስክርነቶቼን ተቃወመ፡፡ {2SM 65.4}Amh2SM 65.4

    የኦ ልጆች አባት በባትል ክሪክ የተካሄደውን ኮንፍረንስና የአገልጋዮች የመጽሐፍ ቅዱስ ተቋም ተከታተለ፤ ነገር ግን ራሱን ከሌሎች በመለየት ከስብሰባው መንፈስ ጋር ራሱን አላዋሃደም ነበር፡፡ ወደ ቤቱ ተመለሰና በ----የነበረችውን ትንሽ ቤተ ክርስቲያን ማበላሸት ጀመረ፡፡ እዚያ ቦታ ባልለፋ ኖሮ እውነትንና የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያንን አቋም፣ እና በተለይም ሚስስ ኋይትን በመካዳቸው መላውን ቤተ ክርስቲያን ሊገነጥሉ ነበር፡፡ {2SM 65.5}Amh2SM 65.5

    በተመሳሳይ ጊዜ አንዲት ሚስስ ፒ የተባለች ሴት ሙሉ በሙሉ እንደተቀደሰችና የመፈወስ ኃይል እንዳላት እየተናገረች ከዋሽንግተን ዲ ሲ መጣች፡፡ ይህ መንፈስ ብዙዎችን ወደ ግራ መጋባት መራ፡፡ ከእነርሱም ጋር ተመሳሳይ የሆነ የክስ መንፈስ ነበር፡፡ ያውም ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ እንደ ተሳሳተች እና ከእሷ ውስጥ ተአምራቶችን የሚሰራን ሕዝብ እግዚአብሔር እየጠራ እንደሆነ የሚናገር ነበር፡፡ በባትል ክሪክ ከነበረው ሕዝባችን አብዛኛው ክፍል እየተገነጠለ ነበር፡፡ በማታ ወቅት በባትል ክሪክ ለነበረው ሕዝባችን እንድጽፍ የእግዚአብሔር መንፈስ አነሳሳኝ፡፡ {2SM 66.1}Amh2SM 66.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents