Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በዕድሜ እያረጁ መሄድ ግን መመስከርን መቀጠል

    ውድ ወንድም ጂ አይ ቡትለር ሆይ፣

    በእምነት ልጅ የሆኑት ከዚህ በፊት ጌታ የሰጠን መልእክቶች በዚህ የምድር ታሪክ ወቅት እጅግ ጠቃሚ መሆናቸውን መገንዘብ እንዲችሉ በጌታ አገልግሎት የሸበቱ ሽማግሌ ወታሮች ምስክርነታቸውን እስከ ተገቢው ቦታ ድረስ መሸከማቸውን እንዲቀጥሉ ታላቅ ፍላጎት አለኝ፡፡ ያለፈው ልምምዳችን ከነበረው ጥንካሬ አንዲት ነጥብ እንኳን አላጣም፡፡ ስለ ቅዱስ ቃሉ እያንዳንዱ ነጥብና ርዕስ ጌታን አመሰግናለሁ፡፡ ከልምምዳችን ጠንካራ ክፍሎች ወደ ኋላ አላፈገፍግም፡፡ Amh2SM 229.3

    ካለህ ብርታት ባሻገር መሥራት የለብህም፡፡ ወደ ፊት ልምምዳችን የተለያየ ዓይነት ይሆናል ብዬ እገምታለሁ፤ ነገር ግን በክርስቶስ አገልግሎት፣ ፈቃዱን በማድረግ እያረጀን ያለን አንተና እኔ ከፍተኛ ዋጋ ያለውንና እጅግ ጥልቅ ፍላጎት የሚያሳድረውን ልምምድ እያገኘን ነን ብዬ አስባለሁ፡፡Amh2SM 229.4

    የእግዚአብሔር ፍርዶች በምድር ላይ ናቸው፡፡ ሌሎች ወደ ፊትና ወደ ላይ መንቀሳቀስ እንዲችሉ ለመርዳት በምናደርገው ሥራ ውስጥ መላው እኛነታችንን በማስቀመጥ ከሙሉ ልብ በሆነ ታማኝነት መሥራት አለብን፡፡ ጦርነቱን እስከ ደጅ ድረስ እንግፋ፡፡ ለሚያመነቱትና ለደከሙት የማበረታቻ ቃላትን ለመናገር ሁልጊዜ እንዘጋጅ፡፡ ከክርስቶስ ጋር ስንራመድ ያለ ችግር መራመድ እንችላለን፡፡ ምንም ነገር ቢሆን በድፍረትህ ላይ ውኃ አያርከፍክፍብህ፡፡Amh2SM 229.5

    ከስብሰባዎቻችን መካከል በአንዳንዶቹ ውስጥ ወደ ፊት አገኝሃለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እምነትን ለረዥም ጊዜ ከጠበቁትና በሕይወት ካሉት መካከል እኔና አንተ በዕድሜ በጣም ያረጀን ነን፡፡ የጌታችንን መገለጥ ለማየት በሕይወት መኖር ካልቻልን፣ የተሰጠንን ሥራ ሰርተን የጦር መሣሪያዎቻችንን በተቀደሰ ክብር እናስቀምጣለን፡፡ የምንችለውን ሁሉ እናድርግ፣ የምናደርገውን ሁሉ በእምነትና በተስፋ እናድርግ፡፡ ጌታ ሕይወቴን እስከዚህ ድረስ ስላቆየ ልቤ በምሥጋና ተሞልቷል፡፡ እስከሁን ድረስ ቀኝ እጄ ሳይንቀጠቀጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ጉዳዮችን መጻፍ ይችላል፡፡ የእህት ኋይት እጆች እስካሁን ድረስ መመሪያ የሚሆኑ ቃላትን መጻፍ ይችላሉ ብለህ ለሁሉም ንገር፡፡ በብሉይ ኪዳን ታሪክ ላይ ሌላ መጽሐፍ ጽፌ እያጠናቀቅኩ ነኝ፡፡Amh2SM 230.1

    ጌታ ይባርክህ፣ በተስፋና በድፍረትም ይጠብቅህ፡፡ Letter 130, 1910.Amh2SM 230.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents