Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 28—በመድኃኒት አጠቃቀም ላይ የተሰጡ መግለጫዎች

    በመድኒቶች ላይ የተነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ የተሰጠ መግለጫ

    ጥያቄዎችህ ሙሉ በሙለም ባይሆን በአብዛኛው ሃው ቱ ሊቭ በሚለው መጽሐፍ ውስጥ ተመልሰዋል እላለሁ፡፡ የመድኃኒት መርዞች ማለት አንተው የጠቀስካቸው ነገሮች ናቸው፡፡ ቀላል መድኃኒቶች ከቀላልነታቸው የተነሳ ጎጂነታቸው አነስተኛ ነው፤ ነገር ግን እነዚህም ቢሆኑ በብዙ አጋጣሚዎች በፍጹም አስፈላጊ ባልሆኑበት ጊዜ ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡Amh2SM 279.1

    እያንዳንዱ ቤተሰብ ለራሱ ጠበቃን ከሚፈልገው ባልበለጠ ፍጥነት ወደ ሐኪም መሄድ ሲያስፈልገው መጠቀም የሚችላቸው ቀላል ቅጠላቅጠሎችና ሥራሥሮች አሉ፡፡ ሐኪሞች ቀምመው ከሚጠቀሟቸው መድኃኒቶች መካከል በፍጹም ጎጂ ያልሆኑት የመድኃኒት ዓይነቶች እነዚህ ናቸው ብዬ ዝርዝር መስጠት የምችል አይመስለኝም፡፡ ቢሆንም በዚህ ጉዳይ ላይ ተቃራኒ ሆኖ መገኘት ጠቢብነት አይደለም፡፡Amh2SM 279.2

    ባለሙያዎች ቀምመው ያዘጋጁአቸውን አደገኛ መድኋኒቶቻቸውን መጠቀምን በተመለከተ ጽኑ አቋም ስላላቸው እነዚህን ነገሮች እንደ መጨረሻ አማራጭ አድርጎ መውሰድን በጽኑ ተቃውሜያለሁ፡፡ በፍጹም አይፈውሱም፤ ችግሩን ከመፍታት ይልቅ የከፋ ሁኔታ ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡ መድኃኒቶችን ከሚያዙት መካከል አብዛኞቹ ያንን መድኃኒት ለራሳቸው አይጠቀሙትም፣ ወይም ለልጆቻቸው አይሰጡም፡፡ ስለ ሰብአዊ አካል ትክክለኛ እውቀት ቢኖራቸውና በቀላሉ ሊጎዳ የሚችለውን አስደናቂ የሆነ የሰብአዊ አካል ፋብሪካ ቢገነዘቡ ኖሮ፣ ግሩምና ድንቅ ሆነው መፈጠራቸውን በተገነዘቡና እነዚህን ጠንካራ መድኃኒቶች በሰብአዊ አካል ውስጥ ማስገባትን ባልተለማመዱም ነበር፡፡Amh2SM 280.1

    ይህ ጉዳይና የመድኃኒት ሕክምና አሳዛኝ ሸክም በፊቴ ክፍት ሆኖ ሳለ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች እነዚህን ጤናን የሚያበላሹ ፈጠራዎችን ሁሉ በማስወገድ የጤና ተቋማትን እንዲያቋቁሙና ሐኪሞች ህመምተኞችን ንጽህናን የመጠበቅን መርህ በመከተል እንዲያክሙ ብርሃን ተሰጥቶኝ ነበር፡፡ ትልቁ ሸክም መሆን ያለበት «ትዕዛዝ በትዕዛዝ፣ ትዕዛዝ በትዕዛዝ፣ ሥርዓት በሥርዓት፣ ሥርዓት በሥርዓት፣ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ” (ኢሳ. 28፡ 10) ለማስተማር በደንብ የሰለጠኑ ነርሶችንና የህክምና ባለሙያዎችን ማግኘት ነው፡፡ Amh2SM 280.2

    አንድ ወቄት (ounce) መከላከያ ከአንድ ነጥር (pound) ፈዋሽ መድኃኒት የበለጠ ዋጋ እንዳለው በማስታወስ ሰዎች ልምዶቻቸውን እንዲያርሙና ጤናማ የሆኑ ልምምዶችን እንዲያጎለብቱ አሰልጥኑ፡፡ በዚህ መስመር የሚሰጡ ትምህርታዊ መግለጫዎችና ጥናቶች እጅግ ከፍተኛ ዋጋ አላቸው፡፡ Letter 17a, 1893.Amh2SM 280.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents