Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የደሞዝ እርከን፣ ግን በትክክለኛነት

    በእስዊዘርላንድ ሳለሁ በቢሮ የሚሰራ ማንም ቢሆን በሳምንት ከአስራ ሁለት ዶላር በላይ ማግኘት የለበትም የሚል ቃል ከባትል ክሪክ መጣልኝ፡፡ እኔም ይህ አይሰራም አልኩ፤ አንዳንዶች ከዚህ በላይ ማግኘት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ቢሮ ለሚሰራ ለማንኛውም ሰው የዚህ ደሞዝ እጥፍ ሊሰጥ አይገባም፤ ምክንያቱም ጥቂቶች ከግምጃ ቤት ይህን ያህል ብዙ ደሞዝ ከወሰዱ ለሁሉም ፍትህ ሊሰራ አይችልም፡፡ በሌሎች መንገዶች ልክ እንደ እነርሱ ከፍተኛ ደሞዝ የሚገባቸው ሰዎች እጅግ አነስተኛ ሲከፈላቸው ለጥቂት ሰዎች ከፍተኛ ደሞዝ መክፈል የዓለም ዕቅድ ነው፡፡ ይህ ፍትህ አይደለም፡፡ Amh2SM 192.1

    በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት፣ የሕትመት ቢሮ፣ የጤና ተቋም እና ማተሚያ ቤት ውስጥ የሚሰሩ ጌታን የሚወዱና የሚፈሩ ሰዎች ይኖራሉ፡፡ ደሞዛቸው በዓለማዊ መስፈርት መሰረት መዘጋጀት የለበትም፡፡ በተቻለ መጠን መሳፍንታዊ ስርዓትን ለማስቀጠል ሳይሆን የሰማይ ሕግ የሆነውን እኩልነትን ለማስቀጠል ጥሩ የሆነ ውሳኔ ሥራ ላይ መዋል አለበት፡፡ «ሁላችሁም ወንድማማቾች ናችሁ” (ማቴ. 23፡ 8)፡፡ ጥቂቶች ከፍተኛ የሆነ ደሞዝ መጠየቅ የለባቸውም፣ እንደዚህ ዓይነት ደሞዝም ችሎታንና መክሊትን ለማግኘት እንደ ማባበያ መቅረብ የለበትም፡፡ ይህ ነገሮችን በዓለማዊ መርህ ላይ ማስቀመጥ ነው፡፡ የደሞዝ ጭማሪ ከጭማሪው ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ራስ ወዳድነትን፣ ኩራትን፣ ታይታን፣ የራስ ፍላጎትን ማሟላትን እና አሥራታቸውን ለመክፈልና ሥጦታቸውን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ የሚቻላቸውን ሁሉ እያደረጉ ያሉ ሰዎች መሸፈን የማይችሉትን አስፈላጊ ያልሆነ ብክነት ያመጣል፡፡ ድህነት በሁሉም ወሰኖቻቸው ይታያል፡፡ ራሳቸውን መስዋዕት የሚያደርጉ፣ ትሁት የሆኑ፣ እግዚአብሔርን የሚወዱና ሊያገለግሉት ጥረት የሚያደርጉ ተናዛዥ ነፍሳት በዚህ ሕይወት ያሉትን መልካም ነገሮች ለማግኘት ነጻነት ከሚሰማው ሰው ይልቅ በዘላለማዊው ፍቅር ወሰን የለሽ ልብ አጠገብ ከሚጠበቁ በቀር እግዚአብሔር አንዱን እንደ ሌላኛው ሁሉ ይወዳል፡፡ Amh2SM 192.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents