Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 6—ከማታለያዎች መዳኛችን (መጠበቂያችን)

    ቅንነት ብቻውን አያድንም

    በውሸት ማመን በሕይወት ወይም በባሕርይ ላይ የመቀደስ ተጽእኖ አይኖረውም፡፡ ስህተት እውነት አይደለም፣ ወይም በመደጋገም እውነት ሊደረግ አይችልም፣ ወይም በእሱ በማመን እውነት ሊደረግ አይችልም፡፡ ቅንነት ውሸትን ማመን ከሚያስከትለው ውጤት ነፍስን በፍጹም ማዳን አይችልም፡፡ ያለ ቅንነት እውነተኛ ኃይማኖት የለም፣ ነገር ግን በውሸት ኃይማኖት ላይ ቅን መሆን ሰውን በፍጹም አያድንም፡፡ በፍጹም ቅንነት የስህተትን መንገድ ልከተል እችላለሁ፣ ነገር ግን ያ ድርጊቴ መንገዱን ትክክለኛ መንገድ አያደርገውም፣ ወይም እኔ መድረስ ወደ ፈለግኩበት ቦታ አያደርሰኝም፡፡ ጌታ ጭፍን እምነት እንዲኖረንና ያንን እምነት የሚቀድስ እምነት ብለን እንድንጠራ አይፈልግም፡፡ እውነት የሚቀድስ መርህ ነው፣ ስለዚህ እውነት ምን እንደሆነ ማወቅ ይጠበቅብናል፡፡ መንፈሳዊ ነገርን ከመንፈሳዊ ነገር ጋር ማወዳደር አለብን፡፡ ሁሉን መፈተን አለብን፣ ነገር ግን መልካም የሆነውን፣ መለኮታዊ መረጃ የያዘውን፣ ወደ ተግባር ማስቸኮል ያለባቸውን ሀሳቦችና መርሆዎች በፊታችን የሚያስቀምጠውን ነገር ብቻ አጽንተን መያዝ አለብን፡፡ --Letter 12, 1890. {2SM 56.1}Amh2SM 56.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents