Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለአንባቢያን

    ይህ መጽሐፍ ከአንደኛው መጽሐፍ ጋር በመሆን በአንዳንድ ጽሁፎች፣ በተባዙ ዶክመንቶች፣ እና መጽሔቶች ላይ የወጡ ምክሮችን ክፍተት ይሞላል፣ በቋሚነትም እንዲጠበቁ ያደርጋል፡፡ አሁን ያለው የትንቢት መንፈስ ሥነ-ጽሁፍ ቋሚ አካል እንደመሆኑ በአዲሱ የኤለን ጂ ኋይት ጽሁፎች ቃላት ማውጫ ዝርዝር ውስጥ ተካትቷል፡፡ ምርጥ መልእክቶች የሚለው መጽሐፍ እንዴት እና ለምን እንደተሰባሰበ የሚገልጽ አረፍተ ነገር በአንደኛው መጽሐፍ ላይ «ለአንባቢያን» በሚለው ክፍል ውስጥ ተሰጥቷል፤ ስለዚህ በዚህኛው ላይ መድገም አያስፈልግም፡፡Amh2SM 11.1

    በዚህኛው መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ምክሮች ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች የነፍሳት ጠላት በቅሬታዋ ቤተ ክርስቲያን ላይ በወግ አጥባቂነት፣ በአሳሳች ትምህርቶች እና ስህተትና ተቃዋሚ በሆኑ እንቅስቃሴዎች መልክ የሚያመጣቸውን ጥቃቶች ለመቋቋም ይጠቅማሉ፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች ምክሮቹ ለግለሰቦች ልዩ በሆነ መመሪያ የተቀመጡ ሲሆኑ የቀረቡት ነጥቦች መጨረሻ ከመምጣቱ በፊት እንደሚነሱ እርግጠኛ መሆን ከምንችልባቸው ጉዳዮች ጋር ተመሳሳይ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ነገሮች ቤተ ክርስቲያኗን በአጠቃላይ የሚያሰጉ አደጋዎችን ለመመከት ይጠቅማሉ፡፡ ሌሎች አጠቃላይ ምክሮች እንደ ጥበብ የጎደላቸው ሕብረቶች፣ የሠራተኞች ደመወዝ እና እውነተኛውና ሐሰተኛው ፈውሶች ያሉትን ጥያቄዎች ይመልሳሉ፡፡Amh2SM 11.2

    በተለየ ሁኔታ የሚደነቀው ነገር በክፍል 7 ላይ «መድኃኒትነት ያላቸውን ነገሮች መጠቀም» የሚለው ክፍል ነው፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ያሉት ዓረፍተ ነገሮች፣ ከኤለን ኋይት ምንጮች የተወሰዱትና በዚህ ቦታ የተሰባሰቡት፣ አንባቢው ስለ መድኃኒቶች ጥቅም የሚነሱ ጥያቄዎችን እያጠና ሳለ ይጠቅሙታል፡፡Amh2SM 11.3

    ይህ መጽሐፍ ስድስት ምዕራፎች ባሉት ተጨማሪ መግለጫ ይደመደማል፡፡ ይህ ከሚስስ ኋይት «በሽታና መንስኤው” ከሚለው ጽሁፍ እንደገና የታተመ ሲሆን መጀመሪያ ጤና ወይም እንዴት መኖር እንዳለብን በሚለው መጽሐፍ ስድስት ቁጥሮች ውስጥ ከታተመው የተወሰደ ነው፡፡Amh2SM 11.4

    የአንባቢው ትኩረት የዚህን አዲስ መጽሐፍ በርካታ ክፍሎች ወደሚያስተዋውቁ አረፍተነገሮች፣ በተላይም ወደ ክፍል 7 እና ወደ ተጨማሪ መግለጫ፣ እንዲሳብ ተደርጓል፡፡Amh2SM 11.5

    ምርጥ መልእክቶች በሚለው አንደኛው መጽሐፍ ውስጥ ‹ለአንባቢያን» በሚለው ክፍል በተለያዩ ክፍሎች ውስጥ ያሉት ነገሮች ያልተገናኙ ቢሆኑም እንዲመች በማለት ብቻ በእነዚህ ቋሚ መጽሐፎች ውስጥ አንድ ላይ መደረጋቸው ተጠቁሞአል፡፡Amh2SM 11.6

    መጽሐፎቹ «ወደ ፍጻሜ ስንቃረብ” የሚል ርዕስ ባላቸው ክፍሎች መደምደማቸው ገጣሚ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ በቤተ ክርስቲያን አሸናፊነት ላይ መተማመንን የሚፈጥሩ በርካታ የተለዩ መልዕክቶች አሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ኤለን ኋይት በሕይወት እያለች በተካሄደው የመጨረሻው የጄኔራል ኮንፈረንስ ስብሰባ ወቅት በ1913 ዓ.ም የተናገረቻቸው ሁለት መልእክቶች ነበሩ፡፡ እድሜዋ ገፍቶ ስለነበር ይህንን ታላቅ ስብሰባ መካፈል አልቻለችም ነበር፡፡ እነዚህ መልእክቶች እንደ እርሷ ባሉ ሰራተኞች ላይ የነበራትን መተማመንና እርሷ ሕይወትዋን የሰጠችው ሥራ ድል እንደሚያደርግ የነበራትን መተማመን ይገልጻሉ፡፡Amh2SM 11.7

    ዳግም ምጻትን የሚጠብቁ የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባላት ወደ እግዚአብሔር ከተማ በሚያደርጉት ጉዞ የመጨረሻዎቹን ማይሎች እየተጓዙ ሳሉ ይህኛው ምርጥ መልእክቶች በሚል ርዕስ የቀረበው መጽሐፍ ደስ እንዲያሰኛቸው አሳታሚዎችና የኤለን ኋይት ጽሁፎች ባለአደራዎች ልባዊ ምኞታቸው ነው፡፡Amh2SM 11.8

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents