Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 51—ታማኝ ወይም ታማኝነት የጎደለው

    ክህደቶች

    ስለ ሕዝባችን ነፍሴ ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት ይሰማታል፡፡ እየኖርን ያለነው በፍጻሜ ዘመን አደጋዎች ውስጥ ነው፡፡ ጥልቀት የሌለው እምነት ጥልቀት የሌለውን ልምምድ ያመጣል፡፡ መናዘዝ የሚያስፈልግ ኑዛዜ አለ፡፡ በኃይማኖታዊ አስተምህሮ ውስጥ ትክክለኛ የሆነ ልምምድ ሁሉ የያህዌን አሻራ ይይዛል፡፡ ሁሉም ለራሳቸው በግላቸው እውነትን የመረዳትን አስፈላጊነት ማየት አለባቸው፡፡ በጥንቃቄና በጸሎት ሲጠኑ የነበሩትን አስተምህሮዎች መረዳት አለብን፡፡ የሶስተኛውን መልአክ መልእክት መነሳትና ወደ ፊት መቀጠልን በተመለከተ በሕዝባችን መካከል ታላቅ የእውቀት እጦት እንዳለ ተገልጦልኛል፡፡ የዳንኤልንና የራዕይን መጻሕፍት የመመርመርና የተጻፈውን ነገር ለማወቅ መጻሕፍቱን በጥልቀት የመማር ከፍተኛ አስፈላጊነት አለ፡፡Amh2SM 392.1

    ተሰጥቶኝ የነበረው ብርሃን በጣም ኃይለኛ ሲሆን ብዙዎች ጆሮአቸውን ለአሳሳች መናፍስትና ለሰይጣን አስተምህሮዎች በመስጠት ከእኛ እንደሚለዩ ተገልጦልኝ ነበር፡፡ ጌታ የሚፈልገው እያንዳንዱ እውነትን አምናለሁ የሚል ነፍስ እውነት ምን እንደሆነ በደንብ እንዲያውቅ ነው፡፡ ሀሰተኛ ነቢያት በመነሳት ብዙዎችን ያስታሉ፡፡ የሚበጠር ነገር ሁሉ ይበጠራል፡፡ ታዲያ የእምነታችንን ጉዳይ ማወቅ የእያንዳንዱ ግለሰብ ጉዳይ አይደለምን? በብዙ ስብከቶች ፈንታ አሁን ወዳለንበት ወደ ዘላለማዊ የእውነት መድረክ ያመጡንን መሠረታዊ አስተምህሮዎች የያዙትን ጠንካራ ማስረጃዎች ለማግኘት መጻሕፍትን በመግለጥ የእግዚአብሔርን ቃል በቅርበት መመርመር መኖር አለበት፡፡Amh2SM 392.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents