Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ግላዊ ቃል

    በሥራው መስክ ቅንነት ባለበት ሥራ ላይ በግሌ ለመሰማራት እመኛለሁ፣ በእኔ እድሜ ባለው የአካል ብርታት መተማመን ጥበብ ያለበት አይደለም የሚል እምነት ባይኖረኝ ኖሮ እጅግ በእርግጠኝነት መሳተፍ የምፈልገው በሕዝብ አገልግሎት ላይ ነው፡፡ የሶስተኛው መልኣክ መልእክት በታወጀባቸው አመታት በሙሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይሰጠኝ የነበረውን ብርሃን ለቤተ ክርስቲያን እና ለዓለም በማሳወቅ ረገድ የምሰራው ሥራ አለኝ፡፡ ለመድረስ በምችልባቸው ሰዎች ሁሉ ፊት እውነትን የማስቀመጥ ልባዊ የሆነ ፍላጎት አለኝ፡፡ አሁንም አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ለሕትመት በማዘጋጀት ድርሻዬን እየተወጣሁ ነኝ፡፡ ነገር ግን በፍጹም መጻፍ በማልችልበት ቦታ ራሴን እንዳላስቀምጥ እጅግ በጥንቃቄ መንቀሳቀስ አለብኝ፡፡ ምን ያህል ዘመን እንደምኖር አላውቅም፣ ነገር ግን እኔ የምጠብቀውን ያህል የጤና ችግር የለብኝም፡፡Amh2SM 404.3

    የ1909 ዓ.ም የጄነራል ኮንፍራንስ ስብሰባን ተከትሎ በኒው ኢንግላንድ፣ በመካከለኛ እና በመካከለኛ ምዕራብ ግዛቶች በሰፈር በተደረጉና ሌሎች አጠቃላይ ስብሰባዎች ላይ በመሳተፍና የተለያዩ ተቋሞችን በመጎብኘት በርካታ ሳምንታትን አሳልፌ ነበር፡፡Amh2SM 404.4

    በካሊፎርኒያ ወዳለው ቤቴ በመመለስ ነገሮችን ለሕትመት የማዘጋጀትን ሥራ እንደ አዲስ ጀመርኩ፡፡ ባለፉት አራት አመታት ውስጥ ከሌላ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር ጥቂት ደብዳቤዎችን ጽፌያለሁ፡፡ የቀረኝን ጉልበቴን የሰጠሁት በአብዛኛው አስፈላጊ የሆኑ መጻሕፍትን የማዘጋጀት ሥራዎችን ለመጨረስ ነበር፡፡Amh2SM 405.1

    አልፎ አልፎ ስብሰባዎችን ተሳትፌያለሁ፣ በካሊፎርኒያ ያሉ ተቋሞችንም ጎብኝቻለሁ፣ ነገር ግን ካለፈው የጄነራል ኮንፍራንስ ስብሰባ ወዲህ ከጊዜዬ ትልቁን ክፍል ያሳለፍኩት በሰይንት ሄሌና አጠገብ በነበረው የገጠር ቤቴ «እልምስሀቨን» በጽሁፍ ሥራ ላይ ነበር፡፡Amh2SM 405.2

    በመጻሕፍቴ ላይ ትንሽ ረዘም ያለ ጊዜ እንድሰራ ጌታ እድሜ እየጨመረልኝ ስለሆነ አመሰግነዋለሁ፡፡ መሰራት እንዳለበት የሚታየኝን ሁሉ ለመሥራት ምነው ብርታት በኖረኝ! ሕዝባችን እጅግ የሚፈልገውን እውነት ግልጽ በሆነና ተቀባይነት ባለው ሁኔታ መቅረብ እንድችል ጥበቡን እንዲሰጠኝ እጸልያለሁ፡፡ ይህን እንዳደርግ እግዚአብሔር እንዲያስችለኝ እንዳምን ተደፋፍሬያለሁ፡፡Amh2SM 405.3

    በአጠቃላይ ሥራው ላይ ያለኝ ፍላጎት ከዚህ በፊት እንደነበረው ሁሉ ጥልቅ ነው፡፡ የወቅቱ እውነት ሥራ በመላው የዓለም ክፍሎች ያለማቋረጥ እንዲቀጥል በጣም እመኛለሁ፡፡ ነገር ግን የመጻሕፍት ዝግጅት ሥራ የእኔን ክትትል ስለሚፈልግ በበርካታ የህዝብ አገልግሎት ላይ መሳተፍ የሚመከር እንዳልሆነ አያለሁ፡፡ ከሁሉ ከተሻሉ ሰራተኞች መካከል አንዳንዶች አብረውን ይሰራሉ፤ እነዚህ ሠራተኞች ወደ አሜሪካ ከተመለስኩ ጀምሮ ከእኔ ጋር አንድነት ከፈጠሩት ሌሎች ጋር በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ከእኔ ጋር በአውስትራሊያ የተገናኙ ናቸው፡፡ ስለ እነዚህ የሚረዱኝ ሰዎች እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፡፡ ነገሮችን ለህትመት ለማዘጋጀት የምንችለውን ሁሉ በማድረግ ሁላችንም እጅግ ሥራ ይበዛብናል፡፡ ስለ እምነታችን ምክንያቶች እውቀት የሌላቸው ሰዎች እውቀት እንዲያገኙ የእውነት ብርሃን ወደ ሁሉም ቦታዎች እንዲሄድ እፈልጋለሁ፡፡ አንዳንዴ ዓይኖቼ ያስቸግሩኛል፣ ከፍተኛ የህመም ስሜት ይሰማኛል፡፡ ነገር ግን የማየት ችሎታዬን ስለጠበቀልኝ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፡፡ በእኔ እድሜ ዓይኖቼን በፍጹም መጠቀም ባልችል እንግዳ ነገር አይሆንም ነበር፡፡Amh2SM 405.4

    ከፍ ከፍ ስለሚያደርገው የእግዚአብሔር መንፈስ፣ እሱ እየሰጠኝ ስላለው ምቾትና ፀጋ፣ ለሕዝቡ ማበረታቻና እርዳታ እንድሰጥ ብርታቱንና እድሉን ስለሰጠኝ መግለጽ ከምችለው በላይ ምስጋናዬ የበዛ ነው፡፡ ጌታ በሕይወት እስካኖረኝ ድረስ ፈቃዱን ለመፈጸምና ስሙን ለማስከበር በመሻት ለእርሱ ታማኝና እውነተኛ እሆናለሁ፡፡ እርሱን ለማወቅ የማደርገውን ጥረት እንድቀጥልና ፈቃዱን በተሟላ ሁኔታ ማድረግ እንድችል ጌታ እምነቴን ይጨምርልኝ፡፡ እግዚአብሔር መልካም ስለሆነ ምስጋናው ከፍ ማለት አለበት፡፡Amh2SM 405.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents