Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    እግዚአብሔር የተጠቀመባቸው ስዕሎች

    ሁለተኛው ትዕዛዝ ለምስል መስገድን ይከለክላል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ራሱ ለሕዝብ የሚሰጡ መልእክቶች በሌላ መንገድ ቢሰጡ ኖሮ በደንብ ለመረዳት ስለሚከብዱ ለነቢያቱ ትምህርት ሲሰጥ ስዕሎችንና ምልክቶችን ተጠቅሟል፡፡ ይህንን በማድረጉ በማየት ስሜታቸው አማካይነት እንዲረዱ አደረጋቸው፡፡ ለዳንኤልና ዮሐንስ ትንቢታዊ ታሪክ የቀረበው በምልክቶች ነበር፣ የሚያነባቸው ሰው እንዲያስተውላቸው እነዚህ ነገሮች በጠረጴዛዎች ላይ በግልጽ እንዲቀመጡ ነበር፡፡ Amh2SM 319.4

    ለስዕሎች እጅግ ብዙ ገንዘብ እየወጣ መሆኑ እውነት ነው፤ ወደ እግዚአብሔር ግምጃ ቤት መፍሰስ ያለበት ጥቂት የማይባል ገንዘብ ለሰዓሊው እየተከፈለ ነው፡፡ ነገር ግን ጽንፈኞች ከሚከተሉት መንገድ የተነሳ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚመጣው ክፉ ነገር እነርሱ ለማስተካከል ከሚሞክሩት ነገር እጅግ ይበልጣል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የመለያ መስመሩ እምኑ ላይ እንደሆነ እና ስዕል መስራት ኃጢአት የሚሆነው የት እንደሆነ መናገር ከባድ ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔርን የሚወዱና በፍጹም ልባቸው ትዕዛዛቱን ለመጠበቅ የሚሹት በእርሱ ይመራሉ፡፡ ማንም ሰው የእነርሱ ህሊና እንዲሆን አይፈቅድም፡፡ ሚዛናቸውን ካልጠበቁ አእምሮዎች የሚመጡ ሀሳቦችንና አመለካከቶችን ሁሉ የሚቀበል ሰው ይወዛገባል ግራም ይጋባል፡፡ በፀጋና በእውነት እውቀት ማደግ ያለባቸው አእምሮዎችና ልቦች እግዚአብሔር እንዳይከበርባቸው እንዲቀጭጩና ደካማ እንዲሆኑ ለማድረግ ትኩረትን ከሶስተኛው መልአክ መልእክት መመለስ የሰይጣን ዓላማው ነው፡፡ Historical Sketches of the Foreign Missions of the Seventh-day Adventists, pp. 211, 212.Amh2SM 320.1