Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ክፍል 8—አጠቃላይ ምክሮች

    መግቢያ

    የትንቢት መንፈስ ምክሮች ሁልጊዜ ተግባራዊ ናቸው፡፡ ከኤለን ኋይት ብዕር የክርስቲያን ሕይወትን እና ልምምድን እያንዳንዱን ምዕራፍ የሚነካ ምክርና መመሪያ እናገኛለን፡፡ ምንም እንኳን አብዛኞቹ የተሰጡት መመሪያዎች በቴስቲሞኒስ እና በሌሎች የኤለን ጂ ኋይት መጻሕፍት ውስጥ የተወከሉ ቢሆንም ከዚህ በፊት ታትመው አሁን ከሕትመት ውጭ ለሆኑት ነገሮች እና ላልታተሙ የእጅ ጽሁፎች እንደገና የቃላት ማውጫ ሲዘጋጅላቸው ዛሬ አዲስና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ብቅ ከማለታቸው የተነሳ ጠቀሜታቸው እየጨመረ በመሄድ ላይ ያሉትን ምክሮች በአንዳንድ መስመሮች አሳይቷል፡፡ እነዚህ ነገሮች ተጨባጭ በሆነ መንገድ በሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች እጅ ውስጥ ባለው የመመሪያ ሀብት ላይ ተጨማሪ ይሆናሉ፡፡ Amh2SM 310.1

    ለምሳሌ ያህል በሕክምና ችግር ጽንሰ ሀሳብ ላይ በአንዳንድ የሕክምና ክበቦች ውስጥ ለሕክምና የሚረዱ ተደርገው የሚታዩትንና መጀመሪያ ያልታተሙ አረፍተ ነገሮችን እናቀርባለን፡፡ ሰዎችን በሰመመን ውስጥ መክተትን ሕመምተኞችን የማከሚያ ዘዴ አድርጎ መጠቀምን በተመለከተ ኤለን ጂ ኋይት የሰጠቻቸው ልዩ ምክሮች እና ይህ ዘዴ በማንኛውም መንገድ የሚያስከትለውን አደጋ ያመለከተችበት ነገር ለአሁኑ ጊዜ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡Amh2SM 310.2

    ይህ ክፍል የሚደመደመው ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች ለመኖሪያቸው የገጠር አካባቢ ያለውን ጠቀሜታ እንዲያስቡበት ጥሪ በማቅረብ ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች የተወሰዱት ከታተሙት መጻሕፍት ውጭ ከሆኑ ምንጮች ነው፣ ነገር ግን በገጠር መኖር በሚል መጽሔት ውስጥ ቤትን ለመስራት ከከተሞች መጨናነቅ ርቆ በገጠር ውስጥ አዲስ ቦታን መምረጥን በተመለከተ በጥንቃቄ እና በእርጋታ መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግ አስቀድሞ አጽንዖት በመስጠት ቀርቦ ነበር፡፡ በዚህ ቦታ ቋሚ በሆነ መልክ በመቅረብ ዝግጁ እንደሆነ ማጣቀሻ ሆኖ ቀርቧል፡፡ Amh2SM 310.3

    የኋይት ባለአደራዎች፡፡

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents