Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    አድልዎ የሌለው ፍቅር አግባብነት የሌለውን ጥላቻ ያቀልጣል

    እውነተኛ የሆነ ሚስዮናዊ መንፈስ ወደ ሰዎች ልብ ሲገባ የወገንተኝነት፣ የመደብና የዘር ግድግዳዎች ይወድቃሉ፡፡ አግባብነት የሌለው ጥላቻ በእግዚአብሔር ፍቅር ይቀልጣል፡፡--Review and Herald, Jan. 21, 1896; The Southern Work, 1966 ed., p. 55.Amh2SM 486.5

    በጥቁሮችና በነጮች መካከል የመለያ ግምብ ተገንብቷል፡፡ ክርስቲያኖች ለፈጣሪያቸው ከሁሉ የበለጠ ፍቅር እና ለጓረቤቶቻቸው አድልዎ የሌለበት ፍቅር እንዲኖራቸው የሚመክረውን የእግዚአብሔርን ቃል ሲታዘዙ እነዚህ አግባብነት የሌላቸው የጥላቻ ግድግዳዎች እንደ ኢያሪኮ ግንብ በራሳቸው ይፈራርሳሉ፡፡ --Review and Herald, Dec. 17, 1895; Republished in The Southern Work, 1966 ed., p. 43.Amh2SM 486.6

    መንፈስ ቅዱስ ሲፈስ ሰዎች የሰብዓዊ ፍጡራንን ነፍስ መዳን ስለሚሹ ሰብአዊነት አግባብነት በሌለው ጥላቻ ላይ ድልን ይቀዳጃል፡፡ እግዚአብሔር አእምሮዎችን ይቆጣጠራል፡፡ ሰብዓዊ ልቦች ክርስቶስ እንደወደደ ይወዳሉ፡፡ የቆዳ ቀለም መለያዎች አሁን ብዙዎች ከሚመለከቱት በተለየ ሁኔታ ይታያል፡፡ ክርስቶስ እንደወደደ መውደድ አእምሮን ንጹህና ሰማያዊ በማድረግ ራስ ወዳድነት ወደ ሌለው ከባቢ አየር ከፍ ያደርጋል፡፡ --Testimonies, vol. 9, p. 209.Amh2SM 487.1