Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    አዲስ ድርጅት አይኖርም

    ጊዜው ካለፈ በኋላ እግዚአብሔር ለታማኝ ተከታዮቹ የወቅቱን እውነት የከበሩ መርሆዎች ሰጣቸው፡፡ እነዚህ መርሆዎች የመጀመሪያውንና የሁለተኛውን መላእክት መልእክቶች በማሳተላለፍ ሥራ ድርሻ ላልነበራቸው አልተሰጡም ነበር፡፡ መርሆዎቹ የተሰጡት ከሥራው ጅምር ጀምሮ የራሳቸው ድርሻ ለነበራቸው ሠራተኞች ነበር፡፡ Amh2SM 389.3

    በእነዚህ ልምምዶች ውስጥ ያለፉ ሰዎች ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች እንድንሆን ላደረጉን መርሆዎች እንደ ዓለት የፀኑ እንዲሆኑ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በደቀመዛሙርቱ መካከል ምስክርን በማሰርና ሕግን በማተም ከእግዚአብሔር ጋር አብረው ሠራተኞች ሊሆኑ ነው፡፡ ሥራችንን በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት መሠረት ላይ በመመስረት ሥራ ላይ የተሳተፉ ሰዎች፣ ትክክለኛውን መንገድ ያመለከቱትን ምልክቶች የሚያውቁ ሰዎች እጅግ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ሰራተኞች ተደርገው ሊታዩ ነው፡፡ የተሰጣቸውን እውነት በተመለከተ ከግል ልምምዳቸው ተነስተው መናገር ይችላሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች እምነታቸው ወደ አለማመን እንዲለወጥ አይፈቅዱም፤ የሶስተኛው መልአክ አርማ ከእጃቸው እንዲወሰድ አይፈቅዱም፡፡ የመጀመሪያውን መታመናቸውን እስከ መጨረሻው ድረስ ሊይዙ ነው፡፡Amh2SM 389.4

    ወደ ፍጻሜው ሥራ ስንገባ ሳለ ያለፈው ታሪክ እንደሚደገም ጌታ ተናግሮናል፡፡ ለዚህ የመጨረሻ ዘመን የሰጠው እያንዳንዱ እውነት ለዓለም መታወጅ አለበት፡፡ እሱ የመሠረተው እያንዳንዱ ምሶሶ መጠናከር አለበት፡፡ እግዚአብሔር የመሠረተውን መሠረት ትተን መሄድ አንችልም፡፡ አሁን ወደ ማንኛውም አዲስ ድርጅት መግባት አንችልም፤ ይህን ማድረግ እውነትን መካድ ነው፡፡ Manuscript 129, 1905.Amh2SM 390.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents