Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 39—ለምርጫ ድምጽ ስለመስጠት የተሰጠ ምክር

    የእኛ ሥራ መንቃት፣ መጠበቅና መጸለይ ነው፡፡ መጻሕፍትን መርምሩ፡፡ ከዓለም ጋር እንዳትደባለቁ ክርስቶስ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷችኋል፡፡ ከውስጣቸው ወጥተን የተለየን መሆን አለብን፣ «ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኩስንም አትንኩ ይላል፤ ሁሉን የሚገዛ ጌታ፡- እኔም እቀበላችኋለሁ፣ ለእናንተም አባት እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ ይላል” (2ኛ ቆሮ. 6፡ 17፣ 18)፡፡ በፖለቲካዊ ጥያቄዎች ውስጥ ድምጽ መስጠትን በተመለከተ ያሉአችሁ አመለካከቶች ምንም ቢሆኑ በብዕር ወይም በጽሁፍ ማሳወቅ የለባችሁም፡፡ ከሶስተኛው መልአክ መልእክት ጋር ግንኙነት በሌላቸው ጥያቄዎች ላይ ሕዝባችን ዝም ማለት አለበት፡፡ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ የሚያስፈልገው ሕዝብ ካለ ያ ሕዝብ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች ናቸው፡፡ አስደናቂ የሆኑ ሥራዎችና ዕቅዶች ነበሩ፡፡ አንዳንድ ወንዶችን እና ሴቶችን የሆነ ነገርን ለማወጅ ወይም ከሆነ ነገር ጋር ለመታሰር የሚቃጠል ፍላጎት ተቆጣጥሮ ነበር፡፡ ነገሩ ምን እንደሆነ ግን አያውቁትም፡፡ በብዙ ጉዳዮች ላይ የክርስቶስ ዝምታ እውነተኛ አንደበተ ርቱዕነት ነበር፡፡ Amh2SM 336.1

    ወንድሞቼ ሆይ፣ ማናችሁም ብትሆኑ የፖለቲካ ምርጫዎቻችሁን በእኛ የሕትመት ውጤቶች ላይ እንድታሳትሙ ወይም ሕዝብ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት በሚሰበሰብበት ጊዜ በጉባኤ ውስጥ ስለ ፖለቲካ ምርጫዎቻችሁ እንድትናገሩ ምንም ዓይነት ሀላፊነት እንዳልተሰጣችሁ አታስታውሱምን?Amh2SM 336.2

    እንደ ሕዝብ ከፖለቲካ ጉዳዮች ጋር መቀላቀል የለብንም፡፡ በፖለቲካ ጠብ ውስጥ ከማያምኑት ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፣ ወይም ከእነርሱ ጋር ግንኙነት በመፍጠር አትጠመዱ የሚለውን የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰሙ ሁሉ መልካም ያደርጋሉ፡፡ አብረው መቆምና መሥራት የሚችሉበት ከአደጋ ነጻ የሆነ ቦታ የለም፡፡ ታማኝ የሆኑትና ያልሆኑት የሚገናኙበት ለሁለቱም አማካይ የሆነ ቦታ የለም፡፡ Amh2SM 336.3

    ከእግዚአብሔር ትዕዛዛት አንዲቷን የጣሰ ሕግን ሁሉ ተላልፏል፡፡ ድምጽ መስጠትህን ለራስህ አድርገው፡፡ አንተ የምታደርገውን ሁሉም እንዲያደርጉ መገፋፋት ሀላፊነትህ እንደሆነ አይሰማህ፡፡ Letter 4, 1898.Amh2SM 337.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents