Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ሚስቱን የፈታ ሰውን ለማግባት እያሰላሰለች ላለች ወጣት ሴት የተሰጠ ምክር

    (በዚህ አጋጣሚ ወንድም ኤል ለቤተሰቡ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚሰጥ ለሚስቱ አባት መተማመኛ በመስጠት ሚስቱንና ቤተሰቡን ትቶ ወደ ሩቅ አገር ሄደ፡፡ ከጊዜ በኋላ ባለቤቴ ትቶኛል በማለት ሚስቱ የፍቺ ፈቃድ እንዲሰጣት ከሰሰች፡፡ የፍቺ ፈቃድ ከማግኘታቸው በፊት ባልየው ይህ ምክር ከተሰጣት ወጣት ጋር ፍቅር ጀምሮ ነበር፡፡ አዘጋጆች፡፡)

    ነገሩን ቀስቃሽ የሆነ አካል እንደገና የማግባት መብት የለውም፡፡ ከኤል ጋር በተገናኘ ሁኔታ ስለአንቺ እያሰላሰልኩ የነበርኩ ሲሆን ከዚህ በፊት ከሰጠሁሽ ሌላ የምሰጥሽ ምክር የለኝም፡፡ ኤልን የማግባት የሞራል መብት የለሽም፣ እሱም አንቺን የማግባት የሞራል መብት የለውም፡፡ ሚስቱን እርምጃ እንድትወስድ በከፍተኛ ሁኔታ ካነሳሳት በኋላ ትቷታል፡፡ ሁለቱም በሕይወት እስካሉ ድረስ ሊወዳትና ሊንከባከባት በእግዚአብሔር ፊት መሃላ የፈጸመላትን ሚስቱን ትቷል፡፡ የፍቺ ፈቃድ ከማግኘቷ በፊት፣ ገና የሕግ ሚስቱ ሆና ሳለች፣ ለሶስት አመታት ተዋት፤ ከዚያም በልቡ ከተዋት በኋላ ለአንቺ ያለውን ፍቅር ገለጸ፡፡ ሁለት ልጆች ከወለደችለት ሚስቱ ጋር ሕጋዊ በሆነ መንገድ ባልተለያዩበት ሁኔታ በአንቺና ባለትዳር በሆነ ሰው መካከል በጉዳዩ ላይ በስፋት ድርድር ተደርጓል፡፡ Amh2SM 340.3

    ሚስቱ ብትፈተው እንኳን አንቺና እሱ ጋብቻ እንድትፈጽሙ የሚፈቅድ ኢምንት ያህል ፈቃድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አላይም፡፡ የፍቺ ጥያቄ እንድታቀርብ ያነሳሳት እሱ ስለሆነ ይህን ውጤት ያስከተለው በአብዛኛው የእሱ ተግባር ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ እሱ በአንቺ ላይ ያለውን ፍላጎት የመፈጸም ሕጋዊ መብት እንዳለው ወይም አንቺ በእሱ ላይ ያለሽን ፍላጎት የመፈጸም ሕጋዊ መብት እንዳለሽ አድርጌ አላይም፡፡Amh2SM 341.1

    የዚህን ዓይነት ነገር ለአንድ አፍታ እንኳን በማሰብሽ እና ሚስቱንና ልጆቹን በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ የተወን ባለትዳር ሰው በማፍቀርሽ ተገርሜያለሁ፡፡ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ምክር እንድታገኚና በምን ዓይነት ስህተት ውስጥ እንደወደቅሽ ከእግዚአብሔር ሕግ እንዲያሳዩሽ ሀሳቦችሽንና እቅዶችሽን ሀላፊነት በሚሰማቸው ወንድሞቻችን ፊት እንድታስቀምጪ እመክርሻለሁ፡፡ መጋባት እንደምትችሉ በማሰባችሁ ብቻ ሁለታችሁም ሕግን ጥሳችኋል፡ በመጀመሪያ ይህ ሀሳብ ወደ አእምሮአችሁ እንደመጣ መቋቋም ነበረባችሁ፡፡ Letter 14, 1895.Amh2SM 341.2