Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    «ራሴን መቆጣጠርን አልተውም”

    ቀኑ ሰኔ 23 ቀን 1892 ዓ.ም ነበር፡፡ ሌላ ሌሊት አልፏል፡፡ ለሶስት ሰዓታት ብቻ አንቀላፍቻለሁ፡፡ የተለመደው ዓይነት ብዙ ሕመም አልነበረኝም፣ ነገር ግን እረፍት የለሽነትና መረበሽ ነበረብኝ፡፡ ለተወሰነ ጊዜ ለማንቀላፋት እየሞከርኩ ነቅቼ ከተጋደምኩ በኋላ ለማንቀላፋት የማደርገውን ጥረት ትቼ ትኩረቴን በሙሉ ጌታን ወደመፈለግ አዞርኩ፡፡ «ጠይቁ ይሰጣችኋል፣ እሹ ታገኙማላችሁ፣ አንኳኩ ይከፈትላችሁማል” (ማቴ. 7፡ 7) የሚለው ተስፋ ለእኔ እጅግ የከበራ ነበር፡፡ ጌታ ኢየሱስ ብቻ ሊሰጥ ስለሚችለው መጽናናትና ሰላም ከልቤ ጸለይኩ፡፡ ሕመም እያሰቃየኝ ሳለ ራሴን መቆጣጠር እንዳያቅተኝ የጌታን በረከት እሻለሁ፡፡ ለአንድ አፍታ እንኳን በራስ ለመተማመን አልደፍርም፡፡Amh2SM 235.3

    ጴጥሮስ ለአንድ አፍታ ዓይኖቹን ከክርስቶስ ባነሳ ጊዜ ወዲያውኑ መስመጥ ጀመረ፡፡ የነበረበትን አደጋ በመገንዘብ ጌታ ሆይ ልጠፋ ነውና አድነኝ ብሎ በመጮህ ዓይኖቹንና ድምጹን ወደ ኢየሱስ ባነሳ ጊዜ እየጠፉ ያሉትን ለማዳን ሁልጊዜ ዝግጁ የሆነ እጅ ያዘውና አዳነው፡፡Amh2SM 235.4

    በየቀኑ እቤቴ ውስጥ ሰላምን መሻትና መከተል አለብኝ፡፡…ምንም እንኳን አካል እየተሰቃየ ቢሆንም፣ የነርቭ ሥርዓትም ቢደክምም ተበሳጭተን ለመናገር ወይም ማግኘት የሚገባንን ትኩረት እያገኘን አይደለንም የማለት ነጻነት አለን ብለን ማሰብ የለብንም፡፡ ለትዕግሥት የለሽነት ቦታ ስንሰጥ የእግዚአብሔርን መንፈስ ከልብ ውስጥ በማባረር ለሰይጣን ባሕርያት ቦታ እንሰጣለን፡፡Amh2SM 235.5

    ለራስ ወዳድነት፣ ክፉ ለማሰብ እና ክፉ ለመናገር ሰበቦችን ስናዘጋጅ ነፍስን ክፉ ነገር እያስተማርን ስለሆነ ይህንን ማድረጋችንን ከቀጠልን ለፈተና መሸነፍን የሚያስከትል ልምድ ይሆናል፡፡ ያኔ በሰይጣን ግዛት ሆነን የተሸነፍን ደካማ እና ድፍረት የከደን እንሆናለን፡፡ Amh2SM 236.1

    በራሳችን ከተማመንን በእርግጠኝነት እንወድቃለን፡፡ ክርስቶስ እንዲህ ብሏል፣ «በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ፡፡ ቅርንጫፍ በወይን ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም” (ዮሐ. 15፡ 4)፡፡ Amh2SM 236.2

    የምናፈራው ፍሬ ምንድን ነው? «የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ እምነት፣ የዋህነት፣ ራስን መግዛት ነው፡፡ እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም” (ገላ. 5፡ 22፣ 23)፡፡ Amh2SM 236.3

    በእነዚህ ነገሮች ላይ በጥልቀት ባሰላሰልኩ መጠን ነፍስን በእግዚአብሔር ፍቅር ለማቆየት ችላ የማለት ኃጢአት የበለጠ በጥልቀት እየተሰማኝ መጣ፡፡ እኛ ካልተባበርን በስተቀር ጌታ ምንም ነገር አያደርግም፡፡ ክርስቶስ፡- አባት ሆይ፣ በስምህ ጠብቃቸው ባለ ጊዜ በእግዚአብሔር ፍቅርና እምነት ራሳችንን መጠበቅን ችላ ማለት አለብን ማለቱ አልነበረም፡፡ ለእግዚአብሔር ሕያዋን ሆነን፣ ከክርስቶስ ጋር ሕያው ሕብረት በመፍጠር፣ ኢየሱስን በመመልከት ያለማቋረጥ የበለጠ ጥንካሬ በማግኘት በተስፋዎቹ እንታመናለን፡፡ አዳኝን በመመልከት ወደ እርሱ አምሳያነት የተለወጠ ሰውን ልብ ምን ሊለውጥ ይችላል? ወይም መታመኑን ምን ሊያናጋ ይችላል? እንደዚህ ዓይነቱ ሰው ለማይረቡ ነገሮች ነቅቶ ይጠብቃልን? ሀሳቡ ራስን ማዕከል ያደርጋልን? ትንንሽ ነገሮች ያለውን የአእምሮ ሰላም እንዲያጠፉ ይፈቅዳልን? ክርስቶስ በልቡ የሚኖር ሰው ለመደሰት ፈቃደኛ ነው፡፡ ክፉ አያስብም፣ ክርስቶስ የሞተለትን እያንዳንዱን ነፍስ እንደሚያውቅና ትክክለኛ ዋጋ እንደሚሰጥ ባለው ማረጋገጫ የረካ ነው፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ «ሰውን ከጥሩ ወርቅ ይልቅ የከበረ አደርገዋለሁ፣ ሰውም ከኦፊር ወርቅ ይልቅ የከበረ ይሆናል» (ኢሳ. 13፡ 12)፡፡ ይህ የነፍስን ናፍቆት ያርካ፣ እኛንም እግዚአብሔር ይቅር ስላለን ሌሎችን ይቅር ለማለት እጅግ የተዘጋጀን ጥንቁቆችና ከክፉ የተጠበቅን ያድርገን፡፡ Amh2SM 236.4

    የሕይወት ደስታ የተሰራው ከትናንሽ ነገሮች ነው፡፡ እውነተኛ የሆነ ክርስቶስን መሰል ትህትና እያንዳንዱ ሰው ሊለማመደው የሚችል ነገር ነው፡፡ አሸናፊዎች እንድንሆን የሚረዳን ግሩም የሆኑ መክሊቶች ባለቤት መሆን ሳይሆን የየዕለቱን ተግባሮቻችንን በትጋት ማከናወን ነው፡፡ በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ አጋዥ የሆኑ ነገሮች የርህራሄ እይታ፣ ዝቅ ያለ መንፈስ፣ እርካታ ያለበት ባሕርይ፣ እና ሳያስመስሉ ስለ ሌሎች ደህንነት ከልብ መፈለግ ናቸው፡፡ የኢየሱስ ፍቅር ልብን ከሞላ ይህ ፍቅር በሕይወት ይገለጣል፡፡ ደስተኛ ለመሆን ወይም ደስ ለመሰኘት በትዕቢትና ራስ ወዳድነት ባለበት እምቢተኝነት የራሳችንን መንገድ የመከተል ውሳኔ አናንጸባርቅም፡፡ ብዙዎች ከሚገምቱት በላይ የአካል ጤንነት የሚደገፈው በልብ ጤናማነት ላይ ነው፡፡ Amh2SM 237.1

    አንድ ሰው እንደተናቀ፣ እና ችሎታው እንዲይዝ በሚፈቅደው ከፍ ያለ ቦታ እንዳልተቀመጠ በመገመት ራሱን እንደ ሰማዕት አድርጎ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ይህ ሰው ደስተኛ ላለመሆኑ ጥፋተኛው ማነው? አንድ ግልጽ የሆነ ነገር ቢኖር ጤናማ ያልሆነ የእርግማን ጠባይ ካለው አለኝ ከሚለው ችሎታው ይልቅ ከፍ ከፍ ሊያደርገው የሚችለው ደግነትና መልካም ባሕርይ መሆኑ ነው፡፡ --Manuscript 19, 1892.Amh2SM 237.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents