Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለዛሬ ያለው መልእክት

    ዛሬ ለሕዝብ ማድረስ ያለብን መልእክት እንደ ዮሐንስ መልእክት ቀጥተኛ መሆን አለበት፡፡ ነገሥታትን ለኃጢአታቸው ዘለፋቸው፡፡ ሄሮድስን ዝሙት ስለፈጸመ ገሰጸው፡፡ ሕይወቱ በአደጋ ላይ ቢሆንም እውነትን በከናፍሩ ላይ አላጠወለገም፡፡ በዚህ ዘመን ያለው የእኛ ሥራም እንደዚያው በታማኝነት መፈጸም አለበት፡፡ በዚህ ዘመን ያሉ የምድር ኗሪዎች በጥፋት ውኃ ዘመን በምድር ላይ በኖሩ ሰዎች ተመስለዋል፡፡ በቀድሞ ዘመን በምድር ላይ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ኃጢአት በግልጽ እንዲህ ተብሎ ተገልጾአል፡- «እግዚአብሔርም የሰው ክፋት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደ ሆነ አየ» (ዘፍ.6፡5)፡፡ ሀሳባቸው ደስታ መፈለግና ፍላጎታቸውን መፈጸም ብቻ የሆኑ ሰዎችን መመልከት ለእግዚአብሔር አድካሚ ሆነበት፡፡ የፈጠራቸውን የእግዚአብሔርን ምክር አልፈለጉም፣ የእርሱን ፈቃድ ለማድረግም ግድ አልነበራቸውም፡፡ ሁልጊዜ የልባቸውን ሀሳብ ስለተከተሉ የእግዚአብሔር ተግሳጽ በላያቸው ነበር፤ በምድር ላይ ብጥብጥ ነበር፡፡ «እግዚአብሔርም ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፥ በልቡም አዘነ” «እግዚአብሔርም ምድርን አየ፥ እነሆም ተበላሸች ሥጋን የለበሰ ሁሉ በምድር ላይ መንገዱን አበላሽቶ ነበርና፡፡ እግዚአብሔርም ኖኅን አለው፦ የሥጋ ሁሉ ፍጻሜ በፊቴ ደርሶአል ከእነርሱ የተነሣ ምድር በግፍ ተሞልታለችና እኔም እነሆ ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ” (ዘፍ. 6፡6፣12፣13)፡፡. . . {2SM 151.1}Amh2SM 151.1

    በዚህ የምድር ታሪክ ወቅት መፈጸም ያለባቸው ልዩ ተግባራትና መሰጠት ያለባቸው ልዩ ተግሳፆች አሉ፡፡ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያኑን ያለ ተግሳጽና ያለ ማስጠንቀቂያ አይተውም፡፡ ኃጢአት ተወዳጅ ሆኗል፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር እይታ የሚያበሳጭ ነው፡፡ ኃጢአቶች ተሸፋፍነዋል፣ ተድበስብሰዋል፣ ምክንያትም ተሰጥቷቸዋል፤ የሀሰት ንድፈ ሀሳቦችንና አስተያየቶችን እያመጡ የእግዚአብሔርን ሕዝብ አእምሮ ግራ እያጋቡ ላሉና ትክክለኛ መርሆዎችን በተመለከተ ስሜቶቻቸውን ሙት እያደረጉ ላሉ ሰዎች የህብረት ቀኝ እጅ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ከዚህ የተነሳ ህሊና የተሰጡ ምክሮችንና ተግሳፆችን የማይሰማ ሆኗል፡፡ ለንስሃ እንዲጠራ የተሰጠ ብርሃን የሰብአዊ እቅዶችና ፈጠራዎች ባመጡት አለማመንና ተቃውሞዎች ደመና ውስጥ ጠፍቷል፡፡ {2SM 151.2}Amh2SM 151.2

    እግዚአብሔር የሚፈልገው ሕያው ቅንነት ነው፡፡ አገልጋዮች ከመጻሕፍት የተማሩት ትምህርት ጥቂት ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን በመክሊቶቻቸው ማድረግ የሚችሉትን ቢያደርጉ፣ እንደተሰጣቸው እድል ቢሰሩ፣ ቃሎቻቸውን እጅግ ግልጽና ቀላል በሆነ ቋንቋ ቢያለብሱ፣ በጥንቃቄና ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ ትሁታን ሰዎች ቢሆኑ፣ ሰማያዊ ጥበብን በመሻት፣ በአንድ ገዥ በሆነ ውስጣዊ ስሜት፣ ያውም ክርስቶስን በመውደድና እርሱ የሞተላቸውን ነፍሳት በመውደድ ስሜት በመነሳሳት ከልባቸው ለእግዚአብሔር ቢሰሩ ከፍተኛ የሆነ ችሎታና መክሊቶች ባሏቸው ሰዎች እንኳን ይሰማሉ፡፡ እነርሱ በሚያቀርቡአቸው እውነቶች ቀላልነት ውበት ይኖራል፡፡ ክርስቶስ እስካሁን ዓለም ካወቃቸው መምህራን ሁሉ የሚበልጥ መምህር ነው፡፡ {2SM 152.1}Amh2SM 152.1

    ዮሐንስ በአይሁድ መምህራን ትምህርት ቤት አልተማረም፡፡ ሆኖም ነገሥታትና መሳፍንት፣ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን፣ የሮም ወታደሮችና ባለሥልጣናት፣ በቤተ መንግሥት ሥነ ምግባር የሰለጠኑ፣ አታላይ፣ ሂሳብ የሚያሰሉ ቀራጮች እና ዓለም ያወቃቸው ሰዎች፣ ቃሎቹን ሰሙ፡፡ ግልጽ የሆኑ አረፍተ ነገሮች አሳማኝ ስለነበሩ ኃጢአተኛነታቸውን አመኑ፡፡ ከዚህ የተነሳ «ምን እናድርግ?» (ሉቃስ 3፡14) ብለው ጠየቁ፡፡ . . . {2SM 152.2}Amh2SM 152.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents