Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሁለት ዓይነት የቤተ መቅደስ ማንጻቶች - ሁለት ከባቢሎን የመውጣት ጥሪዎች

    የእውነትን አርማ አጥብቃችሁ በመያዝ የእግዚአብሔርን ሕግ ስታውጁ ሳለ የኢየሱስ ኃይማኖት ከእግዚአብሔር ትዕዛዛት ጋር የተገናኘ መሆኑን እያንዳንዷ ነፍስ ማስታወስ አለባት፡፡ ሶስተኛው መልአክ በታላቅ ድምጽ እየጮኸ በሰማይ መካከል እየበረረ እንደሆነ ተገልጾአል፣ «የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የሚጠብቁና የኢየሱስ እምነት ያላቸው ከዚህ ናቸው” (ራዕይ 14፡ 12)፡፡ የመጀመሪያው፣ የሁለተኛውና የሶስተኛው መላእክት መልእክቶች የተገናኙ ናቸው፡፡ ለእኛ ትልቅ ዋጋ ያላቸውና ከኃይማኖት ዓለም እንዲህ ያለ ኃይለኛ ተቃውሞ የቀሰቀሰው የእነዚህ ታላላቅ መልእክቶች ያለና ለዘላለም የሚኖር እውነት ማስረጃዎች ሊጠፉ አይችሉም፡፡ የእግዚአብሔር ቅሬታ ሕዝብ የእነዚህን መልእክቶች ጥቅም፣ ጊዜና ቦታ እንዳያውቅ ሰይጣን በእነዚህ መልእክቶች ዙሪያ ገሃነማዊ ጥላውን ለመጣል ያለማቋረጥ እየፈለገ ነው፤ ነገር ግን ዘመኑ እስካለ ድረስ ይኖራሉ፣ በኃይማኖታዊ ልምምዳችንም ላይ ተጽእኖአቸውን ያሳርፋሉ፡፡ {2SM 117.2}Amh2SM 117.2

    በሺሆች በሚቆጠሩ ልቦች ውስጥ የተግባር ምንጮችን እንቅስቃሴ እንዲኖራቸው በማድረግ፣ የትምህርት ተቋማት፣ የማተሚያ ቤቶችና የጤና ተቋማት እንዲኖሩ በማድረግ የእነዚህ መልእክቶች ተጽእኖ እየጠለቀና እየሰፋ በመሄድ ላይ ይገኛል፤ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ክርስቶስ በኃይልና በታላቅ ክብር እየመጣ መሆኑን የሚገልጸውን ማስጠንቀቂያ ለምድር ኗሪዎች ለማስተላለፍ በሰማይ መካከል እየበረሩ ካሉት ከመጀመሪያው፣ ከሁለተኛውና ከሶስተኛው መላእክት ጋር እንድንተባበር ለማድረግ እግዚአብሔር የሚጠቀምባቸው መሳሪያዎች ናቸው፡፡ {2SM 117.3}Amh2SM 117.3

    ነቢዩ እንዲህ ይላል፣ «ከዚህ በኋላ ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፣ ከክብሩም የተነሳ ምድር በራች፡፡ በብርቱም ድምጽ፡- ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፣ ወደቀች፣ የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች” (ረቀዕይ 18፡ 1፣ 2)፡፡ ይህ በሁለተኛው መልአክ ከተሰጠው መልእክት ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ባቢሎን የወደቀችው፣ «አህዛብን ሁሉ ከዝሙትዋ ጽዋ ወይን ጠጅ» ስላጠጣች ነው (ራዕይ 14፡ 8)፡፡ ወይን ምንድን ነው? የሀሰት አስተምህሮዋ ነው፡፡ በአራተኛው ትዕዛዝ ሰንበት ፋንታ ለዓለም የውሸት ሰንበት ሰጥታለች፤ ሰይጣን በመጀመሪያ ለሄዋን በኤደን ገነት ውስጥ የነገረውን ውሸት፣ ነፍስ በተፈጥሮ የማትሞት መሆንዋን ደግማለች፡፡ «የሰው ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማረች” (ማቴ. 15፡ 9) ብዙ አይነት ስህተቶችን በስፋት አሰራጭታለች፡፡ {2SM 118.1}Amh2SM 118.1

    ኢየሱስ በሕዝብ ፊት አገልግሎቱን በጀመረ ጊዜ ቅድስናን ከሚያረክሱ ነገሮች ቤተ መቅደሱን አነጻ፡፡ ከአገልግሎቱ የመጨረሻ ተግባራት መካከል ሁለተኛው የቤተ መቅደስ ማንጻት ይገኝበታል፡፡ እንዲሁም ዓለምን ለማስጠንቀቅ በሚደረገው የመጨረሻ ሥራ ለቤተ ክርስቲያናት ሁለት ግልጽ የሆኑ ጥሪዎች ተደርገዋል፡፡ የሁለተኛው መልአክ መልእክት «አህዛብን ሁሉ የዝሙትዋን ቁጣ ወይን ጠጅ ያጠጣች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፣ ወደቀች» ይላል (ራዕይ 14፡ 8)፡፡ በሶስተኛው መልአክ መልእክት ከፍ ባለ ጩኸት ከሰማይ እንዲህ የሚል ድምጽ ተሰማ፣ «ሕዝቤ ሆይ፣ በኃጢአቷ እንዳትተባበሩ ከመቅሰፍቷም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤ ኃጢአትዋ እስከ ሰማይ ድረስ ደርሷልና፣ እግዚአብሔርም አመጻዋን አሰበ” (ራዕይ 18፡ 4፣ 5)፡፡ --The Review and Herald, Dec. 6, 1892. {2SM 118.2}Amh2SM 118.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents