Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ሁሉም በክርስቶስ አንድ ናቸው

    ከሰብአዊ ቤተሰብ ውስጥ ማናቸውም ቢሆኑ ራሳቸውን ለክርስቶስ ቢሰጡ፣ ማናቸውም ቢሆኑ እውነትን ቢሰሙና ቢታዘዙ፣ የአንድ ቤተሰብ ልጆች ይሆናሉ፡፡ ሞኞችና ጠቢባን፣ ሐብታምና ደሃ፣ አህዛብና ባሪያ፣ ነጭ ወይም ጥቁር ቢሆን ኢየሱስ የነፍሳቸውን ዋጋ ከፍሎላቸዋል፡፡ በእርሱ ካመኑ የሚያነፃው ደሙ በእነርሱ ላይ ይደረግላቸዋል፡፡ በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ ከነጭ ሰው ስም አጠገብ የጥቁር ሰው ስም ተጽፏል፡፡ ሁሉም በክርስቶስ አንድ ናቸው፡፡ ትውልድ፣ ቦታ፣ ዜግነት ወይም ቀለም ሰውን ከፍ ወይም ዝቅ ሊያደርግ አይችልም፡፡ የሰውን ማንነት የሚወስነው ባሕርይ ነው፡፡ ቀይ ሰው (የአሜሪካ ሕንድ)፣ ቻይናዊ ወይም አፍሪካዊ በመታዘዝና በእምነት ልቡን ለእግዚአብሔር ከሰጠ ከቆዳ ቀለሙ የተነሳ የክርስቶስ ፍቅር አይቀንስበትም፡፡ እጅግ የተወደድክ ወንድሜ ብሎ ይጠራዋል፡፡ Manuscript 6, 1891.Amh2SM 342.4