Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ስሜት ማስተዋልን መቆጣጠር የለበትም

    ጽንፈኛ በሆነ ትርጉሙ ተቀባይነት ያገኘ እና የግርግር ፀባይ ባላቸው ሰዎች ሥራ ላይ የዋለ ስህተት ከብዙ እውነት ጋር ተቀላቅሏል፡፡ ስለዚህ ወግ አጥባቂነት ሥራውን ወደ ፍጻሜ ለማምጣት በደንብ ቁጥጥር የተደረገባቸውን፣ በደንብ ሥነ ሥርዓትን የጠበቁትን፣ ሰማይ ያዘዛቸውን ጥረቶች ቦታ ይወስዳል፡፡ . . . {2SM 17.2}Amh2SM 17.2

    ያለው አደጋ ሚዛናዊ ያልሆኑ አእምሮዎች ወደ ወግ አጥባቂነት የመመራት ብቻ ሳይሆን አታላይ ሰዎች ግርግሩን የራስ ወዳድነት ዓለማዎቻቸውን ለማስፋፋት መጠቀማቸው ነው፡፡. . . {2SM 17.3}Amh2SM 17.3

    ከክርስቶስ ቀድሞ ከመሮጥ ይልቅ መሪያቸውን እንዲከተሉ ለወንድሞቻችን ማስጠንቀቂያ አለኝ፡፡ በእነዚህ ወቅቶች በዘፈቀደ የሚሰራ ሥራ መኖር የለበትም፡፡ ሚዛናዊ ያልሆኑ አእምሮዎች አስደናቂ የሆነ ብርሃን ከእግዚአብሔር እንዳላቸው እንዲያስቡ የሚመሩአቸውን ጠንካራ አስተያየቶች ከመስጠት ተጠንቀቁ፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለሕዝብ የሚሆን መልእክት ያለው ሰው ፍጹም የሆነ ቁጥጥርን ሥራ ላይ ማዋል አለበት፡፡ የድፍረት መንገድ ከእምነት መንገድ አጠገብ እንዳለ ሁልጊዜ በአእምሮው ውስጥ መያዝ አለበት፡፡ . . . {2SM 17.4}Amh2SM 17.4

    አንድ ጊዜ ጠንካራ ስሜት በተረጋጋ ፍርድ ላይ የበላይነትን ካገኘ፣ ትክክለኛውን መንገድ በመጓዝ ላይ እንኳን ቢሆን ከመጠን ያለፈ ፍጥነት ይኖራል፡፡ ከመጠን ባለፈ ፍጥነት የሚጓዝ ሰው ከአንድ በሚበልጡ መንገዶች አደጋ ያጋጥመዋል፡፡ ከትክክለኛው ጎዳና ወደ ስህተት መንገድ ለመገንጠል ብዙ ጊዜ ላይወስድበት ይችላል፡፡ {2SM 17.5}Amh2SM 17.5

    ስሜት በአእምሮ ፍርድ ላይ የበላይነትን እንዲቀዳጅ ለአንድ ጊዜ እንኳን ሊፈቀድለት አይገባም፡፡ የተፈቀደ ነገር ከመጠን በላይ ሲሆን አደጋ አለው፣ ያልተፈቀደ ነገር ደግሞ በእርግጠኝነት ወደ ስህተት መንገዶች ይመራል፡፡ እያንዳንዱን ሀሳብና መርህ እና እያንዳንዱን የተሰጠ ውክልና ወደ ፊት በማንቀሳቀስ ረገድ እንደ ዓለት የፀና፣ በጥንቃቄ የተሞላ፣ ልባዊ የሆነ እና ማስተዋል ያለበት ሥራ ካልተሰራ በስተቀር ነፍሳት ይጠፋሉ፡፡ --Letter 6a, 1894. [for fuller context see pages 90-92.] {2SM 18.1}Amh2SM 18.1