Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሥራውን ስሩና የተሰጣችሁን ደሞዝ ተቀበሉ

    እያንዳንዱ ሰው እግዚአብሔር የሰጠውን ሥራ እንዲሰራ ይጠበቅበታል፡፡ በሆነ ሰው መደረግ ያለባቸውን ነገሮች በማድረግ፣ ጥቃቅን እድሎችን በማሻሻል፣ ትንንሽ አገልግሎቶችን ለመስጠት ፈቃደኛ መሆን አለብን፡፡ ያሉት የሥራ ዕድሎች እነዚህ ብቻ ከሆኑ አሁንም በታማኝነት መስራት አለብን፡፡ ምንም እንኳን ዝቅተኛም ቢሆን የተሰጠውን ሥራ ለመሥራት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ሰዓታትን፣ ቀናትን እና ሳምንታትን የሚያባክን ሰው ያለአግባብ ለባከነው ጊዜ ለእግዚአብሔር ምለሽ ለመስጠት ይጠራል፡፡ የሚፈልገውን ደሞዝ ማግኘት ስለማይችል ምንም መስራት እንደማይችል የሚሰማው ከሆነ ያ ቀን፣ ያ አንድ ቀን የጌታ መሆኑን ቆም ብሎ ያስብ፡፡ እርሱ የጌታ አገልጋይ ነው፡፡ ጊዜውን ማባከን የለበትም፡፡ «ያንን ጊዜ የሆነ ነገር በመስራት አሳልፍና ያገኘሁትን ሁሉ ለእግዚአብሔር ሥራ እሰጣለሁ፡፡ ምንም የማይሰራ ተብዬ አልቆጠርም» ብሎ ያስብ፡፡ Amh2SM 181.1

    ሰው ከሁሉ አብልጦ እግዚአብሔርን ሲወድና ባልንጀራውን እንደ ራሱ ሲወድ እርሱ ማድረግ የሚችለው ነገር ብዙ ወይም ጥቂት እያመጣ መሆኑን መጠየቁን አያቋርጥም፡፡ ሥራውን ሰርቶ የተሰጠውን ደሞዝ ይቀበላል፡፡ ማግኘት አለብኝ ብሎ የሚያስበውን ያህል ብዙ ገንዘብ መቁጠር ካልቻለ ሥራውን ያለመቀበልን መጥፎ ምሳሌ አያሳይም፡፡Amh2SM 181.2

    እግዚአብሔር የሰውን ባሕርይ የሚመዝነው እርሱን ከሚመስሉ ሰዎች ጋር ባለው ግንኙነት በሚከተላቸው መርሆዎች ነው፡፡ ተራ በሆኑ ግንኙነቶች ውስጥ የሚከተላቸው መርሆዎች ጉድለት ያለባቸው ከሆኑ እነዚሁ መርሆዎች ለእግዚአብሔር በሚሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥም ይመጣሉ፡፡ ክሮቹ በመላው መንፈሳዊ ሕይወቱ ውስጥ የተጠላለፉ ናቸው፡፡ ለራስህ አነስተኛ በሆነ ደሞዝ መስራት ክብርህን የሚነካ ሆኖ ከተሰማህ ለጌታ ሥራ፤ ገቢውን ወደ ጌታ ጎተራ አስገባ፡፡ በሕይወት ስላኖረህ ለእግዚአብሔር የምሥጋና ሥጦታ አድርገው፡፡ ነገር ግን በምንም ምክንያት ቢሆን ሥራ-ፈት አትሁን፡፡ -- Manuscript 156, 1897.Amh2SM 181.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents