Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሀብታችንን የት እያስቀመጥን ነን?

    የዓለም ታላቁ ጥናትና ፍላጎት መንፈሳዊ መልካምነትን ችላ በማለት ቁሳዊና ጊዜያዊ ጥቅምን ማግኘት ነው፡፡ አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አባላትም የሚያደርጉት ይህንኑ ነው፡፡ በመጨረሻ የሥራቸውን ዘገባ ለእግዚአብሔር እንዲሰጡ በሚጠሩበት ጊዜ የሚያፍሩ ብቻ ሳይሆኑ እውነተኛውን ሀብት ለይተው ባለማወቃቸውና ሀብት በሰማይ ባለመሰብሰባቸው ይገረማሉ፡፡ በዚህ ሕይወት ሀብታቸውን ላፈሰሱበት ትርፉን የሚያገኙበት ጊዜ እንደሚመጣ በማሰብ ልግስናቸውንና ስጦታዎቻቸውን ለእውነት ጠላቶች ሰጥተዋል፡፡ ሀብታቸውን ለምስጢር ማህበራት መስጠት ይችላሉ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ለሰብዓዊ ወኪሎች በአደራ በሰጠው ሥራ ውስጥ የገንዘብ እጥረት በሚያጋጥምበት ጊዜ ለመስጠት ፍላጎት አይኖራቸውም፣ እግዚአብሔር ለእነርሱ የሰጠውን ስጦታ ከግምት አያስገቡም፡፡ በዚህ ዓለም አምላክ ታውረዋል፡፡{2SM 134.2}Amh2SM 134.2

    እንዲህ ይላሉ፡- «ምንም ትርፍ ስላላገኘሁበት ለዚህ የንግድ ድርጅት የምሰጠው ምንም ነገር የለኝም፡፡ ለምስጢር ማህበሩ በመክፈል ለወደፊት እያስቀመጥኩ ነኝ፣ ከዚህም ባሻገር የወጪ ድርሻዬን ፍላጎቴን ለሚያሟላልኝ ነገር ማዋል አለብኝ፡፡ እነዚህን ደስታዎች መተው አልችልም፡፡ እነዚህን ያለማቋረጥ የሚደጋገሙ ጥያቄዎችን ለማሟላት እንድረዳ ቤተ ክርስቲያን ወደ እኔ የምትመለከተው ለምንድን ነው? የሆነ ጊዜ ከእርሱ ጥቅም አገኝበት ይሆናል ብዬ በመጠበቅ ‹ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህበት የምታጭድ ካልበተንህበትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት” (ማቴ. 25፡24፣25)፡፡ {2SM 134.3}Amh2SM 134.3

    ጌታ እንዲህ በማለት ይጠራናል፡- «ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤ ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና” (ማቴ. 6፡19-21)፡፡ {2SM 135.1}Amh2SM 135.1

    ብዙዎች ሀብታቸውን በእነዚህ የምስጢር ማህበራት እየሰበሰቡ ናቸው፣ ልባቸው መዝገባቸው ባለበት መሆኑን ማየት አንችልምን? የእውነት ማስረጃዎች ምንም ያህል ኃይለኛ ቢሆኑም፣ ትንሽ በትንሽ ብሩህነቱን እያጣ፣ ኃይሉን እያጣ ይሄድና ሰማይ ከአእምሮ እየደበዘዘ ይሄዳል፤ ምድራዊ ሀብትን በመሰብሰብ ይገኛሉ ተብለው ከሚጠበቁ ጥቅሞች ጋር ሲነጻጸር የዘላለማዊ ክብር ክብደት፣ ታዛዥ ለሆነ ሕይወት እግዚአብሔር የሚሰጠው ስጦታ ዋጋ ቢስ መስሎ ይታያል፡፡ ነፍሳት ለሕይወት እንጀራና ውኃ እየተጠሙ ናቸው፤ ነገር ግን ልቡ በዓለም ላይ ለሆነ ሰው ይህ ምኑ ነው? ብዙዎች በቃላቸው ባይሆንም በድርጊታቸው እንዲህ እያሉ ናቸው፣ «ዘላለማዊ የሆነውን ለማግኘት ስል በእነዚህ ምድራዊ መዝገቦች ላይ ያሉኝን ትርፎች እንዲያመልጡኝ መፍቀድ አልችልም፡፡ ወደ ፊት የሚመጣው ሕይወት ለመተማመን እስከማልችል ድረስ እጅግ የራቀ ነው፡፡ ምድራዊ ሀብትን እመርጣለሁ፣ የወደፊቱን ደግሞ የመጣውን እቀበላለሁ፡፡ እግዚአብሔር መልካምና መሃሪ ነው፡፡» ሀኬተኛ ባሪያ! ይህን መንገድ ከተከተልክ እድል ፈንታህ በእርግጠኝነት ከግብዞችና ከማያምኑት ጋር ይሆናል፡፡ የጭፈራ ክፍሉ፣ የእራቶቹ እና ዓለም ወዳድ የሆኑ ጓደኞች ማራኪነት የቤልሻጽር ግብዣ እንዳደረገው ሁሉ እግዚአብሔርን ወደ መርሳትና ስሙን ወደ አለማክበር መርተውሃል፡፡ {2SM 135.2}Amh2SM 135.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents