Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    “አላማርርም”

    ቀኑ ሀምሌ 6፣ 1892 ዓ.ም ነው፡፡ ለጌታዬ ፍርሃቶቼንና ግራ መጋባቶቼን ሁሉ መንገር ስለምችል እጅግ አመሰግነዋለሁ፡፡ በክንፎቹ ከለላ ሥር እንዳለሁ ይሰማኛል፡፡ አንድ ጊዜ ከሃዲ የሆነ ሰው እግዚአብሔርን የሚፈራን አንድ ወጣት እንዲህ ብሎ ጠየቀው፣ «አንተ የምታመልከው አምላክ ምን ያህል ትልቅ ነው?” ልጁ «የምድርን ስፋት በሙሉ መሸፈን እስከሚችል ድረስ ትልቅ ሲሆን በእያንዳንዱ የተቀደሰ ልብ ውስጥ ማደር እስከሚችል ድረስ ደግሞ ትንሽ ነው» ብሎ መለሰለት፡፡ Amh2SM 238.3

    ክቡር ኢየሱስ ሆይ፣ የአንተን ማዳን እናፍቃለሁ፡፡ «ዋሊያ ወደ ውኃ ምንጮች እንደሚናፍቅ፣ አቤቱ፣ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች» (መዝ. 42፡ 1)፡፡ የኢየሱስን የጠራ እይታ ለማግኘት እናፍቃለሁ፡፡ ስለ እንከን የለሽ ሕይወቱ ለማሰብ፣ የእርሱን ትምህርቶች ለማሰላሰል እወዳለሁ፡፡ «እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፣ እኔም አሳርፋችኋለሁ» (ማቴ. 11፡ 28) የሚሉትን ቃላት የደጋገምኳቸው ስንት ጊዜ ይሆን፡፡ Amh2SM 238.4

    አብዛኛውን ጊዜ አካሌ በሕመም ተሞልቷል፣ ነገር ግን በማማረር ክርስቲያን የሚባል ስም የማይገባኝ መሆን አልፈልግም፡፡ ይህ በሥቃይ ውስጥ የምማረው ትምህርት ለእግዚአብሔር ክብር እንደሚሆን እና ለጤንነት ምቹ ባልሆኑ ፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ ቀጣይነት ያለውን ሥራ እንዳይሰሩ ለሌሎች የማስጠንቀቂያ መንገድ እንደሚሆን ማረጋገጫ ተሰጥቶኛል፡፡ --Manuscript 19, 1892.Amh2SM 238.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents