Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለእግዚአብሔር ታማኝ የመሆን ጥያቄ

    ለእስራኤል ቅዱስ የሚያስጠሉ እጅግ ብዙ ነገሮች በዓለም እውቅና ተሰጥቷቸው ተቀባይነት አግኝተዋል፡፡ ለሔዋን በእግዚአብሔር ከተነገሯት ግልጽ የሆኑ ገደቦች መለየትና እንዳታደርግ የነገራትን ነገር ማድረግ እና አዳም የእሷን ምሳሌ መከተል በጣም ትንሽ ነገር ይመስላል፤ ነገር ግን ያ ነገር ሰዎች የእግዚአብሔርን የተገለጠ ፈቃድ ከመከተል ይልቅ የራሳቸውን ግምት እንዲከተሉ በማድረግ ነፍሳትን ለማጥፋት በታላቁ አታላይ የታቀደ ነበር፡፡ ስለዚህ በእነዚህ ሕብረቶች ውስጥ ሰዎችን አደጋ ከሌለባቸው መንገዶች በመለየት በእግዚአብሔር ላይ ወደማመጽና የጽድቅን ቅዱስ መስፈርቶች ችላ ወደማለት በመምራት ከሰይጣን ማታለያ ሥር የሚያደርጉ መርሆዎች ተይዘዋል፡፡ «ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉ ጸልዩም» (ማር. 14፡38) የሚለው አባባል በአዳኛችን ብዙ ጊዜ የተደጋገመ ትእዛዝ ነው፡፡ ክርስቶስ የራሱን የደም ካሣ የከፈለላቸውን ነፍሳት ሰይጣን በማጥመድ እንዳይሳካለት ንቁ፣ በትጋትና በጥንቃቄ ንቁ፡፡ {2SM 131.4}Amh2SM 131.4

    እግዚአብሔር ልጆቹ የሆናችሁትን እናንተን በመለኮታዊ ዓይን ሥር ቅዱስ የሆነ የጽድቅ መስፈርት እንድትቀበሉ ይጠራችኋል፡፡ የእርሱ ፍትህና እውነት በእያንዳንዱ ነፍስ ውስጥ መመስረት ያለባቸው መርሆዎች ናቸው፡፡ ለእግዚአብሔር ያለውን ታማኝነት የሚጠብቅ ሰው ለሰውም ታማኝ ይሆናል፡፡ እግዚአብሔርን በእውነት የሚወድ ማንም ሰው ቢሆን ለብር ወይም ለወርቅ፣ ጉቦ ወይም ክብር ለማግኘት ወይም ለማንኛውም ምድራዊ ጥቅም ሲል ነፍሱን ለፈተና አያጋልጥም፡፡ «ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ሰውስ ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?” (ማር. 8፡36፣37)፡፡ (Mark 8:36, 37). {2SM 132.1}Amh2SM 132.1

    ክርስቲያኖች እግዚአብሔር ከማይቆጣጠራቸው ከእነዚህ የምስጢር ስርዓቶች ጋር የሚያስተሳስራቸውን እያንዳንዱን ግንኙነት ማቋረጥ አለባቸው፡፡ በአንድ ጊዜ ለእነዚህ ድርጅቶችና ለእግዚአብሔር ታማኝ መሆን አይችሉም፡፡ ከእነዚህ አካሎች ጋር ያለው ግንኙነት መቋረጥ አለበት፤ አለበለዚያ ከእነርሱ ጋር የበለጠውን በቅርበት ከመቀላቀልህ የተነሳ ሙሉ በሙሉ ከእነርሱ ጋር አንድ ትሆንና እግዚአብሔርን ከሚወዱና ከሚፈሩ ሰዎች ራስህን ትለያለህ፡፡ የሚጠይቀው መስዋዕትነት ትልቅ ቢሆንም ክርስቲያን ለመንፈሳዊነቱ እንቅፋት የሚሆኑበትን ነገሮች ይተዋል፡፡ የነፍስን ዋና ፍላጎቶች ለአደጋ ከማጋለጥ ይልቅ ገንዘብን፣ ንብረትን እና ሕይወትን እንኳን ቢሆን ማጣት ይሻላል፡፡ {2SM 132.2}Amh2SM 132.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents