Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እግዚአብሔር በውጭ ከሚታየው ሥር ያለውን ያያል

    እነዚህ በእግዚአብሔር ፍቅርና ፍርሃት ቁጥጥር ሥር ያልሆኑት ማህበራት ለሰው እውነተኛና ቀና መሆን አይችሉም፡፡ አብዛኞቹ የንግድ ልውውጦቻቸው ፍትሃዊነትንና ትክክለኛነትን የሚቃረኑ ናቸው፡፡ ክፉን ለማየት በጣም ንጹህ የሆኑ ዓይኖች ያሉት ሰው በእነዚህ ማህበራት ውስጥ በሚደረጉ ብዙ ነገሮች ውስጥ አይካፈልም፣ ሊካፈልም አይችልም፡፡ እኔ ስለምናገረው እውነት የራሳችሁ ህሊና ይመሰክራል፡፡ እግዚአብሔር ለሰዎች የሰጣቸው መክሊት፣ ሙያና የመፍጠር ኃይል በእነዚህ ማህበራት ውስጥ ሰዎች በመሰሎቻቸው ላይ ማጭበርበርን በመፈጸማቸው ብዙ ጊዜ ወደ ጭካኔ፣ ኢፍትሃዊነትና ራስ ወዳድነት ተቀይሯል፡፡ {2SM 130.2}Amh2SM 130.2

    በርግጥ ይህ ሁሉ የተነፈገው በእነዚህ ማህበራት ውስጥ ባሉት አባላት ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ደስ ከሚሉና ማራኪ ገጽታ ካላቸው ሥር ያሉትን የምስጢር ሀሳቦችና የማህበሩን ትክክለኛ የሆነ አሰራር ይመለከታል፡፡ አንዳንዶቻቸው በአንዳንድ መልኩ የእግዚአብሔርን ቃል የድርጅታቸው መሰረት እንደሚያደርጉ ቢናገሩም ከጽድቅ መርሆዎች እጅግ ይርቃሉ፡፡ ከእነዚህ ሥርዓቶች አንዳንዶቹ እንዲገቡ የሚያስገድዷቸው ቃለ መሃላዎች የሥርዓቱ ምስጢሮች በሚወጡበት ጊዜ የሰውን ሕይወት ማጥፋትን የሚጠይቁ ናቸው፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች አባላቶቹ ጥፋተኞችን ከሚገባቸው ቅጣት ነጻ የማድረግ ቃል ኪዳንም ይገባሉ፡፡ የእነርሱን ሥርዓት የሚቃወሙትን በተመለከተ እንዲከተሉ የሚፈለግባቸው መንገድ በፍጹም ከእግዚአብሔር ሕግ ጋር የማይጣጣም ነው፡፡ {2SM 130.3}Amh2SM 130.3

    ብርታታችን፣ ጽድቃችንና ቅድስናችን የሆነውን እርሱን ሳንተው የእውነትን መንገድ መለወጥ አንችልም፣ ከትክክለኛ መርሆዎች መለየት አንችልም፡፡ ምንም ነገር በየትኛውም መልኩ ቢሆን ከሰዎች ጋር በሚኖረን ግንኙነትና ሽርክና ከእውነትና ከፍትህ ወደ ኋላ የሚመልሰን ከሆነ እንደማይጠቅመንና በከፍተኛ ደረጃ የእግዚአብሔርን ክብር ዝቅ እንደሚያደርግ ባለን እምነት ጸንተን መመስረት አለብን፡፡ እያንዳንዱ የማታለል አይነት ወይም የሚያሳምን ኃጢአት በእርሱ ዘንድ የተጠላ ነው፡፡ {2SM 130.4}Amh2SM 130.4

    በእነዚህ የምስጢር ማህበራት ሁሉ ውስጥ ከላይ እስከ ታች ማጭበርበር ስላለ ማንም ቢሆን ከእነርሱ ጋር ተቆራኝቶ በእግዚአብሔርና በሰማይ ፊት ነጻ ሰው መሆን አይችልም፡፡ የግብረገብ ተፈጥሮ እግዚአብሔር ኢፍትሃዊ ነው እስከሚለው ደረጃ ወደ ታች ይወርዳል፣ ይህ ደግሞ ከእርሱ ፈቃድና ከትዕዛዛቱ ጋር ተቃራኒ ነው፡፡ እግዚአብሔርን እወዳለሁ የሚል ሰው በእነዚህ ማህበራት ውስጥ ክብር ባላቸው ቦታዎች ሊቀመጥ ይችላል፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር ዓይኖች ፊት እንደ ክርስቲያን ክብሩን እያበላሸና ከጽድቅና ከእውነተኛ የቅድስና መርሆዎች እጅግ እየተለየ ነው፡፡ በኢየሱስ ደም የተገዛውን የእርሱን ኃይሎች እያበላሸ ነው፡፡ ነፍሱን ለከንቱ ነገር እየሸጠ ነው፡፡ {2SM 131.1}Amh2SM 131.1

    በእርሱ ቅዱስ ፍርዶች መገለጥ እግዚአብሔር እነዚህን ሕብረቶች ሁሉ ይሰብራል፤ ችሎት በሚሰየምበትና መጻሕፍት በሚገለጡበት ጊዜ የመላው ሕብረት ክርስቶስን አለመምሰል ይገለጣል፡፡ ከእነዚህ የምስጢር ማህበራት ጋር አንድነት ለመፍጠር የሚመርጡ ሰዎች እንደ ሒንዱዎች አማልክት ላሉ ነፍስን ለመባረክና ለማዳን ስሜትና ኃይል የለሽ ለሆኑ አማልክት እየታዘዙ ናቸው፡፡ {2SM 131.2}Amh2SM 131.2

    እነዚህ ማህበራት ከሰብዓዊ አመለካከት አንጻር ታላላቅ በረከቶች መስለው የሚታዩ አንዳንድ ጥቅሞችን ይሰጣሉ፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር ሚዛን ሲፈረዱ እንዲህ አይደለም፡፡ ከሚሰጡት ግልጽ ከሆኑ ጥቅሞች በስተጀርባ ሰይጣናዊ ወኪሎች ተደብቀዋል፡፡ ወደ ግምጃ ቤቱ የሚገባው ገቢ ትልቅ በሆነ ቁጥር ክፋቱም የበዛና የጠለቀ ነው፡፡ እነዚህን ማህበራት ባለፀጋ ያደረገው እግዚአብሔር የሌለበት ትርፍ በሁሉም አቋሞቹ ሲመረመር እርግማን መሆኑ ይታያል፡፡ ከእነዚህ ሕብረቶች አንጻር ኤሊፋዝ ለኢዮብ የተናገራቸው ቃላቶች እውነት ናቸው፡- «ሰነፍ ሰው ሥር ሰድዶ አየሁት፥ ድንገትም መኖሪያውን ረገምሁ» (ኢዮብ 5፡3)፡፡ እነርሱ የሰይጣን ወጥመዶች፣ ነፍሳትን ለማጥመድ የእርሱ መረብ ናቸው፡፡ {2SM 131.3}Amh2SM 131.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents