Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ለእሁድ ሕግ ችግር መዘጋጀት

    እግዚአብሔርን ከማያከብሩት ጋር የቀረበ ግንኙነት ለመፍጠር በምንገደድበት ቦታ ራሳችንን ማስቀመጥ የለብንም፡፡ …የእሁድ ጥበቃን በተመለከተ በቶሎ ችግር ሊመጣ ነው፡፡…Amh2SM 359.2

    የእሁድ ፓርቲ የውሸት ምክንያት በማቅረብ ራሱን እያጠናከረ ሲሆን ይህ ማለት ደግሞ የእግዚአብሔርን ሰንበት ለመጠበቅ ለሚወስኑት ጭቆና ነው፡፡ ራሳችንን ማስቀመጥ ያለብን የሰንበት ትዕዛዝን በሙላት መፈጸም በምንችልበት ቦታ ነው፡፡ ጌታ እንዲህ ይላል፣ «ስድስት ቀን ሥራ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው፡፡…በእርሱ ምንም ሥራ አትስሩ» (ዘጸ. 20፡ 9፣ 10)፡፡ ሰንበትን ለመጠበቅ ለእኛና ለልጆቻችን አስቸጋሪ በሚሆንበት ቦታ ራሳችንን እንዳናስቀምጥ መጠንቀቅ አለብን፡፡Amh2SM 359.3

    በእግዚአብሔር ፈቃድ ከከተሞች ራቅ ብለን ቦታዎችን መያዝ ከቻልን ይህን እንድናደርግ እግዚአብሔር ይፈልጋል፡፡ ከፊታችን አስቸጋሪ ጊዜያቶች አሉ፡፡ Manuscript 99, 1908.Amh2SM 359.4

    ለነገስታት የተሰጠው ኃይል ለመልካም ሕብረት መፈጠር ምክንያት የሚሆነው ኃላፊነት ላይ ያለው ግለሰብ በመለኮታዊ ትዕዛዝ ሥር ስለሆነ ነው፡፡ ይህ ኃይል ከክፉ ጋር ሕብረት ሲፈጥር፣ ሕብረት የፈጠረው ከሰይጣናዊ ወኪሎች ጋር ስለሆነ የጌታ ንብረት የሆኑትን ለማጥፋት ይሰራል፡፡ የፕሮቴስታንት ዓለም የእግዚአብሔር ሰንበት መቀመጥ በሚገባው ቦታ ላይ የጣዖት ሰንበትን ያቆሙ ሲሆን በጳጳሳዊው ሥርዓት ዱካ እየተራመዱ ናቸው፡፡ ከዚህ የተነሣ የእግዚአብሔር ሕዝብ ከከተሞች ወጥተው መሬትን በማረስ የራሳቸውን ምርት ወደሚያመርቱባቸው ራቅ ወዳሉ ገጠራማ ቦታዎች የመንቀሳቀስ አስፈላጊነትን እመለከታለሁ፡፡ በመሆኑም ልጆቻቸውን ቀለል ባሉ ጤናማ ልምዶች ማሳደግ ይችላሉ፡፡ እየመጣ ላለው አስጨናቂ ሁኔታ ሁሉንም ነገር ዝግጁ ለማድረግ የመቸኮል አስፈላጊነትን እመለከታለሁ፡፡ Letter 90, 1897.Amh2SM 359.5