Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 24—በእድሜ ለገፉት የተሰጡ ቃላት

    የከሰዓት በኋላ ፀሐይ፡- ለስላሳና ውጤታማ

    እውነተኛ የክርስቶስ አገልጋይ የማያቋርጥ መሻሸልን ማሳየት አለበት፡፡ የሕይወቱ የከሰዓት በኋላ ፀሐይ ከጧቱ ፀሐይ የበለጠ ለስላሳና ፍሬ የሚያፈራ ሊሆን ይችላል፡፡ ከምዕራብ ኮረብታዎች ባሻገር እስኪጠልቅ ድረስ በመጠንና በብሩህነት እየጨመረ ሊሄድ ይችላል፡፡ በአገልግሎት ውስጥ ያላችሁ ወንድሞቼ ሆይ፣ ባለመሥራት ከመዛግ ይልቅ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ከባድ ሥራ ከመሥራት የተነሣ መሞት ይሻላል፣ በጣም ይሻላል፡፡ ከችግሮች የተነሣ ተስፋ አትቁረጡ፤ ሳትማሩና መሻሸል ሳታሳዩ በመቀመጣችሁ አትርኩ፡፡ ያልተማሩትን ለማስተማርና የእግዚአብሔርን መንጋ ለመመገብ የሚሆን ትምህርትን ለማግኘት የእግዚአብሔርን ቃል ተግታችሁ መርምሩ፡፡ ከቃሉ መዝገብ አዲስና አሮጌ ነገሮችን ማምጣት እንድትችሉ ቃሉ ይሙላባችሁ፡፡Amh2SM 221.1

    ልምምዳችሁ የአሥር፣ የሃያ ወይም የሰላሳ ዓመት መሆን የለበትም፣ ነገር ግን ለእያንዳንዱ ሰው በወቅቱ ድርሻውን ምግብ መስጠት እንድትችሉ በየዕለቱ ሕያው ልምምድ ሊኖራችሁ ይገባል፡፡ ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ አትመልከቱ፡፡ ያለፈውን ልምምዳችሁን ለመንገር በማስታወስ ችሎታችሁ ለመጎተት በፍጹም መገደድ የለባችሁም፡፡ ለእናንተም ሆነ ለሌሎች ይህ ምን ያህል ይሆናል? ጥሩ የሆነውን ነገር ሁሉ ባለፈው ልምምዳችሁ ውስጥ ስታስቀምጡ በምታልፉበት መንገድ ላይ ብሩህና አዲስ ልምምድ ትፈልጋላችሁ፡፡ ከዚህ በፊት ባደረጋችሁት ነገር አትኩራሩ፣ ነገር ግን አሁን ማድረግ የምትችሉትን ነገር አሳዩ፡፡ ሥራዎቻችሁ እንጂ ቃላቶቻችሁ አያሞግሱአችሁ፡፡ «በእግዚአብሔር ውስጥ ተተክለዋል፣ በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ፡፡ ያን ጊዜ በለመለመ ሽምግልና ያፈራሉ፤ ደስተኞችም ሆነው ይኖራሉ፡፡ አምላኬ እግዚአብሔር እውነተኛ እንደሆነ ይነግራሉ፣ በእርሱም ዘንድ አመጻ የለም” (መዝ. 92፡ 13-15) የሚለውን የእግዚአብሔርን ተስፋ አረጋግጡ፡፡ ልባችሁንና አእምሮአችሁን ሁልጊዜ በማሰራት ወጣት አድርጉት፡፡ The Review and Herald, April 6, 1886.Amh2SM 221.2

    ራስን መግራትን ለማላላት ምክንያት የለም፡፡ በእምነት ውስጥ ለዓመታት የነበሩ ሰዎች ከዚህ በፊት መከራንና ችግርን መሸከም ይችሉ እንደነበረ እና ከዕድሜ የተነሣ የሚመጣ ድካም እየተጫናቸው ሲመጣና ከእድሜ ጋር ሥነ ሥርዓትን መከተልን የሚጠይቅ ነገር ሲመጣባቸው ከፍተኛ ጭንቀት እንደሚይዛቸው ሲናገሩ ሰምቻለሁ፡፡ ይህ ማለት ምን ማለት ነው? ኢየሱስ አዳኛቸው መሆኑን አቋርጧል ማለት ነውን? ስታረጁ ወይም ስትሸብቱ ያልተቀደሰ ስሜትን የማሳየት ዕድል አላችሁ ማለት ነውን? አስቡበት፡፡ ለዓለማዊ ነገሮች እንደምታደርጉት ሁሉ በዚህ ጉዳይም የማሰብ ኃይሎቻችሁን መጠቀም አለባችሁ፡፡ ራሳችሁን ክዳችሁ እግዚአብሔርን ማገልገልን የሕይወታችሁ የመጀመሪያ ሥራ ማድረግ አለባችሁ፡፡ ምንም ነገር ቢሆን ሰላማችሁን እንዲረብሽ መፍቀድ የለባችሁም፡፡ ይህንን ማድረግ አያስፈልግም፤ በመለኮታዊ ሕይወት የማያቋርጥ እድገት፣ የማያቋርጥ ለውጥ መኖር አለበት፡፡Amh2SM 222.1

    ክርስቶስ ሥሩ መሬት ላይ ያረፈውና ጫፉ ደግሞ ወደ ሰማይ የደረሰው፣ ያዕቆብ የተመለከተው መሰላል ነው፤ ስለዚህ ወደ ዘላለማዊው መንግሥት እስክትደርስ ድረስ በዚህ መሰላል ላይ ደረጃ በደረጃ መውጣት አለብህ፡፡ የበለጠ ሰይጣንን ለመምሰልና ሰብአዊ ተፈጥሮ ያለን ለመሆን ምክንያት የለም፡፡ እግዚአብሔር ከፊታችን ክርስቲያን መድረስ ያለበትን ከፍታ አስቀምጦልናል፣ «እርሱም በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በውስጣችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ፣ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፣ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፣ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ” (ኤፌ. 3፡ 16-19) የሚለው ነው፡፡ The Review and Herald, Oct. 1, 1889.Amh2SM 222.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents