Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 6

    እህቶቼ ሆይ፣ በመካከላችን የአለባበስ ተሃድሶ ያስፈልጋል፡፡ አሁን ባለው የሴቶች አለባበስ ላይ ብዙ ስህተቶች አሉ፡፡ ሴቶች የሚያጠብቁ ልብሶችን ወይም ከአሳ ነባሪ የተሰሩ አጥንቶችን መልበስ ወይም ወገባቸውን ማጥበቅ ጤናን የሚጎዳ ስለሆነ ኃጢአት ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች በልብ፣ በጉበት እና በሰንባዎች ላይ አስከፊ የሆነ ተጽዕኖ አላቸው፡፡ የመላው አካል ክፍሎች ጤንነት የሚደገፈው በመተንፈሻ አካሎች ጤናማ ተግባር ነው፡፡ በሺሆች የሚቆጠሩ ሴቶች ጤናማ እና ተፈጥሮአዊ የሆነ ቅርጻቸውን ጤናማ እና ተፈጥሮአዊ ያልሆነ ለማድረግ ጥረት ሲያደርጉ የሰውነት አቋማቸውን አበላሽተዋል፣ በራሳቸው ላይም የተለያዩ ዓይነት በሽታዎችን አምጥተዋል፡፡ በተፈጥሮአዊ አቀማመጥ ያልረኩ ናቸው፡፡ ተፈጥሮን ለማረም እና እነርሱ ለጨዋነት ተገቢ ናቸው ወዳሉአቸው ሀሳቦች ደረጃ ለማምጣት በሚያደርጉአቸው ልባዊ ጥረቶች ሥራዋን ይሰብሩና ያፈራርሷታል፡፡{2SM 473.1}Amh2SM 473.1

    ብዙ ሴቶች በወገባቸው ላይ ከባድ የሆኑ ጉርዶችን በማንጠልጠል ሆዳቸውንና ዳሌያቸውን ወደ ታች ይጎትታሉ፡፡ እነዚህ ጉርዶች ክብደትን ለመጠበቅ የተሰሩ አይደሉም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ከባድ ድሪቶ የተደረተባቸው ጉርዶች በፍጹም መለበስ የለባቸውም፡፡ የማያስፈልጉና ታላቅ ክፋት ያለባቸው ናቸው፡፡ የሴት ቀሚስ ከትከሻ ላይ መንጠልጠል አለበት፡፡ በአማኞች መካከል አለባበስን በተመለከተ በከፍተኛ ደረጃ መመሳሰል ቢኖር ኖሮ እግዚአብሔርን ያስደስት ነበር፡፡ አስቀድሞ በጓደኛሞች ተቀባይነት አግኝቶ የነበረው የአለባበስ ዓይነት ተገቢ ነው፡፡ ከእነርሱ መካከል ብዙዎቹ ወደ ኋላ አፈግፍገዋል፡፡ ምንም እንኳን የቀለም አንድ ወጥነትን ቢያቆዩም ኩራት ስለያዛቸው እና ያለመጠን ስላጋነኑት ልብሳቸው እጅግ ውድ ከሆነ ነገር የተሰራ ነበር፡፡ ያም ሆኖ ልሙጥ የሆኑ ቀለሞችን መምረጣቸውና መጠነኛ እና ደስ የሚል ዓይነት የልብስ አደረጃጀታቸው ክርስቲያኖች ሊቀዱት የሚገባ ነገር ነው፡፡ {2SM 473.2}Amh2SM 473.2

    የእሥራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ በዙሪያቸው ካሉ አህዛቦች እንዲለያቸው እና የእግዚአብሔር የተለዩ ሕዝብ መሆናቸውን ለማመልከት በልብሳቸው ጫፍ ላይ ቀለል ያለ ሰማያዊ ክር (ጥብጣብ) እንዲኖረው ታዘው ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝብ አሁን በልብሳቸው ላይ የተለየ ዓይነት ምልክት እንዲያደርጉ አልተጠየቁም፡፡ ነገር ግን በአዲስ ኪዳን ውስጥ የጥንቷ እሥራኤል እንደ ምሳሌ ተጠቅሳ እናገኛለን፡፡ እግዚአብሔር በጥንት ዘመን ለነበረው ሕዝቡ አለባበስን በተመለከተ እንደዚህ ዓይነቶቹን ቁርጥ ያሉ መመሪያዎች ከሰጠ በዚህ ዘመን ያለው የሕዝቡ አለባበስ ወደ እይታው አይቀርብምን? በአለባበሳቸው ከዓለም መለየት የለባቸውምን? የተለየ ርስቱ የሆኑት የእግዚአብሔር ሕዝብ በአለባበሳቸው እግዚአብሔርን ለማስከበር መሻት የለባቸውምን? ቀለል ያለ አለባበስን በመከተልና ምሳሌ በመሆን ኩራትን፣ ከንቱነትን እና ዓለማዊ ብክነትን፣ ደስታ ወዳድ የሆኑ ክርስቲያን ነን ባዮችን መዝለፍ የለባቸውምን? እግዚአብሔር ከሕዝቡ ይህን ይፈልጋል፡፡ ኩራት በቃሉ ውስጥ ተገስፆአል፡፡ {2SM 473.3}Amh2SM 473.3

    ነገር ግን ያለማቋረጥ ኩራትን እና አለባበስን ደጋግሞ የሚያነሳ ክፍል አለ፤ እነዚህ ለራሳቸው ልብስ ግድ የሌላቸው፣ መቆሸሽን እንደ መልካም ነገር አድርገው የሚያስቡ እና ሥርዓትና ለዛ የሌለው አለባበስ የሚለብሱ ናቸው፡፡ ብዙ ጊዜ ልብሳቸው በርሮ መጥቶ በሰውነታቸው ላይ ያረፈ ይመስላል፡፡ ልብሶቻቸው ቆሻሻ ናቸው፣ እንዲህም ሆኖ እንደ እነዚህ ዓይነቶቹ ስለ ኩራት ይናገራሉ፡፡ በተገቢ ሁኔታ መልበስን እና ንጽህናን ከኩራት ጋር ይመድቧቸዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች በተራራው ዙሪያ ከሲና የተነገረውን ሕግ ለመስማት ከተሰበሰቡት መካከል ቢሆኑ ኖሮ በሚያስፈራ ድምቀት የተሰጠውን ሕግ ለመስማት እንዲዘጋጁ «ልብሳቸውን ይጠቡ” የሚለውን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ስላልታዘዙ ከእሥራኤል ጉባኤ ይባረሩ ነበር፡፡ {2SM 474.1}Amh2SM 474.1

    በሲና ተራራ ላይ ያህዌ የተናገራቸው አሥርቱ ትዕዛዛት በተመሰቃቀሉ ቆሻሻ ልቦች ውስጥ መኖር አይችሉም፡፡ የጥንቶቹ እሥራኤላውያን የያህዌን ትዕዘዝ ካልታዘዙ እና ልብሳቸውን ካላጠቡ በስተቀር ያንን ቅዱስ ሕግ እወጃ መስማት ካልቻሉ በአካላቸው፣ በልብሳቸውና በቤታቸው ንጹህ ባልሆኑ ሰዎች ልብ ውስጥ ያ ቅዱስ ሕግ እንዴት ሊጻፍ ይችላል? ሊሆን አይችልም፡፡ ሙያቸው የሰማይን ያህል ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን የገለባን ያህል ዋጋ የለውም፡፡ ተጽዕኖአቸው ለማያምኑት የሚያስጠላ ነው፡፡ እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች ለዘላለም ከእግዚአብሔር ታማኝ ሕዝብ ውጭ ቢኖሩ ይሻላል፡፡ ክርስቲያን ነን በሚሉ እነዚህን በመሳሰሉ ሰዎች ምክንያት የእግዚአብሔር ቤት ክብሩን ያጣል፡፡ በሰንበት ቀን እግዚአብሔርን ለማምለክ የምሰበሰቡ ሁሉ፣ ከተቻለ፣ በአምልኮ ቤት ውስጥ ለመልበስ ንጹህ፣ በደንብ የሚገጥም እና ደስ የሚል ሙሉ ልብስ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ሰንበት የእግዚአብሔር የተቀደሰ እና የተከበረ ቀን ነው ብለው የሚናገሩ ሰዎች ሌላ ቅያሪ ልብስ ማግኘት ሲችሉ ሳምንቱን በሙሉ እርሻቸውን ሲያርሱ ለብሰው የሰነበቱትን ልብስ በሰንበት ቀን መልበስ ሰንበትን ማርከስና እግዚአብሔርን በቤቱ ውስጥ ማዋረድ ነው፡፡ የሰንበትን ጌታ እና የእግዚአብሔርን አምልኮ በሙሉ ልባቸው የሚያከብሩና የተገባቸው ሆነው ግን ልዋጭ ልብስ ማግኘት የማይችሉ ካሉ፣ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ንጹህና ገጣሚ የሆነ ልብስ ለብሰው እንዲመጡ፣ አቅም ያላቸው ሰዎች ለእነዚህ ግለሰቦች ለሰንበት ቀን የሚሆን ሙሉ ልብስ ይለግሱዋቸው፡፡ አለባበስን በተመለከተ ታላቅ የሆነ አንድ ወጥነት እግዚአብሔርን ያስደስተዋል፡፡ ገንዘባቸውን ውድ የሆኑ ልብሶችንና ተጨማሪ ነገሮችን ለመግዛት የሚያወጡ ሰዎች በጥቂት ራስን መካድ፣ በአለባበስ ትህትና እና በተለምዶ ለማያስፈልግ ነገር ወጪ ይሆን የነበረውን ገንዘብ እግዚአብሔር ለሚወዳቸው አንዳንድ ደሃ ወንድሞች/እህቶች ንጹህና ገጣሚ የሆነ ልብስ እንዲያገኙ በመርዳት ንፁህ ኃይማኖትን ማሳየት ይችላሉ፡፡ {2SM 474.2}Amh2SM 474.2

    አንዳንዶች የእግዚአብሔር ቃል የሚጠይቀውን ከዓለም መለየት ለመተግበር ስለ አለባበሳቸው ግድ የለሾች መሆን እንዳለባቸው የሚገልጸውን ሀሳብ ይቀበላሉ፡፡ በቅዱሳን ጉባኤ በመገኘት እግዚአብሔርን ለማምለክ በሰንበት ቀን ተራ የሆነ የፀሐይ ባርኔጣን እና ሳምንቱን በሙሉ ሲለብሱት የነበሩትን ልብስ በመልበሳቸው ዓለምን አትምሰሉ የሚለውን መርህ እየፈጸሙ እንደሆነ የሚያስብ የእህቶች ቡድን አለ፡፡ ክርስቲያኖች ነን ከሚሉ አንዳንድ ወንዶች መካከልም የአለባበስን ጉዳይ በተመሳሳይ ብርሃን የሚያዩ አሉ፡፡ አቧራ የቃመ፣ የቆሸሸ እና የተቀደደ ልብስን በተዝረከረከ መልክ ለብሰው በሰንበት ቀን ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር ይሰበሰባሉ፡፡ እነዚህ ክፍሎች ዓለም የሚያከብረውን ጓደኛ ለመገናኘት ቀጠሮ ካላቸውና በተለየ ሁኔታ በእሱ ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት ከፈለጉ ሊያገኙ የሚችሉትን ከሁሉ የተሻለ ልብስ ለብሰው በፊቱ ለመቅረብ ራሳቸውን ያስጨንቃሉ፣ ይህን የሚያደርጉት ፀጉራቸውን ሳያበጥሩ እና የተዝረከረከና ንጹህ ያልሆነ ልብስ ለብሰው በእሱ ፊት መቅረብ ስድብ ስለሚሆንበት ነው፡፡ ሆኖም እነዚሁ ግለሰቦች ታላቁን እግዚአብሔር ለማምለክ በሰንበት ቀን በሚገናኙበት ጊዜ የትኛውንም ዓይነት ልብስ ቢለብሱ ወይም ሁኔታቸው ምንም ቢሆን ምንም ችግር የለም ብለው ያስባሉ፡፡ የሰማይ መላእክት በሚገኙበት በልዑል መሰብሰቢያ ክፍል በሆነው በቤቱ ውስጥ ማንነታቸው እና አለባበሳቸው እንደሚያመለክተው አክብሮት በጎደለው ሁኔታ ይሰበሰባሉ፡፡ መላው አቀራረባቸው የእነዚህን ዓይነት ወንዶችና ሴቶች ባሕርይ ይወክላል፡፡ {2SM 475.1}Amh2SM 475.1

    የዚህ ክፍል ተወዳጅ መሪ ሀሳብ የአለባበስ ኩራት የሚል ነው፡፡ መልካም ምግባርን፣ ተገቢነትን እና ሥርዓትን እንደ ኩራት ይቆጥራሉ፡፡ እንደ እነዚህ የተሳሳቱ ነፍሳት አለባበስ ሁሉ ንግግራቸው፣ ተግባራቸው እና አያያዛቸውም ያው ነው፡፡ ግድ የለሾች ናቸው፣ ብዙ ጊዜ በቤቶቻቸው፣ በወንድሞች መካከል እና በዓለም ፊት ንግግራቸው የወረደ ነው፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ አንድ ግለሰብ የሚለብሰው ልብስና ልብሱ በግለሰቡ ላይ ያለው ቅንጅት የዚያ ወንድ ወይም ሴት መለኪያ መሆኑ ታውቋል፡፡ በአለባበሳቸው ግድ የለሾችና ንጹህ ያልሆኑት ሰዎች ንግግራቸውም የወረደ ነው፣ ስሜታቸውም ያልተሞረደ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ እንግዳ የሆነ ባሕርይን ማሳየትንና ሸካራነትን እንደ ትህትና ይቆጥሩታል፡፡ {2SM 475.2}Amh2SM 475.2

    ክርስቶስ ተከታዮቹን የምድር ጨው እና የዓለም ብርሃን አድርጎ አስቀምጧቸዋል፡፡ የክርስቲያኖች የማዳን ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ዓለም በራሱ መጥፎነት ይጠፋ ነበር፡፡ አስቀድሞ እንደተገለጸው ስለ ራሳቸውና ስለ አለባበሳቸው ግድ የለሽ የሆኑትን፣ በስራ ግንኙነታቸው ልል የሆኑትን፣ አለባበሳቸው እንደሚወክለው ያልሰለጠኑ፣ በባሕርያቸው ትህትና የሌላቸውና ሸካራዎች የሆኑትን እና የወረደ ንግግር የሚናገሩትን ክርስቲያን ነን ባይ ክፍሎች ተመልከቱ፡፡ እነዚህን አሳዛኝ ባሕርያትን የእውነተኛ ትህትናና ክርስቲያናዊ ሕይወት ምልክቶች አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ አዳኛችን በምድር ላይ ቢሆን ኖሮ እነዚህን ሰዎች የምድር ጨውና የዓለም ብርሐን ናቸው ብሎ ይጠቅሳል ብላችሁ ታስባላችሁን? በፍጹም አያደርግም፡፡ ክርስቲያኖች በንግግራቸው ከፍ ያሉ ናቸው፤ ምንም እንኳን የሞኝ ሽንገላን በፀጋ መቀበል ኃጢአት መሆኑን ቢያምኑም ገሮች፣ ቸሮች እና ለጋሶች ናቸው፡፡ ቃላቶቻቸው ልባዊ እና እውነተኛ ናቸው፡፡ ከወንድሞቻቸው እና ከዓለም ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ታማኝ ናቸው፡፡ በአለባበሳቸው ከመጠን ማለፍንና ታይታን ይሸሻሉ፤ ነገር ግን ልብሳቸው ንጹህ፣ ብልጭልጭ ያልሆነ፣ ጨዋነት የሚታይበት እና በግለሰቡ ላይ በስርዓትና በተገቢ ሁኔታ የተቀናጀ ይሆናል፡፡ አለባበስ ለቅዱስ ሰንበት እና ለእግዚአብሔር አምልኮ የተቀደሰ አክብሮትን መስጠት በሚችልበት ሁኔታ የተለየ ጥንቃቄ መደረግ አለበት፡፡ በዚህ ክፍል በሚመደቡትና በዓለም መካከል ያለው የመለያ መስመር መሳሳት እስከማይቻል ድረስ ግልጽ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ግድ የለሾች እና በልማዶቻቸው ቸልተኛ የነበሩት፣ አሁን ግን እውነትን የያዙ ወንዶችና ሴቶች፣ በአለባበሳቸው ንጽህናን፣ ሥርዓትን እና ጥሩ ምርጫን ለመከተል ከፍ የሚሉና በእውነት የሚቀደሱ ከሆነ የአማኞች ተጽዕኖ አስር እጥፍ ይሆናል፡፡ አምላካችን የስርዓት አምላክ ነው፤ እሱ በማንኛውም ደረጃ ቢሆን በሀሳብ መሰረቅ፣ በመቆሸሽ ወይም በኃጢአት አይደሰትም፡፡ {2SM 476.1}Amh2SM 476.1

    ክርስቲያኖች ከዓለም በተለየ ሁኔታ በመልበስ ራሳቸውን መላገጫ ለማድረግ መቸገር የለባቸውም፡፡ ነገር ግን ከእምነታቸውና ከተግባራቸው ጋር በሚስማማ መልኩ ትህትናን የሚያሳይና ጤናማ የሆነ አለባበስን ቢከተሉ ኖሮ ራሳቸውን ከፋሽን ይለዩ ነበር፤ ዓለምን ለመምሰል ብለው አለባበሳቸውን መቀየር የለባቸውም፡፡ ነገር ግን ዓለም በሙሉ ከእነርሱ ቢለይም ትክክለኛ ሆኖ ለመገኘት ከጥገኝነት ነጻነትን እና የግብረገብ ድፍረትን ማሳየት አለባቸው፡፡ ዓለም መጽሐፍ ቅዱስ ከሚያስተምረው አስተምህሮ ጋር የሚጣጣም ጨዋነትን የተላበሰ፣ ምቹ የሆነ፣ ለጤና የሚስማማ ዓይነት ልብስ ካመጣ የዚህን ዓይነት ልብስ መልበስ ከእግዚአብሔር ጋር ወይም ከዓለም ጋር ያለንን ግንኙነት አይለውጥም፡፡ ክርስቲያኖች ክርስቶስን መከተልና አለባበሳቸውን በተመለከተ ከእግዚአብሔር ጋር መስማማት አለባቸው፡፡ ከጽንፈኝነት መራቅ አለባቸው፡፡ ቢጨበጨብላቸው ወይም ተግሳጽ ቢደርስባቸው በትህትና ቀጥተኛውን መንገድ መከተል አለባቸው፣ ትክክል የሆነ ነገር የራሱ መልካምነት ስላለው ትክክል ከሆነው ነገር ጋር መጣበቅ አለባቸው፡፡ {2SM 476.2}Amh2SM 476.2

    ሴቶች እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ጤናን እና ምቾትን ባገናዘበ መልኩ ማልበስ አለባቸው፡፡ እጆቻቸውና እግሮቻቸው እንደ ወንዶች ሁሉ ሙቀት በሚያገኙበት መልክ መልበስ አለባቸው፡፡ ፋሽን ተከታይ ሴቶች የሚለብሷቸው ቀሚሶች ርዝመት ከብዙ ምክንያቶች የተነሳ የሚያስጠላ ነው፡፡ {2SM 477.1}Amh2SM 477.1

    1. ጎዳናውንና መንገዱን የሚጠርግ ርዝመት ያለውን ቀምስ መልበስ ብክነትና አለአስፈላጊ ድርጊት ነው፡፡ {2SM 477.2}Amh2SM 477.2

    2. የዚህ ዓይነት ርዝመት ያለው ልብስ ከሳር ላይ ጤዛን እና ከመንገድ ላይ የሚያቆሽሸውን ጭቃ ይሰበስባል፡፡ {2SM 477.3}Amh2SM 477.3

    3. ያ ልብስ በደንብ መከላከያ ያልተደረገላቸውንና በቀላሉ የሚሰማቸውን ቁርጭምጭሚቶች በተጨማለቀ ሁኔታ በሚነካበት ጊዜ በፍጥነት ስለሚያቀዘቅዛቸው ጉንፋንን እና የሰውነት ውስጥ ፈሳሽን የሚያመነጩ ዕጢዎችን እብጠት ከሚያስከትሉት ዋና ዋና ምክንያቶች አንዱ ሲሆን ጤንነትንና ሕይወትን ለአደጋ ያጋልጣል፡፡ {2SM 477.4}Amh2SM 477.4

    4. ከሚያስፈልገው በላይ የሆነው ርዝመት በዳሌ እና በወገብ ላይ ተጨማሪ ክብደት ይጨምራል፡፡ {2SM 477.5}Amh2SM 477.5

    5. መራመድን ይገድባል፣ ብዙ ጊዜ ደግሞ የሌሎችን መንገድም ይዘጋል፡፡ {2SM 477.6}Amh2SM 477.6

    የአለባበስ ተሃድሶ አራማጆች ተብለው በሚጠሩት ሰዎች ሥራ ላይ ሊውል የሚችል ሌላ የአለባበስ ዘዴ አለ፡፡ በተቻለ መጠን የተቃራኒ ፆታን አለባበስ ለመቅዳት ይሞክራሉ፡፡ ቆብን፣ ሱሪን፣ ሰደርያን፣ ኮትን እና ቦቲ ጫማን ያደርጋሉ፡፡ ለእነርሱ ከእነዚህ ውስጥ የመጨረሻው እጅግ ጠቃሚ የሆነ የልብስ ክፍል ነው፡፡ ይህንን የአለባበስ ዘዴ የሚቀበሉና የሚደግፉ ሰዎች የአለባበስ ተሃድሶን እጅግ ወደሚያስጠላ ርቀት እየወሰዱት ነው፡፡ ውጤቱም ግራ መጋባት ነው፡፡ የጤና ጥያቄን በተመለከተ ይህን አለባበስ የሚቀበሉ አንዳንድ ሰዎች በአጠቃላይ ሲታይ በአመለካከታቸው ትክክል ሊሆኑ ይችላሉ፣ የአለባበስን ጉዳይ ወደ ጽንፎች ባይወስዱት ኖሮ በሰፊው ጥሩ የሆነ ነገር ለመፈጸም መሳሪያ ይሆኑ ነበር፡፡ {2SM 477.7}Amh2SM 477.7

    በዚህ የአለባበስ ዘዴ እግዚአብሔር ያስቀመጠው ሥርዓት ተገልብጧል፣ ልዩ የሆኑ መመሪያዎቹም ችላ ተብለዋል፡፡ ዘዳግም 22፡ 5፡፡ «ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፣ ወንድም የሴት ልብስ አይልበስ፤ ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና፡፡” ይህን ዓይነት አለባበስ ሕዝቡ ተቀብሎ ሥራ ላይ እንዲያውል እግዚአብሔር አልፈቀደም፡፡ ይህ አለባበስ ጨዋነት የሌለበት እና የክርስቶስ ተከታዮች ነን ለሚሉ ጨዋ እና ትሁት ሴቶች በፍጹም የማይገጥም ነው፡፡ በወንድ እና በሴት ልብስ መካከል የተቀመጠው መለያ መወገድ አለበት የሚለውን ሀሳብ የደግፉ ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔርን ክልከላ ችላ ብለዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በአንዳንድ የአለባበስ ተሃድሶ አራማጆች የተያዘው ጽንፈኛ አቋም ተጽዕኖአቸውን ሽባ ያደርጋል፡፡ {2SM 477.8}Amh2SM 477.8

    በወንድና በሴት ልብስ መካከል ግልጽ የሆነ ልዩነት እንዲኖር ያቀደው እግዚአብሔር ነው፣ ይህንን በተመለከተ ግልጽ የሆኑ መመሪያዎችን መስጠት በቂ የሆነ ጠቀሜታ እንዳለውም አስቧል፡፡ ለዚህ ምክንያቱ በሁለቱም ፆታዎች ተመሳሳይ ልብስ ከተለበሰ ግራ መጋባትን ስለሚፈጥር እና ወንጀል በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር ስለሚያደርግ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በሕይወት ቢኖርና እግዚአብሔርን እንደሚፈሩ የሚናገሩ ሴቶች የዚህን ዓይነት ልብስ ለብሰው ቢያያቸው ኖሮ ይገስጻቸው ነበር፡፡ «እንዲሁም ሴቶች ደግሞ በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ፤ እግዚአብሔርን እንፈራለን ለሚሉት ሴቶች እንደሚገባ፣ መልካም በማድረግ እንጂ በሽሩባና በወርቅ ወይም በእንቁ ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሸለሙ፡፡” አብዛኞቹ ክርስቲያን ነን ባዮች የሐዋርያትን ትምህርት ችላ በማለት ወርቅን፣ ብርን፣ እንቁን እና ዋጋቸው እጅግ የከበሩ ልብሶችን ይለብሳሉ፡፡ {2SM 478.1}Amh2SM 478.1

    የእግዚአብሔር ታማኝ ሕዝብ የዓለም ብርሃንና የምድር ጨው ናቸው፡፡ ተጽዕኖአቸው ዋጋ እንዳለው ሁልጊዜ ማስታወስ አለባቸው፡፡ እጅግ ረዥም የነበረውን ልብስ እጅግ አጭር ወደሆነ ልብስ የሚቀይሩ ከሆነ በከፍተኛ ደረጃ የሚኖራቸውን ተጽዕኖ ያበላሻሉ፡፡ ሊጠቅሙአቸውና ወደ እግዚአብሔር በግ ሊያመጡአቸው የሚፈልጉአቸው በእግዚአብሔር የማያምኑ ሰዎች ይጠላሉ፡፡ ለተመልካች እስከሚያስጠላ ድረስ ትልቅ ለውጥ ሳይደረግ ከጤና ጋር በተገናኘ ሁኔታ በሴቶች ልብስ ላይ ብዙ መሻሸሎች ሊደረጉ ይችላሉ፡፡ {2SM 478.2}Amh2SM 478.2

    የሴቶች ቅርጽ በሚያጠብቁ የውስጥ ልብሶችና ከጅማት በተሰሩ መቀነቶች መጨቆን የለበትም፡፡ ልብና ሳንባዎች ጤናማ ተግባር እንዲኖራቸው ለማድረግ ቀሚሳቸው ፍጹም ቀላል መሆን አለበት፡፡ ቀሚሳቸው ከቦቲ ጫማ ጫፍ ትንሽ ዝቅ ማለት አለበት፤ ነገር ግን ከእግረኞች መንገድና ከአውራ ጎዳና ቆሻሻን እስከማይጠርግ እና በእጅ ወደ ላይ አንስቶ መያዝ እስከማያስፈልግ ድረስ አጭር መሆን አለበት፡፡ ሴቶች የቤት ውስጥ ሥራ በሚሰሩበት ጊዜ፣ እና በተለይ ይብዛም ይነስም ከቤት ውጭ ሥራን የመስራት ግዴታ ላለባቸው ሴቶች፣ ከዚህም አጠር ያለ ቀሚስ ተገቢ፣ ምቹና ጤናማ ሊሆን ይችላል፡፡ ለዚህ ዓይነት አለባበስ የሚያስፈልገው አንድ ቀለል ያለ ጉርድ፣ ወይም ቢበዛ ሁለት፣ ሲሆን እነዚህ በወገብ ላይ መቆለፍ ወይም በገመድ መንጠልጠል አለባቸው፡፡ ዳሌዎች የተሰሩት ከባድ ሸክም ለመሸከም አይደለም፡፡ ክብደታቸው ዳሌን ወደ ታች የሚጎትቱ ሴቶች የሚለብሱአቸው ከባድ ጉርዶች በቀላሉ ለማይድኑ ብዙ በሽታዎች መንስኤዎች ናቸው፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት በሕመሙ የሚሰቃዩ ግለሰቦች በሽታውን ያመጣው ምን እንደሆነ ካለማወቃቸው የተነሳ በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ዋጋ ቢሶች እስኪያደርጋቸው ድረስ ወገባቸውን በመታጠቅና ከባድ ጉርዶችን በመልበስ አካላዊ ሕጎችን መጣሳቸውን ስለሚቀጥሉ ነው፡፡ ብዙዎች ወዲያውኑ እንዲህ በማለት በቃለ አጋኖ ይናገራሉ፣ «የዚህ ዓይነት ቀሚስ ለምን ፋሽኑ ያልፍበታል!” ቢያልፍበትስ? በብዙ መንገድ አሮጌውን ፋሽን እንድንከተል እመኛለሁ፡፡ ባለፉት ትውልዶች የነበሩት ሴቶች ተለይተው የሚታወቁበት ጊዜው ያለፈበት የአለባበስ ጥንካሬ ሊኖረን ቢችል ኖሮ እጅግ ተፈላጊ ይሆን ነበር፡፡ የሴቶች የአለባበሳቸው ሁኔታ የምግብ ፍላጎታቸውን ካለመቆጣጠር ጋር ተደምሮ አሁን ያሉበትን ደካማና በሽተኛ ሁኔታ አስከትሏል ብዬ ስናገር በቂ መረዳት ሳይኖረኝ አይደለም፡፡ እጆቿንና እግሮቿን ማልበስ እንደሚገባት የምታለብስ ሴት ከአንድ ሺህ ሴቶች መካከል አንድ ብቻ ነች፡፡ የቀሚሱ ርዝመት ምንም ቢሆን ሴቶች እጃቸውንና እግራቸውን ልክ እንደ ወንዶች በደንብ ማልበስ አለባቸው፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው ውስጣቸው ገበር ያላቸውና በቁርጭምጭሚት አከባቢ በላስቲክ የጠበቁ ወይም ሙሉ ሆነው ተሰርተው ወደ ታችኛው ጫፍ የጠበቡ ሱሪዎችን በመልበስ ነው፡፡ እነዚህ ሱሪዎች እስከ ጫማ ድረስ መድረስ አለባቸው፡፡ በልብስ የተሸፈኑ እጅና እግሮች እና ቁርጭምጭሚቶች ከንፋስ ይጠበቃሉ፡፡ የእጆችና እግሮች ምቾት በሚሞቅ ልብስ ከተጠበቀ ደም ስለማይቀዘቅዝና በአካል ውስጥ በየተፈጥሮ መንገድን ተከትሎ እንዳይዘዋወር ስለማይከለከል የደም ዝውውር ይመጣጠንና ጤናማና ንጹህ ይሆናል፡፡ How to Live, No. 6, pp. 57-64. {2SM 478.3}Amh2SM 478.3

    ኤለን ኋይት ለጤና ተስማሚ፣ መጠነኛ፣ ወጪ ቆጣቢ እና ከክርስቲያናዊ የዋህነት ጋር የሚስማማ አለባበስን አስፈላጊነት ሁል ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ፊት ብታስቀምጥም፣ ከእነዚህ መርሆዎች ወሰን ሳይወጣ ልብስ «ለዘመኑ ገጣሚ መሆን አለበት» ወደሚለው እውነታ የአንባቢው ትኩረት ተስቧል፡፡ በ1897 ዓ.ም የተወሰኑ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን ሴቶች፣ ለትንቢት መንፈስ ምክሮች ታማኝ በመሆን፣ በ1860ዎቹ ተቀባይነት ወዳገኘው አለባበስ መመለስ እንዳለባቸው ወይም እንደሌለባቸው ጥያቄ ሲያቀርቡላት «እንደ ትክክለኛ ደንብ ለሁሉም የሚሆን አንድ ዓይነት የአለባበስ ዘዴ» እንዳልተሰጣት መከረቻቸው፡፡ «እህቶቻችን ወደ ተሃድሶ ዘመን አለባበስ የመመለስ ግዴታ እንዳለባቸው እግዚአብሔር አላመለከተኝም፡፡» ይህን አቋም ለምን እንደያዘች ምክንያቱን የሚገልጽ መግለጫ ሙሉ በሙሉ እንደ ተጨማሪ መግለጫ ሆኖ በዲ. ኢ ሮቢንሰን በ1965 ዓ.ም በተጻፈው ዘ ስቶሪ ኦቭ አወር ሄልዝ መሰጅ በሚል መጽሐፍ ገጽ 441- 445 ላይ ይገኛል፡፡ …አሰባሳቢዎች፡፡Amh2SM 479.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents