Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሁልጊዜ ለውጥ (እድገት) የምታሳይ

    የቤተ ክርስቲያን ሥራ እየጨመረ ሊሄድና ወሰኖቿን ልታሰፋ ነው፡፡ ሚስዮናዊ ሥራዎቻችን እየሰፉ የሚሄዱ ናቸው፤ ወሰናችንን ማስፋት አለብን፡፡…ልዩ ባሕርያችንን ለመጠበቅ በምናደርገው ጥረት ውስጥ የከረረ ጠብ ቢኖርም በመጽሐፍ ቅዱስ የምናምን ክርስቲያኖች እንደመሆናችን ሁልጊዜ እድገት እያሳየን ነው፡፡ Letter 170, 1907 (May 6, 1907).Amh2SM 396.4

    ላለፉት ሃምሳ አመታት እንደ ሕዝብ የእግዚአብሔር መንፈስ ከእኛ ጋር ስለመሆኑ የነበረን ማረጋገጫ ዛሬ ራሳቸውን በጠላት ወገን በማሰለፍ የእግዚአብሔርን መልእክት ለመቃወም እየተዘጋጁ ያሉትን ሰዎች ፈተና ይቋቋማል፡፡ Letter 356, 1907 (Oct. 24, 1907).Amh2SM 397.1

    ይህን ሀሳብ ቀጥለው በነበሩት አመታት በበርካታ አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ ማቅረብ የሚያበረታታ እና ወሳኝ ነው፡፡ Compilers.Amh2SM 397.2

    ወንድሞቼ ሆይ፣ ምንም እንኳን ሁላችሁም መገንዘብ ባትችሉም እነዚህን ነገሮች እጽፍላችኋለሁ፡፡ የእግዚአብሔር ዓይኖች በሕዝቡ ላይ መሆናቸውን ባላምን ኖሮ ተመሳሳይ የሆነ ነገር ደግሜ ደጋግሜ ልጽፍላችሁ ድፍረት አይኖረኝም ነበር፡፡ እግዚአብሔር እየመራው እና እያስተማረው ያለ ሕዝብ አለው፡፡ Letter 378, 1907 (Nov. 11, 1907).Amh2SM 397.3

    በመላው ዓለም ላይ ላሉት የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች እግዚአብሔር ለራሱ የተለየ ሐብት እንድንሆን እንደጠራን እንድነግራቸው ታዝዣለሁ፡፡ በምድር ላይ ያለችው ቤተ ክርስቲያን እስከ ፍጻሜ ዘመን ድረስ በሰራዊት ጌታ መንፈስና ምክር በደንብ አንድ ሆና እንድትቆም መርጧታል፡፡ Letter 54, 1908 (Jan. 21, 1908).Amh2SM 397.4

    በዚህች ምድር ላይ ለእግዚአብሔር እንደ ራሱ ቤተ ክርስቲያን የከበረ ምንም ነገር የለም፡፡ እሱን የሚሹትን ሰዎች በቅንዓት እንክብካቤ ይጠብቃቸዋል፡፡ የሰይጣን አገልጋዮች የእሱን ሕዝብ መብቶች ለመንጠቅ ጥረት ሲያደርጉ ከማየት የበለጠ እግዚአብሔርን የሚያስከፋ ሌላ ምንም ነገር የለም፡፡ እግዚአብሔር ሕዝቡን አልተወም፡፡ ሰይጣን እነርሱ የሰሯቸውን ስህተቶች በመጠቆም ራሳቸውን ከእግዚአብሔር እንደለዩ ሊያሳምናቸው ይሞክራል፡፡ በኃጢአት ላይ ድልን ለመቀዳጀት እየጣሩ ያሉ ሰዎችን ተስፋ ለማስቆረጥ ክፉ መላእክት በሁሉም መንገድ ይሻሉ፡፡ በፊታቸው ያለፈውን ዋጋ ቢስነት በመያዝ ጉዳያቸው ተስፋ የሌለው እንደሆነ አድርጎ ያቀርባል፡፡ ነገር ግን ኃያል የሆነ አዳኝ አለን፡፡ ክርስቶስ ከሰማይ በሰብአዊነት ተሸፍኖ ወደዚህች ምድር የመጣው በዚህ ዓለም የጽድቅን መርሆዎች ለመተግበር ነበር፡፡ እንደ ግል አዳኛቸው አድርገው የሚቀበሉትን ለማገልገል፣ የኃጢአትን ኃጢአተኝነት በማመን ንሰሃ የሚገቡትን ለመርዳት ኃይል ተሰጥቶታል፡፡ «ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም» (ዕብ. 4፡15)፡፡ Letter 136, 1910 (Nov. 26, 1910).Amh2SM 397.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents