Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 29—ፈውስ ሰጭ ነገሮች ጥቅም

    ሕመምን ለማስታገስና ጤናን ለመመለስ

    እያንዳንዱን አጋጠሚ ተጠቀሙ፡፡ ሕመምን እንዲያስታግሱና ተፈጥሮ ራሷን ወደ ቀድሞ ሁኔታ ለመመለስ በምታደርገው ጥረት እንዲረዱ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ፈውስ ሰጭ ነገሮች መጠቀም እምነትን መካድ አይደለም፡፡ ከሕመማቸው ለመፈወስ እንዲጸለይላቸው የሚጠይቁ በሽተኞች ከእግዚአብሔር ጋር መተባበርና ጤንነታቸውን ለመመለስ ምቹ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ራሳቸውን ማስቀመጥ እምነትን መካድ አይደለም፡፡ የሕይወት ህጎችን እውቀት እንድናገኝ እግዚአብሔር በእኛ ኃይል ሥር አስቀምጧል፡፡ ይህ እውቀት እንድንጠቀምበት እኛ ልንደርስ በምንችልበት ቦታ ተቀምጧል፡፡ ጤናን ለመመለስ ከተፈጥሮ ሕጎች ጋር በተጣጣመ ሁኔታ በመሥራት መጠቀም የምንችለውን እያንዳንዱን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም እያንዳንዱን መገልገያ ሥራ ላይ ማዋል አለብን፡፡ The Ministry of Healing, pp. 231, 232 (1905).Amh2SM 286.1

    ማግኘት የምንችለውን ነገር ተጠቀሙ፡፡ ሕመምተኞች ምንም ዓይነት ፈዋሽ መድሃኒት መጠቀም የለባቸውም የሚለው አመለካከትህ ስህተት ነው፡፡ ሰዎች ሊያገኙ በሚችሉበት ቦታ ያሉ ነገሮችን ካልተጠቀሙ፣ ወይም እግዚአብሔር በንጹህ አየርና ውኃ ውስጥ ያስቀመጣቸውን ቀላል ፈውሶች ለመጠቀም እምቢ ሲሉ እግዚአብሔር ሕሙማንን አይፈውስም፡፡Amh2SM 286.2

    በክርስቶስ ዘመንና በሐዋርያት ዘመን ሐኪሞች ነበሩ፡፡ ሉቃስ የተወደደው ሐኪም ተብሏል፡፡ ፈዋሽ መድሃኒቶችን የመጠቀም ችሎታን እንዲሰጠው በእግዚአብሔር ታመነ፡፡Amh2SM 286.3

    ጌታ ለሕዝቅያስ በዕድሜው ላይ አሥራ አምስት ዓመት እንደሚጨምርለት በነገረው ጊዜ ቃሉን እንደሚፈጽም ምልክት እንዲሆን ፀሐይ አሥር ምዕራፍ ወደ ኋላ እንድትሄድ ባደረገ ጊዜ ለምን ቀጥተኛ የሆነ የመፈወስ ኃይሉን አልተጠቀመም? በቁስሉ ላይ የሾላ ፍሬን ጥፍጥፍ እንዲጨምር ነገረው፤ ያ የተፈጥሮ ፈዋሽ መድኃኒት በእግዚአብሔር ተባርኮ ፈወሰው፡፡ የተፈጥሮ አምላክ አሁንም ሰብአዊ ወኪሎች የተፈጥሮ ፈውሶችን እንዲጠቀሙ ያዛል፡፡Amh2SM 286.4

    ወንድሜ ሆይ፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ርቀት መሄድ እችላለሁ፣ ነገር ግን ለአሁኑ ጥቂት አጋጣሚዎችን ብቻ ተናግሬ እተዋለሁ፡፡ (ከዚያም ከሰል ጥቅም ላይ የዋለባቸውን ሁለት አጋጣሚዎች ተከታተል፡፡ ምዕራፍ 30ን ይመልከቱ)፡፡Amh2SM 287.1

    ጽንፈኛ የሆኑ ሀሳቦችንና ግምቶችን እንዳንቀበል በጣም መጠንቀቅ እንዳለብን እነዚህ ነገሮች ሁሉ ያስተምሩናል፡፡ የመድኃኒት ሕክምናን በተመለከተ ያሉህን ሀሳቦች ማክበር አለብኝ፤ ነገር ግን ሕመምተኞች ራሳቸው በዚህ ጉዳይ ላይ ብልህ እስኪሆኑ ድረስ መድሃኒቶችን ሙሉ በሙሉ እንደማትቀበል እንዲያውቁ ሁልጊዜ አታድርግ፡፡ ብዙ ጊዜ ያሉህን እምነቶች በሙሉ በመናገር ማንንም ሳትጠቅም ያለህን ተጽእኖ በምትጎዳበት ቦታ ራስህን ታስቀምጣለህ፡፡ በመሆኑም ራስህን ከሕዝብ ትለያለህ፡፡ ጠንካራ የሆኑ አግባብ የሌላቸውን ጥላቻዎች ማረም አለብህ፡፡ Letter 182, 1899 (To a worker in an overseas field).Amh2SM 287.2

    የእግዚአብሔር ፈውሶች፡፡ የፈውስ ጥበብን የምንለማመድባቸው በርካታ መንገዶች አሉ፣ ነገር ግን ሰማይ የሚያረጋግጠው አንድ መንገድ ብቻ አለ፡፡ እግዚአብሔር ያዘጋጃቸው ፈውሶች ኃይለኛ በሆኑ ባሕርያቶቻቸው ሥራ የማያበዙና አካልን የማያደክሙ ቀላል የተፈጥሮ ወኪሎች ናቸው፡፡ እንደ ንፁህ አየርና ውኃ፣ ንጽህና፣ ተመጣጣኝ ምግብ፣ የሕይወት ንጽህና፣ እና በእግዚአብሔር ላይ ያለ ጽኑ መታመን ብዙዎች ከማጣታቸው የተነሳ እየሞቱ ያሉ ፈውሶች ናቸው፤ ነገር ግን ጥበብ ያለበት የእነዚህ ፈውሶች አጠቃቀም ሰዎች የማያደንቁትን ሥራ ስለሚሻ ፈውሶቹ ጊዜ እያለፈባቸው ነው፡፡ ንፁህ አየር፣ የሰውነት እንቅስቃሴ፣ ንፁህ ውኃ፣ እና ንፁህና ምቹ አከባቢ ያለምንም ወጪ ሁሉም ሊያገኛቸው የሚችላቸው ነገሮች ናቸው፤ ነገር ግን መድሃኒቶች በገንዘብ ወጪም ሆነ በአካል ላይ ከሚያደርሱት ተጽእኖ አንጻር ውድ ናቸው፡፡ Testimonies, Vol. 5, p. 443 (1885).Amh2SM 287.3

    እጅግ ቀላል የሆኑ ፈውሶችን ተጠቀሙ፡፡ ተፈጥሮ ነገሮችን ወደ ትክክለኛ ሁኔታቸው ለመመለስ ጥቂት እርዳታን ትሻለች፡፡ ይህ እርዳታ በቀላል ፈውሶች ውስጥ፣ በተለይም ተፈጥሮ ራሷ በምትሰጣቸው እንደ ንጹህ አየር እና ስለ አተነፋፈስ ባለ የከበረ እውቀት፣ ንፁህ ውኃ እና እንዴት ሥራ ላይ መዋል እንዳለበት በማወቅ፣ ከተቻለ በቤት ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ክፍል በቂ የፀሐይ ብርሃን እንዲያገኝ በማድረግ እና እሱን በመጠቀም ስለሚገኙ ጥቅሞች ብልህነት ባለው እውቀት ይገኛል፡፡ እነዚህ ነገሮች በሙሉ በብቃታቸው ኃይለኛ ስለሆኑ እንዴት ጤናማ በሆነ ሁኔታ መብላትና መልበስ እንዳለበት እውቀት ያገኘ ሕመምተኛ በምቾት፣ በሰላምና በጤንነት ይኖራል፤ ተፈጥሮን ከመርዳት ይልቅ ኃይሎቿን ሽባ የሚያደርጉ መድሃኒቶችን አፉ ውስጥ ለመጨመር አይሸነፍም፡፡ በሕመምና ሥቃይ ላይ ያሉ ሰዎች የጤና ተሃድሶ መርሆዎችን በተመለከተ የሚያውቁትን ያህል ብቻ ቢኖሩ ኖሮ ከአሥር ሕመምተኞች መካከል ዘጠኙ ከሕመማቸው ይፈወሳሉ፡፡ Medical Ministry, pp. 223, 224 (Manuscript 22, 1887).Amh2SM 287.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents