Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለጥያቄ የተሰጠ ምላሽ

    ውድ ጓደኛ፣Amh2SM 344.1

    በነጭ እና በጥቁር ዝርያ ክርስቲያን ወጣቶች መካከል ጋብቻ ይመከራልን? ለሚለው ጥያቄ ለመመለስ በቀደምት ልምምዴ ይህ ጥያቄ የቀረበልኝ ሲሆን ጌታ ሰጥቶኝ የነበረው ብርሃን ይህ እርምጃ መወሰድ እንደሌለበት ነው፤ ይህ የሚሆንበት ምክንያት ግጭትንና ውዝግብን መፍጠሩ አይቀሬ ስለሆነ ነው፡፡ ሁልጊዜም እሰጥ የነበረው ምክር ተመሳሳይ ነበር፡፡ ሕዝባችን የዚህ ዓይነት ባሕርይ ያላቸውን ጋብቻዎች እንዲፈጽሙ መደፋፈር የለባቸውም፡፡ ጥቁር ወንድም እግዚአብሔርን ከምትወድና ትዕዛዛቱን ከምትጠብቅ ጥቁር እህት ጋር መጋባት አለበት፡፡ ከጥቁር ወንድም ጋር ጋብቻ ለመፈጸም እያሰበች ያለች ነጭ እህት፣ ጌታ በዚህ አቅጣጫ እየመራ ስላልሆነ፣ ይህን እርምጃ ከመውሰድ ትታቀብ፡፡Amh2SM 344.2

    በዚህ ጉዳይ ላይ ከሚነሳ ግጭት የተነሳ የሚባክን ጊዜ የለም፡፡ የዚህ ዓይነት ባሕርይ ያለው ጥያቄ አገልጋዮቻችንን ከሥራ እንዲያስተጓጉል መፈቀድ የለበትም፡፡ የዚህን ዓይነት እርምጃ መውሰድ ውዝግብና እንቅፋት ይፈጥራል፡፡ የእግዚአብሔር ሥራ ወደ ፊት እንዲቀጥል ወይም ለእግዚአብሔር ክብር አይሆንም፡፡ Letter 36, 1912.Amh2SM 344.3

    እግዚአብሔር የፈጠራቸውን ፍጥረታት ከየትኛውም ዘር ቢሆኑ በርኅራኄ ይመለከታቸዋል፡፡ «እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ፊት ይኖሩ ዘንድ በሁሉም አገሮች የሚኖሩትን ሰዎች ከአንድ ደም ፈጠረ፡፡»….ለደቀ መዛሙርቱ ሲናገር አዳኙ እንዲህ አለ፣ «ሁላችሁም ወንድማማቾች ናችሁ፡፡” እግዚአብሔር የሁላችንም የጋራ አባት ሲሆን እያንዳንዳችን ደግሞ የወንድማችን ጠባቂዎች ነን፡፡ The Review and Herald, Jan. 21, 1896.Amh2SM 344.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents