Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ 38—በውትድርና ጥያቄ ላይ

    ጦርነት በብሉይ ኪዳን ዘመን

    ሙሴ ምድያናውያንን እንዲያስጨንቃቸውና እንዲመታቸው እግዚአብሔር ያዘዘበት ምክንያት እነርሱም እሥራኤልን በማታለያቸው በማስጨነቅ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እንዲተላለፉ ስላታለሉአቸው ነው፡፡Amh2SM 332.1

    ሙሴ ስለ እሥራኤል ልጆች ምድያማውያንን እንዲበቀልና ከዚያ በኋላ ወደ ሕዝቡ እንዲሰበስብ አዘዘው፡፡ ሙሴም ጦረኛ የሆኑ ወንዶች ከምድያማውያን ጋር ለመዋጋት እንዲዘጋጁ አዘዘ፡፡ እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው ከሚድያማውያን ጋር ተዋግተው ወንዶቻቸውን በሙሉ ገደሉአቸው፣ ነገር ግን ሴቶችንና ሕጻናትን ማረኩአቸው፡፡ በለዓም ከሚድያማውያን ጋር ተገድሎ ነበር፡፡ «ሙሴና ካህኑ አልዓዛርም የማህበሩም አለቆች ሁሉ ከሰፈሩ ወደ ውጭ ሊገናኙአቸው ወጡ፡፡ ሙሴም ከዘመቻ በተመለሱት በጭፍራ አለቆች፣ በሻለቆችና በመቶ አለቆች ላይ ተቆጣ፡፡ ሙሴም አላቸው፡- በውኑ ሴቶችን ሁሉ አዳናችኋቸውን? እነሆ እነዚህ በፌጎር ምክንያት በበለዓም ምክር እግዚአብሔርን ይበድሉ ዘንድ ለእሥራኤል ልጆች እንቅፋት ሆኑ፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር ማህበር ላይ መቅሰፍት ሆነ» (ዘሁ. 31፡ 13-16)፡፡ Amh2SM 332.2

    ሙሴ ለጦርነት የሚሄዱት ሰዎች ከምድያም ወገን ወንዶችን፣ ሴቶችንና ወንዶች ልጆቻቸውን እንዲገድሉ አዘዛቸው፡፡ በለዓም የእሥራኤልን ልጆች ለጥቅም ሽጦ ነበር፣ ሃያ አራት ሺህ እሥራኤላውያንን መስዋዕት በማድረግ ተቀባይነትን ካገኘው ሕዝብ ጋር አብሮ ነበር፡፡Amh2SM 332.3

    ሕዝቡ ከሌላ ሕዝብ ጋር እንዲዋጉ በማድረጉ እግዚአብሔርን እንደ ጨካኝ አድርገው ቆጥረውታል፡፡ ይህ ድርጊት ቸር ከሆነው ባሕርዩ ጋር የሚጻረር ነው ይላሉ፡፡ ነገር ግን ዓለምን የፈጠረውና በምድር ላይ እንዲኖር ሰውን የፈጠረው በእጁ ሥራዎች ላይ ገደብ የለሽ ቁጥጥር ስላለው ደስ እንዳለው ማድረግ እና በእጁ ሥራዎች ላይ ደስ ያለውን ማድረግ መብቱ ነው፡፡ ሰው ፈጣሪውን ለምን እንዲህ ታደርጋለህ ብሎ የመጠየቅ መብት የለውም፡፡ በእሱ ባሕርይ ውስጥ ኢፍትሃዊነት የለም፡፡ እሱ የዓለም ገዥ ሆኖ ሳለ ከተገዦቹ መካከል የሚበዙት በሥልጣኑ ላይ በማመጽ ሕጉን ረግጠዋል፡፡ በረከትን በልግስና ሰጥቷቸው እና በሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ ዙሪያቸውን ከቦ ሳለ እጆቻቸው ለሰሩአቸው ለእንጨትና ለድንጋይ፣ ለብርና ለወርቅ ምስሎች ሰገዱ፡፡ ለልጆቻቸው እነዚህ አማልክት ሕይወትና ጤና የሚሰጡ፣ መሬታቸውን ፍሬያማ የሚያደርጉ እና ሃብትና ክብር የሚሰጡ እንደሆኑ አስተማሩ፡፡ በእሥራኤል አምላክ ላይ ቀለዱ፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝብ ሥራ ጽድቅ ስለሆነ ናቁአቸው፡፡ «ሰነፍ በልቡ አምላክ የለም ይላል፡፡ በሥራቸው ረከሱ፣ ጎሰቆሉ» (መዝ. 14፡1)፡፡ የኃጢአታቸው ጽዋ እስኪሞላ ድረስ እግዚአብሔር ታግሶአቸዋል፣ ከዚያም ፈጣን ጥፋት አምጥቶባቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ሕዝቡን የተጠቀመው ያስጨነቁአቸውንና ጣዖት እንዲያመልኩ ያታለሉአቸውን ኃጢአተኛ ሕዝብ ለመቅጣት እንደ መሣሪያ ነበር፡፡Amh2SM 333.1

    የቤተሰብ ስዕል በፊቴ ቀርቦልኝ ነበር፡፡ ከልጆቹ መካከል ግማሾቹ የአባትን መስፈርቶች ለመማርና ለመታዘዝ ጉጉት የነበራቸው ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ሥልጣኑን የሚረግጡና በእርሱ የቤተሰብ አስተዳደር ላይ ንቀት በማሳየት የሚፈነጥዙ ይመስል ነበር፡፡ በአባታቸው ቤት ውስጥ ያሉትን ጥቅሞች የሚጋሩና ያለማቋረጥ ከልግስናው የሚቀበሉ ናቸው፡፡ ለሚያገኙት ነገር ሁሉ ሙሉ በሙሉ በአባታቸው የሚደገፉ ናቸው፣ ነገር ግን አመስጋኞች አይደሉም፡፡ ከለጋስ አባታቸው የሚቀበሏቸውን ጥቅሞች በሙሉ በራሳቸው ጥረት ያገኙ ይመስል ራሳቸውን የሚያሳዩት በትዕቢት ነው፡፡ አባት የልጆቹን አመጸኛና ምሥጋና ቢስ የሆነውን አክብሮት የጎደለው ተግባር ቢገነዘብም ይታገሳቸዋል፡፡Amh2SM 333.2

    በጊዜ ብዛት እነዚህ አመጸኛ ልጆች ተጨማሪ እርምጃዎችን በመራመድ እስከ አሁን ታዛዥ በነበሩት የአባታቸው ቤተሰብ አባላት ላይ ተጽእኖ በማሳደር ወደ አመጽ መምራት ይፈልጋሉ፡፡ ያኔ የአባት ስብዕናና ሥልጣን በተግባር ላይ ይውላል፡፡ ከአባታቸው የተቀበሏቸውን ፍቅርና በረከቶች ያለአግባብ የተጠቀሙ ብቻ ሳይሆኑ በአባታቸው ቤተሰብ ውስጥ ላሉት በጥበብ ለተሞላ እና ሚዛናዊ ለሆነ ሕግ ተገዥ የነበሩትን ጥቂቶች ለመገልበጥ የሞከሩትን አመጸኛ ልጆች ከቤቱ ያስወጣቸዋል፡፡Amh2SM 334.1

    አመጸኛ ከሆኑት የቤተሰብ አባላት የማነሳሳት ተጽዕኖ የተነሣ ደስታቸው ለአደጋ ተጋልጦ ለነበሩት ለጥቂት ታማኞች ብሎ የማይታዘዙ ልጆችን ከቤተሰቡ ይለያል፤ የቀሩትን ታማኝና ታዛዥ የሆኑትን ወደ ራሱ ለማስጠጋት ይሰራል፡፡Amh2SM 334.2

    እግዚአብሔር በዚህ መልክ ለልጆቹ ሰርቷል፡፡ ነገር ግን ሰው በእውርነቱ እግዚአብሔርን የማያውቁ ሰዎችን እርኩሰቶች ሳያስተውል በማለፍ የእግዚአብሔርን ሕግ በእግራቸው የሚረግጡትን እና ሰማይን የሚዳፈሩ ኃጢአተኞችን ሰይገነዘብ ያልፋል፡፡ በዚህ ቦታም አያቆሙም፣ ነገር ግን በክፋታቸው የእግዚአብሔርን ሕዝብ አመለካከት በማዛባት ሕጉን እንዲተላለፉና በጥበብ በተሞሉ የያህዌ መስፈርቶች ላይ ግልጽ የሆነ ንቀት እንዲያሳዩ ተጽእኖ በማሳደራቸው ይፈነድቃሉ፡፡Amh2SM 334.3

    አንዳንዶች ለእነርሱ ምህረት የለሽ እና ጭካኔ ያለበት የሚመስላቸውን የእግዚአብሔርን ጠላቶች ጥፋት ብቻ ማየት ይችላሉ፡፡ ሌላኛውን ወገን አያዩም፡፡ ነገር ግን ስሜታዊና ተለዋዋጭ የሆነ ሰው፣ ጉራ ከተሞላበት ልግስናው ጋር፣ ክስተቶች እንዲከሰቱ የሚፈቅድና የሚቆጣጠር ስላልሆነ ዘላለማዊ ምሥጋና ይሰጥ፡፡ «የኃጢአን ምህረት ግን ጨካኝ ነው» (ምሳሌ 12፡ 10) spiritual gifts, vol. 4, pp. 49-52.Amh2SM 334.4