Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ልጆች በትንሳኤ መስመሮች

    የሚስስ ኋይት መንታ እህት በሞተች ጊዜ የተጻፈ

    እዚህ እጅግ የምንናፍቃቸው ተስፋዎቻችን በዋግ የተመቱ ናቸው፡፡ የምንወዳቸው በሞት ይለዩናል፡፡ ዓይኖቻቸውን ጨፍነን ለመቃብር እናዘጋጅና ከዓይናችን አርቀን እንቀብራቸዋለን፡፡ ነገር ግን ተስፋ መንፈሳችንን ይደግፋል፡፡ የምንለያቸው ለዘላለም አይደለም፣ ነገር ግን የምንወዳቸውን በኢየሱስ ያንቀላፉትን እንገናኛለን፡፡ ከጠላት ምድር እንደገና ተመልሰው ይመጣሉ፡፡ ሕይወት ሰጭ የሆነው እየመጣ ነው፡፡ እርሱ ሲመጣ የተለያዩ ዓይነት ቅዱሳን መላእክቶች ያጅቡታል፡፡ የሞትን ገመድ ይበጥሳል፣ የመቃብርን እግር ብረቶች ይሰብራል፣ የከበሩ ምርኮኞች በጤንነትና በማይሞት ውበት ከመቃብር ይወጣሉ፡፡ Amh2SM 259.6

    ትንንሽ ሕጻናት ከአፈር አልጋቸው የማይሞቱ ሆነው ሲወጡ ወዲያውኑ ወደ እናቶቻቸው ክንዶች ይበራሉ፡፡ ለዘላለም ላይለዩ እንደገና ይገናኛሉ፡፡ ነገር ግን ብዙዎቹ ትናንሽ ልጆች እናቶች አልነበሩአቸውም፡፡ ከእናት አስደሳች የሆነ የድል መዝሙር በነጻ እንሰማለን፡፡ እናት የሌላቸውን ሕጻናት መላእክት በመቀበል ወደ ሕይወት ዛፍ ይመሩአቸዋል፡፡ Amh2SM 260.1

    ኢየሱስ በትንንሽ ጭንቅላቶቻቸው ላይ የብርሐንን ወርቃማ ቀለበት፣ ዘውድ ይጭንላቸዋል፡፡ ውድ “የኢቫ’’ እናት በዚያ ቦታ ተገኝታ ትንንሽ ክንፎቿ በደስታ በተሞሉ በእናቷ ጉያዎች እንዲታጠፉ እግዚአብሔር ያድርግ፡፡ --The Youth’s Instructor, April, 1858.Amh2SM 260.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents