Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ፈውስ የተፈጸመበት አጋጣሚ

    አገልጋይ የሆነው የ----ጉዳይ በፊቴ ቀርቦ ነበር፤ የያዕቆብን አስተምህሮ በማክበር ለታመመች እህት እንዲጸልይ ሰማኒያ ማይል ርቆ ወዳለ ቦታ ተልኮ ነበር፡፡ ሂዶ ከልቡ ጸለየላት፣ እሷም ጸለየች፤ አገልጋዩ የእግዚአብሔር ሰው እና የእምነት ሰው እንደሆነ አመነች፡፡ ሐኪሞች ተስፋ በመቁረጥ በሳንባ ነቀርሳ ሕመም እንድትሞት ትተዋት ነበር፡፡ ከተጸለየላት በኋላ ወዲያውኑ ተፈወሰች፡፡ ከዚያም ተነስታ እራት አዘጋጀች፣ ይህን ነገር ላለፉት አሥር አመታት አድርጋ አታውቅም ነበር፡፡ አገልጋዩ መጥፎ ሕይወቱም የተበላሸ ነበር፣ ነገር ግን ታላቅ ሥራ ተሰራ፡፡ እሱም ክብሩን ለራሱ ወሰደ፡፡Amh2SM 347.2

    ከዚያም ከላይ የተጠቀሰው እይታ በድጋሚ በፊቴ አለፈ፡፡ ሴትዮዋ እውነተኛ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር እንደነበረች አየሁ፤ መዳን እንዳለባት አምና ነበር፡፡ ጸሎታቸውን ተመለከትሁ፡- አንዱ ጉም የበዛበት እና ጨለማ የሆነ ስለነበር ወደ ታች ወደቀ፤ ሌላኛው ጸሎት ደግሞ ከብርሃን ወይም አልማዝ ከሚመስሉ ፍንጣቂዎች ጋር የተቀላቀለ ስለነበር ወደ ላይ ወደ ኢየሱስ ተነሳና እሱም እንደ ጣፋጭ እጣን ወደ አባቱ ልኮት ለሕመምተኛዋ ወዲያውኑ የብርሃን ጮራ ተላከላትና ጤንነቷ ተመልሶ ብርታት አገኘች፡፡ መልአኩ እንዲህ አለ፣ እግዚአብሔር እውነተኛና ልባዊ የሆነ ጸሎትን እያንዳንዷን ቅንጣት ይሰበስባል፤ እንደ አልማዞች ይሰበሰቡና ውጤት ያስገኛሉ፣ ወይም መልስ ይሰጣቸዋል፤ እግዚአብሔር ክቡር የሆነውን መጥፎ ከሆነው ይለያል፡፡ ግብዝንና ኃጢአተኛን ቢታገስም በመጨረሻ ይመረምረዋል፡፡ እንደ አረንጓዴ ባሕረ-ሰላጤ ዛፍ ለአጭር ጊዜ ታማኝ ከሆነው ጋር ቢለመልምም ከንቱነቱ የሚጋለጥበት ጊዜ ይመጣና ግራ ይጋባል፡፡ Letter 2, 1851. Amh2SM 347.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents