Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    የእግዚአብሔር ሥራ በእርጋታና በክብር ይገለጻል

    የዛሬ ሁለት ሳምንት አከባቢ፣ እየጻፍኩ ሳለሁ፣ ልጄ ደብሊዩ ሲ ኋይት ወደ ክፍሌ መጣና ሊያናግሩኝ የሚፈልጉ ሁለት ሰዎች ታች እንዳሉ ነገረኝ፡፡ ታች ወዳለው ሳሎን ወረድኩና የእግዚአብሔርን ቃል እንደሚከተሉና በምስክሮች እንደሚያምኑ የሚናገሩ ባልና ሚስት ተገናኘሁ፡፡ ላለፉት ሁለት ወይም ሶስት አመታት ከተለመደው ውጭ የሆነ ልምምድ ነበራቸው፡፡ በልባቸው ታማኝ የሆኑ ሰዎች ይመስሉ ነበር፡፡ {2SM 41.1}Amh2SM 41.1

    ከልምምዳቸው ጥቂቱን እየተረኩልኝ አዳመጥኳቸሁና ጌታችንን ለማየት የጠበቅነው ሰዓት ካለፈ በኋላ ወግ አጥባቂነትን ለመጋፈጥና ለመቃወም ማድረግ ስለነበረብን ሥራ የሆነ ነገር ነገርኳቸሁ፡፡ በእነዚያ ፈታኝ ቀናት እጅግ ውድ ከነበሩ አማኞቻችን መካከል አንዳንዶቹ ወደ ወግ አጥባቂነት ተመርተው ነበር፡፡ ፍጻሜ ከመምጣቱ በፊት በመንፈስ ቅዱስ እንደሚመሩ በሚናገሩ ሰዎች መካከል እንግዳ የሆኑ መገለጦችን እንደምንመለከትም አክዬ ነገርኳቸው፡፡ እነዚህን ከእግዚአብሔር ያልሆኑ፣ ነገር ግን የብዙዎችን አእምሮ ከቃሉ አስተምህሮ ወደ ሌላ አቅጣጫ ለመቀየር የተሰሉ ልዩ መገለጦችን ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ነገር አድርገው የሚይዙ ሰዎች አሉ፡፡ {2SM 41.2}Amh2SM 41.2

    በምድራችን ታሪክ በአሁኑ ዘመን የወግ አጥባቂነትንና ሥርዓት አልበኝነትን ምልክት የሚያሳየውን ማንኛውንም ነገር ለመከላከል በጣም መጠንቀቅ አለብን፡፡ የማያምኑ ሰዎችን አእምሮ ሊቀሰቅሱ የሚችሉትን ልዩ ዓይነት እንቅስቃሴዎች ሁሉ መከላከል አለብን፡፡ እንደ ሕዝብ በስሜት እንደምንመራና ወጣ ባሉ ድርጊቶች በታጀበ ሁካታና ምስቅልቅል እንደምንደሰት እንዲያምኑ እንዳንመራቸው መጠንቀቅ አለብን፡፡ በመጨረሻዎቹ ቀናት ውስጥ የወቅቱ እውነት ጠላት ከመንፈስ አሰራሮች ጋር የማይጣጣሙትን፣ ነገር ግን የሆነ አዲስና እንግዳ ነገርን ለመቀበል ተዘጋጅተው የሚቆሙትን ወደ ስህተት ለመምራት የተሰሉ መገለጦችን ያመጣል፡፡ {2SM 41.3}Amh2SM 41.3

    ለዚህ ወንድምና ለባለቤቱ እኔ በወጣትነቴ ከ1844 ዓ.ም ማለፍ በኋላ ለአጭር ጊዜ ያለፍኩበት ልምምድ፣ ያኔ ከገጠመንና በጌታ ስም ከገሰጽነው ጋር የሚመሳሰል ማንኛውንም ልምምድ ከመቀበል እጅግ እንድጠነቀቅ እንደመራኝ ነገርኳቸሁ፡፡ {2SM 41.4}Amh2SM 41.4

    በዚህ ወቅት ወግ አጥባቂነት በስህተት የእግዚአብሔር መንፈስ አሰራር ተደርገው ከተወሰዱ ሥራዎች ጋር በመታጀብ ወደ ቤተ ክርስቲያናችን እንዲመጣ ከመፍቀድ የበለጠ የእግዚአብሔርን ሥራ የሚጎዳ ሌላ ነገር የለም፡፡ {2SM 42.1}Amh2SM 42.1

    ይህ ወንድምና እህት መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ በወረደው ኃይል ስለወረደብን መጣልን የሚሉትን ልምምዳቸውን ሲዘረዝሩ ያ ልምምዳቸው በቀድሞው ልምምዳችን ልንጋፈጠውና ልናርመው የተጠራነው ነገር ትክክለኛው ቅጂ ይመስል ነበር፡፡ {2SM 42.2}Amh2SM 42.2

    ቃለ መጠይቃችንን ወደ ፍጻሜ ስናመጣ ሳለ ወንድም ኤል በጸሎት ሆነን ሳለን ከዚህ በፊት ገልጸውልኝ እንደነበረው ሁሉ ባለቤቱ በዚያ ልምምድ ውስጥ ትሆንና ልምምዱ ከእግዚአብሔር መሆን አለመሆኑን እኔ መለየት እንድችል በጸሎት እንድንተባበር ሀሳብ አቀረበ፡፡ አንድ ሰው እነዚህን የተለዩ መገለጦች ለማሳየት ሀሳብ ሲያቀርብ የእግዚአብሔር ሥራ ላለመሆኑ ጽኑ ማስረጃ እንደሆነ መመሪያ ስለተሰጠኝ በዚህ ሀሳብ መስማማት አልቻልኩም፡፡ {2SM 42.3}Amh2SM 42.3

    እነዚህ ልምምዶች ተስፋ ወደ መቁረጥ ስሜት እንዲመሩን መፍቀድ የለብንም፡፡ እንደ እነዚህ ያሉ ልምምዶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ እኛ ይመጣሉ፡፡ አእምሮን ጥልቅ ከሆነ የመንፈስ ቅዱስ አንቀሳቃሽነት ለሚያርቁ እንግዳ ልምምዶች ቦታ አንስጥ፡፡ ሁል ጊዜ የእግዚአብሔር ሥራ የሚገለጸው በመረጋጋትና በክብር ነው፡፡ ማንኛውም ውዝግብ የሚፈጥርና ለክርስቶስ ዳግም ምጻት ለመዘጋጀት በዓለም ውስጥ እንድንሰራ እግዚአብሔር የሰጠንን ሥራ ለመስራት ያለንን ቅናት የሚያዳክም ነገር ተቀባይነት እንዲያገኝ አንፈቅድም፡፡ --Letter 338, 1908. {2SM 42.4}Amh2SM 42.4