Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ 8—የሀሰተኛ ነቢያትን ሀሳቦች መጋፈጥ

    ልንጠብቅ የምንችለው ነገር

    በተለየ ሁኔታ እግዚአብሔር እንዳስተማራቸው የሚናገሩና ሌሎችን ለመምራት የሚሞክሩ ብዙ ሰዎችን እንዳይ ተደርጌ ነበር፤ እነዚህ ሰዎች ለተግባር ካሉአቸው የተሳሳቱ ሀሳቦች በመነሳት እግዚአብሔር በፍጹም ያልሰጣቸውን ሥራ ይሰራሉ፡፡ የዚህ ውጤት ግራ መጋባት ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው በግል ደረጃ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማስተዋል እንዲችል እሱን ከልቡ ይፈልግ፡፡ --Letter 54, 1893. {2SM 72.1}Amh2SM 72.1

    ራዕዮች እንዳሉአቸው የሚናገሩ ሰዎች ይኖራሉ፡፡ በውጭ አገርና በአሜሪካ ብዙዎች ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ ሊመሩ ስለሆነ ራዕዩ ከእሱ እንደሆነ እግዚአብሔር ግልጽ ማስረጃ ሲሰጥህ ልትቀበል ትችላለህ፣ ነገር ግን በሌላ በማንኛውም ማስረጃ አትቀበል፡፡ --The Review and Herald, May 25, 1905. {2SM 72.2}Amh2SM 72.2