Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 23—በገንዘብ ምክንያት የእግዚአብሔርን ሥራ ለመልቀቅ እያቀደ ላለ ሰው የተሰጠ ምክር

    {በህዳር 3 ቀን 1892 ዓ.ም የማተሚያ ቤት ሥራ መሪ በግል ካገጠመው የገንዘብ ማነስ እፍረት የተነሳ ከድርጅት ውጭ ሥራ ለመቀጠር ተቋሙን ለመልቀቅ እንደወሰነ ለማሳወቅ ለኤለን ጂ ኋይት ጸፈላት፡፡ በገቢው መኖር ስላልቻለ በስምንት ዓመት ውስጥ ከድርጅቱ የተበደረው 1244 ዶላር ዕዳ አለበት፡፡ በተመሳሳይ ወቅት በተመሳሳይ ሁኔታ በጤና ማሰልጠኛ ተቋም ላይ ዕዳ አከማችቷል፡፡ ሁለቱም ተቋሞች ሂሳቡን እንዲያወራርድ በትህትና እየጠየቁት ነበሩ፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ዕዳውን ለመክፈል ተስፋ በማድረግና በእግዚአብሔር ቤት ዳግመኛ ተመልሶ ላለመስራት በመወሰን ውጭ በተሻለ ደሞዝ ተቀጥሮ ለመስራት ድርጅቱን ለቆ ለመውጣት በቂ ምክንያት እንዳለው ተሰማው፡፡ ቀጥሎ ያለው ደብዳቤ ሚስስ ኋይት የሰጠችው መልስ ነው፡፡---አሰባሳቢዎች}Amh2SM 210.1

    ወንድሜ ሆይ፣ በደብዳቤህ የሪቪው ቢሮን እንደምትለቅ ነግረሃል፡፡ ከጠቀስካቸው ምክንያቶች የተነሳ ከስራው ለመለየት ፈቃደኛ ልትሆን ስለምትችል አዝናለሁ፡፡ ምክንያቶችህ አሁን ካለህ ልምምድ የበለጠ ገንዘብ የማግኘት ልምምድ እንደነበረህ ይነግሩኛል፡፡ እምነትህ በጣም ደካማ ነው፡፡ ከአንተ ቤተሰብ ይልቅ ትልቅ የቤተሰብ መጠን ያላቸው ሌሎች ቤተሰቦች የአንተን ደሞዝ ግማሽ ያህል እያገኙ ያለ አንዳች ማጉረምረም ራሳቸውን ያኖራሉ፡፡ በቦታው ላይ ስለነበርን ምን እየተናገርኩ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ የሪቪውን ቢሮ ብትለቅም ባትለቅም ከድርጊትህ መማር ያለብህ ከፍተኛ የሆነ ዋጋ ያላቸው ትምህርቶች አሉ፡፡ ለቀህ እንዳትወጣ ለመገፋፋት ነጻነት አይሰማኝም፤ ከሕያው ውኃ ምንጮች በደንብ ካልጠጣህ በስተቀር አገልግሎትህ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ Amh2SM 210.2

    አንተ ከለቀቅክ ቦታውን ማን እንደሚይዝ አላውቅም፣ ነገር ግን ጌታ ለማድረግ ያቀደውና እንዲደረግ የሚመኘው ሥራ በባትል ክሪክ ላለችው ቤተ ክርስቲያን ከተሰራ በማንኛውም ችግር ውስጥ እንደሚረዳቸው እርግጠኛ ነኝ፡፡ እርሱ የግዴታ አገልግሎት አይፈልግም፡፡ ቃላቶች ወደ ነፍስ የሚገቡበትን መንገድ ካላገኙና መላውን ሰው ለክርስቶስ እንዲገዛ ካላደረጉ በስተቀር ሰብአዊ ወኪል ፈተናና ሲቃይ ሲደርስበት የጌታን መንገድ ከመከተል ይልቅ የራሱን ዝንባሌ ለመከተል ይመርጣል፡፡ ከሚኒያፖሊስ ስብሰባ ወዲህ ግልጽና ጉልህ የሆነ የብርሃን ጮራን በመስጠት እየበራ ያለው እውነት ነፍስህን እንዲያጥለቀልቅ ተመኝቼ ነበር፡፡ ነገር ግን ከጻፍካቸው ደብዳቤዎች በብርሃን እየሄድክ እንዳልሆንክ አውቃለሁ፡፡. . .Amh2SM 211.1

    ከሕትመት ቢሮ ጋር በተገናኘ መልኩ አንድ ሰው ማንኛውንም ቦታ ቢይዝ፣ ያ ሰው ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ አይከፈለውም፤ ለዚህ ምክንያቱ እግዚአብሔር በዚህ መንገድ ስለማይሰራ ነው፡፡ መንፈሳዊ እይታ የለህም፣ የእግዚአብሔር ሥራ በመስዋዕትነት እንደተመሰረተና በመስዋዕትነት ብቻ ወደ ፊት መቀጠል እንደሚችል ማየት እንድትችል ሰማያዊው ቅባት አስፈልጎሃል፡፡. . .Amh2SM 211.2

    ከማተሚያ ቤት ጋር ግንኙነት ያላቸውና ከእነርሱ በፊት የነበሩ ሰዎች ሥራውን ለመገንባት ምን ያህል እንደከፈሉ ከልምድ የማያውቁ ወይም ማወቅ የማይፈልጉ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ ኋላ ወደ ሥራው የገቡ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር አብረው ለመስራት ሽርክና አልፈጠሩም፡፡ ሰብአዊ ወኪል ከመለኮት ጋር ሕብረት ሲፈጥር ገዥ ሊሆኑ የሚገቡ መርሆዎችን አይገነዘቡም፡፡ «በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲሆንለት እንጂ ማንም እንዳይጠፋ አንድያ ልጁን አሳልፎ እስኪሰጥ ድረስ እግዚአብሔር እንዲሁ ዓለምን ወዷልና፡፡» የዚህ ራስን መስዋዕት የሚያደርግ ፍቅር ተካፋይ ያልሆነ ማንም ቢሆን ለእግዚአብሔር ለመስራት ዝግጁ አይደለም፡፡ ብዙዎች የራሳቸውን የራስ ወዳድነት ሸክም እንደ ከበረ ሀብት በመቁጠርና በእርሱ ላይ በመንጠልጠል፣ እንዲሁም የራሳቸውን መንገድ ተግተው በመጠበቅ እየተሰናከሉ ናቸው፡፡ «ጌታ ሆይ፣ ክፈትልን” በማለት የሰማይን ደጅ ሲያንኳኩ ብዙዎች የሚሰሙት ድምጽ «እዚህ መግባት የሚችሉት ‹አንተ መልካምና ታማኝ ባርያ፣ በጥቂት ታምነሃልና በብዙ እሾማሃለሁ፡- ና ወደ ጌታህ ደስታ ግባ› የሚለውን ሰማያዊ በረከት መቀበል የሚችሉት ብቻ ናቸው፡፡› ነገር ግን አንተ ራስህን በታማኝነት አገልግለሃል፣ ለራስህ ጥሩ በመሆን የራስህን ፍላጎት ለማሟላት ሰርተሃል፡፡ በሰማይ ሀብት አላከማቸህም” የሚለውን ድምጽ ብዙዎች ይሰማሉ፡፡ Amh2SM 211.3

    የነፍሳችንን መዳን በተመለከተ ግድ የለሾች ስንሆን ለአንድ አፍታ እንኳን ከአደጋ የተጠበቅን አይደለንም፡፡ ከዳኑት መካከል ብዙዎች መነሳትና የተግባር መንገዳቸውን መቀየር ይኖርባቸዋል፡፡ የመጨረሻው ቀናት አደጋዎች በላያችን ናቸው፡፡ ጠንካራ፣ ሕያውና በሚሰራ እምነት ከመለኮት ጋር የመገናኘት ተጽእኖ ብቻ ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ ሰራተኞች ሊያደርገን ይችላል፡፡ የኃይማኖትን ራስን የመካድና መስዋዕት የማድረግ ክፍል መቀበል የማይፈልጉ ሰዎች ከክርስቶስ ጋር በክብሩ ተካፋዮች መሆን አይችሉም፡፡ የሕይወትን አክሊል የሚያገኙት ሰዎች ሁሉ በጸሎት የተሞላ የቃል ጥናት እና ጽኑ የሆነ ጥረት ማድረግ አለባቸው፡፡ Amh2SM 212.1

    ማናቸውም ቢሆኑ በመወለድ ወይም በሥልጣን ወይም በትምህርት ካገኙአቸው ጥቅሞች የተነሳ ዋጋ እንዲሰጣቸው መጠየቅ እንደሚችሉ አይሰማቸው፡፡ እነዚያን ጥቅሞች እንዴት ነው ያገኙት? ያገኙአቸው በክርስቶስ አማካይነት ብቻ ነው፡- የዘላለም ሕይወት እንዲኖራቸው የሚሹት ሁሉ ምሳሌውን እንዲቀዱ እግዚአብሔር ይጠራቸዋል፡፡ የወንጌል የመጀመሪያዎቹ መርሆዎች እውነትና ጽድቅ ሲሆኑ ክርስቶስ በማንኛውም ሰብአዊ ወኪል ውስጥ እውቅና የሚሰጣቸው መርሆዎች ናቸው፡፡ ከልብ የሆነ ፈቃዳችንን ለእግዚአብሔር ማስገዛት መኖር አለበት፤ አሉን የምንላቸውን የራሳችንን መልካምነቶች በመካድ ወደ ቀራኒዮ መስቀል መመልከት አለብን፡፡ ይህ ለእግዚአብሔር ራስን አሳልፎ መስጠት ሰብአዊ ወኪል ከመለኮታዊ ወኪሎች ጋር ለመተባበር ጥረትን ይጠይቃል፤ ቅርንጫፍ በግንዱ መኖር አለበት፡፡. . .Amh2SM 212.2

    ከአማኞች መካከል ብዙዎች፣ እጅግ ብዙዎች የሚበሉት በቂ ምግብ የላቸውም፣ ነገር ግን በድህነታቸውም ቢሆን ወደ ጌታ ግምጃ ቤት አስራትንና ስጦታን ያመጣሉ፡፡ ከባድና ፈታኝ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ የእግዚአብሔርን ሥራ እንዲቀጥል ማድረግ ምን ማለት እንደሆነ የሚያውቁ ብዙ ሰዎች በማተሚያ ቤት ውስጥ ገንዘባቸውን አፍሰዋል፡፡ በፈቃዳቸው ችግርንና ድህነትን ታግሰዋል፣ ለስራው ስኬትም ነቅተው በመጠበቅ ጸልየዋል፡፡ ስጦታዎቻቸውና መስዋዕቶቻቸው ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን ለጠራቸው ያላቸውን ልባዊ የሆነ ምስጋና ይገልጣሉ፡፡ ከዚህ የበለጠ መልካም መዓዛ ያለው ተጽእኖ ወደ ሰማይ ማረግ አይችልም፡፡ ጸሎቶቻቸውና ስጦታዎቻቸው በእግዚአብሔር ፊት እንደ መታሰቢያ ይወጣሉ፡፡ Amh2SM 212.3

    ነገር ግን የእግዚአብሔር ሥራ በስፋቱ ሁሉ አንድ ስለሆነ በሁሉም ዘርፎች እነዚያው መርሆዎች ሊገዙ፣ ያው መንፈስ ሊገለጥ ይገባል፡፡ የሚስዮናዊ ሥራን ማህተም መያዝ አለበት፡፡ እያንዳንዱ የሥራ መምሪያ ከሁሉም የወንጌል መስክ ክፍሎች ጋር የተገናኘ ስለሆነ አንዱን የስራ መምሪያ የሚቆጣጠረው መንፈስ በመላው የሥራ መስክ ውስጥ ይታወቃል፡፡ ከሰራተኞች መካከል የተወሰኑት ከፍተኛ ደሞዝ ከተቀበሉ ከፍተኛ ደሞዝ እንዲከፈላቸው የሚጠይቁ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ያሉ ሌሎች ሰዎች ስላሉ በስራው ልብ ውስጥ ራስን መስዋዕት የማድረግ መንፈስ ይጠፋል፡፡ ሌሎች ተቋማት ያንኑ መንፈስ ስለሚወስዱና እግዚአብሔር በፍጹም ለራስ ወዳድነት እውቅና ስለማይሰጥ የእግዚአብሔር በጎነት ከእነርሱ ይወገዳል፡፡ ከዚህ የተነሳ በፍጥነት ወደ ፊት እየሄደ ያለው ሥራችን ወደ መጨረሻ ይመጣል፡፡ ሥራው ወደ ፊት መቀጠል የሚችለው ቀጣይነት ባለው መስዋዕትነት ብቻ ነው፡፡ ከሁሉም የዓለም ክፍሎች ሥራውን ወደ ፊት ለማስቀጠል ለወንዶችና ሴቶች ጥሪዎች እየመጡ ናቸው፡፡ «መቆየት አለባችሁ፤ በግምጃ ቤት ውስጥ ገንዘብ የለም” ለማለት እንገደድ ይሆን?Amh2SM 212.4

    ወንድም ኤክስ በቢሮ ውስጥ የነበረውን ስራ የቀድሞ ታሪክ ያውቃል፤ ራስን መካድንና መስዋዕትነትን በተመለከተ እግዚአብሔር ለእርሱና ለሌሎች የላካቸውን ምስክርነቶች ያውቃል፡፡ የእውነትን መስፈርት ከፍ ለማድረግና ሥራውን ለመመስረት ገንዘብ ስለሚያስፈልግባቸው ብዙ የስራ መስኮች እውቀት አለው፡፡ የክርስቶስ መንፈስ ቢኖረው ኖሮ የክርስቶስን አእምሮ ይገልጥ ነበር፡፡ Amh2SM 213.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents