Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ) - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 20—የሰራተኞችን ደሞዝ በተመለከተ ገዥ የሆኑ አጠቃላይ መርሆዎች

    መስዋዕትነት ባለው ሥራ ውስጥ ያለ እርካታና በረከት

    የእግዚአብሔር ሥራ በልባቸው ውስጥ ያለ ሰዎች እየሰሩ ያሉት ለራሳቸው ወይም ለሚያገኙት ጥቂት ደሞዝ አለመሆኑን እና ጌታ የሚያገኙትን ጥቂት እነርሱ ይሰራል ብለው ከሚያስቡት በላይ እንዲሰራ እንደሚያደርግ መገንዘብ አለባቸው፡፡ ራስን መስዋዕት በማድረግ ሥራ ወደ ፊት ሲቀጥሉ ሳለ እርሱ እርካታና በረከት ይሰጣቸዋል፡፡ በክርስቶስ የዋህነት ስንሰራ ሳለ እርሱ እያንዳንዳችንን ይባርከናል፡፡ አንዳንዶች ከፍተኛ ደሞዝ እንዲከፈላቸው ሲፈልጉ ሳይ ለራሴ እንዲህ እላለሁ፣ «የከበረ በረከት እያጡ ናቸው፡፡” ይህ እውነት እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ የዚህን እውነትነት በተደጋጋሚ በተግባር አይቻለሁ፡፡ Amh2SM 179.1

    ወንድሞቼ ሆይ፣ አሁን ከምናገኘው ደሞዝ የበለጠ ካላገኘን የተሰጠንን ሥራ መሥራት የማንችል ካልሆነ በስተቀር ከፍተኛ ደሞዝ እንዲከፈለን ሳንጠይቅ ጠንክረን ማድረግ የምንችለውን ነገር እናድርግ፤ ነገር ግን የሚከፈለን ደሞዝ በቂ እንኳን ባይሆን አስፈላጊነቱን እኛ እንደተመለከትነው ሌሎች ደግሞ ይዩ፡፡ አስፈላጊነቱን እንዲያዩ እግዚአብሔር በልባቸው ስለሚያስቀምጥ እኛ ከምንደረድራቸው ሺህ ቃላቶች የበለጠ ተጽእኖ ያለውን ቃል ይናገራሉ፡፡ በሕዝብ ፊት ተገቢ የሆነ አቋም እንዲኖረን የሚያደርግ ቃል ይናገራሉ፡፡ ጌታ ረዳታችንና አምላካችን፣ የፊት ጠባቂያችንና የኋላ ደጀናችን ነው፡፡ Amh2SM 179.2

    ከእግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ የሆነ ግንኙነት እንዲኖረን ራሳችንን ስናቀርብ በሄድንበት ሁሉ ስኬት እናገኛለን፤ የምንፈልገው ገንዘብ ሳይሆን ስኬት ነው፡፡ የሚያስፈልገን ሕያው ስኬት ሲሆን ያሳየነውን ራስን መካድ ስለሚያውቅ እግዚአብሔር ይሰጠናል፡፡ የምንከፍለውን እያንዳንዱን መስዋዕትነት እርሱ ያውቃል፡፡ ያሳያችሁት ራስን መካድ ምንም ዓይነት ልዩነት እንደማያመጣ፣ የበለጠ ትኩረት እና ወዘተ እንደሚያስፈልጋችሁ ልታስቡ ትችሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በጌታ ዘንድ ትልቅ ልዩነት ያመጣል፡፡ ግለሰቦች ከፍተኛ ደሞዝ ለማግኘት በተንጠራሩ ቁጥር ከዚህ በፊት ቆመውበት በነበረው ከፍ ባለ ቦታ እንዳይቆሙ የሚያደርግ የሆነ ነገር በልምምዳቸው ውስጥ እንደሚመጣ በተደጋጋሚ እንዳይ ተደርጌያለሁ፡፡ ነገር ግን መስዋዕትነት እየከፈሉ እንደሆነ በግልጽ የሚታይ ደሞዝ ሲቀበሉ ጌታ ራስን መካዳቸውን ይመለከትና ስኬትና ድል ይሰጣቸዋል፡፡ ይህ ነገር በተደጋጋሚ ቀርቦልኛል፡፡ የተፈተኑ አገልጋዮቹ ለመክፈል ፈቃደኛ ለሆኑት ለእያንዳንዱ መስዋዕትነት በምስጢር የሚያይ አምላክ በግልጥ ይከፍላቸዋል፡፡--Manuscript 12, 1913.Amh2SM 179.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents